ትምህርት 14
የአምላክ ወዳጆች መጥፎ ከሆነ ነገር ይርቃሉ
ሰይጣን ሰዎች መጥፎ ነገሮችን እንዲያደርጉ ይፈትናቸዋል። የአምላክ ወዳጅ ለመሆን የሚፈልግ ሰው ይሖዋ የሚጠላቸውን መጥላት ይኖርበታል። (መዝሙር 97:10) የአምላክ ወዳጆች ሊርቋቸው ከሚገቧቸው ተግባሮች መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው:-
የፆታ ብልግና። “አታመንዝር።” (ዘጸአት 20:14) ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት መፈጸምም ስህተት ነው።—1 ቆሮንቶስ 6:18
ስካር። “ሰካሮች . . . የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።”—1 ቆሮንቶስ 6:10
መግደል፣ ጽንስ ማስወረድ። “አትግደል።”—ዘጸአት 20:13
ስርቆት። “አትስረቅ።”—ዘጸአት 20:15
ውሸት። ይሖዋ “ሐሰተኛ ምላስ” ይጠላል።—ምሳሌ 6:17
የኃይል ድርጊትና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ቁጣ። “ዓመፃን የወደዳት ግን” ይሖዋ ይጠላዋል። (መዝሙር 11:5) ‘ከሥጋ ሥራዎች አንዱ ቁጣ ነው።’—ገላትያ 5:19, 20
ቁማር። “ከሚስገበገቡ . . . ጋር አትተባበሩ።”—1 ቆሮንቶስ 5:11 የ1980 ትርጉም
የዘርና የጎሳ ጥላቻ። “ጠላቶቻችሁን ውደዱ . . . ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ።”—ማቴዎስ 5:43, 44
አምላክ የሚነግረን የሚጠቅመንን ነገር ብቻ ነው። መጥፎ ከሆኑ ነገሮች መቆጠብ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ከይሖዋና ከምሥክሮቹ በምታገኘው እርዳታ አምላክ የማይደሰትባቸውን ነገሮች ከማድረግ ልትቆጠብ ትችላለህ።—ኢሳይያስ 48:17፤ ፊልጵስዩስ 4:13፤ ዕብራውያን 10:24, 25