የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 2/1 ገጽ 3
  • ከሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መተንበይ ምን ማለት ነው?
  • ሐሰተኛ ነቢያት
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ‘ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ’
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ትንቢት ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የአምላክን ነቢያት እንደ ምሳሌ አድርጋችሁ ተመልከቱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 2/1 ገጽ 3

ከሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ!

ብራዚላዊያን ባልና ሚስት ተኝተው እያሉ ሌቦች ቤታቸውን ሲሰብሩ ሰሙ። በጣም የፈሩት ባልና ሚስት በመኝታ ቤታቸው መስኮት አምልጠው ፖሊስ ለመጥራት ችለዋል። ከዚያ ወዲህ ግን ሚስቲቱ ባጋጠማት ሁኔታ በጣም ከመሰቀቋ የተነሣ በዚያ ቤት ውስጥ እንቅልፍ ሊወስዳት ስላልቻለ ወደ እናቷ ቤት ለመሄድ ተገድዳለች።

ቤቱ የተሰበረበት ወይም በአንድ ዓይነት መንገድ የተዘረፈበት ማንኛውም ሰው የዚህችን ሴት ችግር ሊረዳላትና ሊያዝንላት ይችላል። እንዲህ ዓይነት ገጠመኝ የሰውን አእምሮ ሊያቃውስ ይችላል። የሚያሳዝነው ግን ይህ አይነቱ ሥቃይ የሚያጋጥማቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሄዶአል። ይሁን እንጂ ከዚህ የበለጠ ጎጂ ውጤት የሚያስከትል የሌብነት ዓይነት አለ።

ይህ ይበልጥ ጎጂ የሆነ የሌብነት ዓይነት ምንድን ነው? ሌቦቹስ እነማን ናቸው? ኢየሱስ ስለዘመናችን ሲናገር “ብዙ የሐሰት ነቢያትም ይነሣሉ። ብዙዎችንም ያስታሉ” ብሎ በተናገረ ጊዜ ስለዚህ የሌብነት ዓይነትና ስለ ሌቦቹ ነግሮናል። (ማቴዎስ 24:11) የሐሰት ነቢያት ሌቦች ናቸው። ሌቦች የሆኑት በምን መንገድ ነው? የሚሠርቁትስ ምንድን ነው? ሥርቆታቸው ከሐሰት ትንቢታቸው ጋር የተሣሠረ ነው። ስለዚህ ጉዳዩን በበለጠ ለመረዳትና አስቀድመን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት መተንበይ ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ ያስፈልገናል።

መተንበይ ምን ማለት ነው?

ስለ መተንበይ ስታስብ ምናልባት መጀመሪያ ወደ ሐሳብህ የሚመጣው ነገር ወደፊት ስለሚሆነው ነገር በቅድሚያ መናገር ሊሆን ይችላል። ይህ በእርግጥ በቀድሞ ዘመን የነበሩት የአምላክ ነቢያት ሥራ አንዱ ገጽታ የነበረ ቢሆንም ዋነኛ ሥራቸው ግን ስለወደፊቱ ሁኔታ መናገር አልነበረም። ለምሳሌ ያህል ነቢዩ ሕዝቅኤል በራእይ “ለንፋስ ትንቢት እንዲናገር” በተነገረው ጊዜ ይፈለግበት የነበረው የአምላክን ትዕዛዝ መናገር ብቻ ነበር። (ሕዝቅኤል 37:9, 10) ኢየሱስ በካህናት ፊት ለፍርድ ቀርቦ ሳለ አሳዳጆቹ እየተፉበትና እየመቱት በመዘበት “ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን” ይሉት ነበር። ኢየሱስን ወደፊት የሚሆነውን ነገር እንዲተነብይላቸው መጠየቃቸው አልነበረም። የመቱት ሰዎች እነማን መሆናቸውን በአምላክ ኃይል እንዲያውቅ መወራረዳቸው ነበር።—ማቴዎስ 26:67, 68

እንዲያውም “መተንበይ” ወይም “ትንቢት” ተብሎ የተተረጐመው ቃል በመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ በመሠረቱ በአንድ ጉዳይ ላይ አምላክ ያለው ሐሳብ ምን እንደሆነ መናገር ወይም የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደሚገልጸው “የአምላክን ታላቅ ሥራ” መናገር ማለት ነው። (ሥራ 2:11) ብዙ ሰዎች በሐሰት ነቢያት የሚዘረፉት በዚህ ሁኔታ ነው። ይሁንና የሐሰት ነቢያት እነማን ናቸው? የሚሠርቁትስ ምንድን ነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ በኤርምያስ ዘመን ወደነበረው የእሥራኤል ሕዝብ ታሪክ እንመለስ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ