መዝሙር 6
ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 19)
1. የይሖዋን ግርማ ይናገራሉ፤
የእጁ ሥራዎች፣
በጠፈር ላይ ያሉ።
ቀን በሰማይ ላይ ይታያል ክብሩ።
ሌሊት ’ሚታዩት ከዋክብት
ኃይሉን ያውጃሉ።
2. ያምላክ ሕጎች ሕይወትን ያድሳሉ፤
ማሳሰቢያዎቹም
ጥበብ ይሰጣሉ።
የሱ ፍርዶች ፍትሕ ያለባቸው፣
ቃሉ መሬት ጠብ የማይል፣
እንደ ማር ጣፋጭ ነው።
3. ያምላክ ት’ዛዝ ከወርቅ ይበልጣል ዋጋው፤
እሱን መፍራት ንጹሕ፣
ዘላለማዊ ነው።
መመሪያውም ጥበቃ ያስገኛል።
ክብሩ፣ ዝናውና ስሙ
ዘላለም ከፍ ይበል።
(በተጨማሪም መዝ. 111:9፤ 145:5ን እና ራእይ 4:11ን ተመልከት።)