ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢዩኤል 1-3
‘ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ’
ቅቡዓን ክርስቲያኖች ትንቢት በመናገሩ ሥራ ይካፈላሉ። እነዚህ ቅቡዓን “ስለ አምላክ ታላቅ ሥራ” ይናገራሉ እንዲሁም ‘የመንግሥቱን ምሥራች’ ያውጃሉ። (ሥራ 2:11, 17-21፤ ማቴ. 24:14) ሌሎች በጎችም በዚህ ሥራ በመካፈል ቅቡዓኑን ይደግፋሉ
‘የይሖዋን ስም መጥራት’ ሲባል ምን ማለት ነው?
ስሙን ማወቅ
ስሙን ማክበር
በስሙ ባለቤት ላይ እምነት መጣልና በእሱ መታመን
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ትንቢት በመናገሩ ሥራ ቅቡዓኑን መደገፍ የምችለው እንዴት ነው?’