የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ll ክፍል 13 ገጽ 28-29
  • አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ ይኖርብናል?
  • አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ ወዳጆች መጥፎ ከሆነ ነገር ይርቃሉ
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • አምላክ የሚጠላቸው ድርጊቶች
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • ክፍል 13
    አምላክን ስማ
  • ብቸኛውን እውነተኛ አምላክ ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርገው
    እውነተኛውን አንድ አምላክ አምልክ
ለተጨማሪ መረጃ
አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
ll ክፍል 13 ገጽ 28-29

ክፍል 13

አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ከመጥፎ ነገር ራቅ። 1 ቆሮንቶስ 6:9, 10

አምላክ የሚጠላቸው ነገሮች—ስርቆት፣ ስካር፣ ዕፅ መውሰድ፣ መጣላት፣ ለምስሎች መጸለይ ጣዖት አምልኮ

ይሖዋን የምንወደው ከሆነ እሱ የሚጠላቸውን ነገሮች አናደርግም።

ይሖዋ እንድንሰርቅ፣ እንድንሰክር ወይም አደንዛዥ ዕፆች እንድንወስድ አይፈልግም።

አምላክ ነፍስ ግድያን፣ ፅንስ ማስወረድንና ግብረ ሰዶምን ይጠላል። ከዚህም በላይ ስግብግቦች እንድንሆን ወይም ከሌሎች ጋር እንድንጣላ አይፈልግም።

ጣዖታትን ማምለክ ወይም በመናፍስታዊ ድርጊቶች መካፈል የለብንም።

መጥፎ ነገሮችን የሚፈጽሙ ሰዎች በቅርቡ በምትመጣው ምድራዊ ገነት ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም።

  • አምላክ ስለ አስማታዊ ድርጊቶች ያለው አመለካከት ምንድን ነው?—ዘዳግም 18:10-12

  • ጣዖታትን ማምለክ የሌለብን ለምንድን ነው?—ኢሳይያስ 44:15-20

መልካም የሆነውን ነገር አድርግ። ማቴዎስ 7:12

አምላክን የሚያስደስቱ ነገሮች—ለሌሎች ፍቅር ማሳየት፣ ሐቀኛ መሆን እንዲሁም ይቅር ባይ መሆን

አምላክን ማስደሰት ከፈለግን እሱን ለመምሰል ጥረት ማድረግ አለብን።

ደግና ለጋስ በመሆን ለሌሎች ፍቅር አሳይ።

ሐቀኛ ሁን።

መሐሪና ይቅር ባይ ሁን።

ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች ለአንድ ሰው ሲሰብኩ

ስለ ይሖዋና ስለ መንገዶቹ ለሌሎች ተናገር።—ኢሳይያስ 43:10

  • ይሖዋን ለመምሰል ጣር።—1 ጴጥሮስ 1:14-16

  • ለሌሎች ፍቅር አሳይ።—1 ዮሐንስ 4:7, 8, 11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ