የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 7 ገጽ 24-ገጽ 25 አን. 1
  • የባቤል ግንብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የባቤል ግንብ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰዎች አንድ ትልቅ ግንብ ሠሩ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • በዓለም ላይ ያሉት ቋንቋዎች የመጡት “ከባቤል ግንብ” ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የኖኅ መርከብ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • እንዳሰቡት ስማቸውን አላስጠሩም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 7 ገጽ 24-ገጽ 25 አን. 1
ይሖዋ ቋንቋቸውን ካዘበራረቀባቸው በኋላ ሰዎቹ የባቤልን ግንብ አብረው መሥራት አልቻሉም

ትምህርት 7

የባቤል ግንብ

ከጥፋት ውኃው በኋላ የኖኅ ልጆችና ሚስቶቻቸው ብዙ ልጆች ወለዱ። የቤተሰባቸው ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ልክ ይሖዋ እንደነገራቸው ወደተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው መኖር ጀመሩ።

አንዳንድ ቤተሰቦች ግን ይሖዋን አልታዘዙም። እንዲህ አሉ፦ ‘አንድ ከተማ ገንብተን እዚሁ እንኑር። ቁመቱ ሰማይ የሚደርስ ረጅም ግንብ እንገነባለን። ከዚያም ታዋቂ እንሆናለን።’

ይሖዋ እነዚህ ሰዎች በሚያደርጉት ነገር አልተደሰተም፤ ስለዚህ ሥራቸውን ለማስቆም ወሰነ። ይህን ያደረገው እንዴት እንደሆነ ታውቃለህ? የተለያየ ቋንቋ እንዲናገሩ አደረጋቸው። በዚህ የተነሳ እርስ በርስ መግባባት ስላልቻሉ የግንባታ ሥራቸውን አቆሙ። እየገነቡት የነበረው ከተማ ባቤል ተባለ፤ ባቤል ማለት “ዝብርቅ” ማለት ነው። በመሆኑም ሰዎች ወደተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነው በመላው ዓለም መኖር ጀመሩ። ነገር ግን በሄዱባቸው ቦታዎችም መጥፎ ነገር ማድረጋቸውን ቀጠሉ። ታዲያ በዚያ ጊዜ ይሖዋን የሚወድ ሰው አልነበረም ማለት ነው? በሚቀጥለው ምዕራፍ ላይ ይህን እንመለከታለን።

“ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ግን ከፍ ይደረጋል።”—ሉቃስ 18:14

ጥያቄ፦ የባቤል ሰዎች ምን አደረጉ? ይሖዋስ ያስቆማቸው እንዴት ነው?

ዘፍጥረት 11:1-9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ