መዝሙር 105
ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 19)
1. የይሖዋን ግርማ ይናገራሉ፤
የእጁ ሥራዎች በጠፈር ላይ ያሉ።
ቀን በሰማይ ላይ ይታያል ክብሩ።
ሌሊት ’ሚታዩት ከዋክብት ኃይሉን ያውጃሉ።
2. የአምላክ ሕግ ነፍስን ያለመልማል፤
ልጅ አዋቂ ሳይልም ሁሉንም ይጠቅማል።
አገዛዙ ጽድቅና ፍትሕ ነው።
ቃሉ መሬት ጠብ የማይል፣ እንደ ማር ጣፋጭ ነው።
3. አምላካዊ ፍርሃት ንጹሕ፣ ቀጣይ ነው።
ት’ዛዛቱ ከወርቅ ይበልጣል ዋጋቸው።
ሥርዓቱ ሕዝቦቹን ይጠብቃል።
ክብሩ፣ ዝናውና ስሙ ዘላለም ከፍ ይበል።
(በተጨማሪም መዝ. 111:9፤ 145:5ን እና ራእይ 4:11ን ተመልከት።)