የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 3/1 ገጽ 22
  • ይሖዋ አንድን ታማኝ ወጣት ባረከ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ አንድን ታማኝ ወጣት ባረከ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመመሥከሩ ሥራ በቤትም ሆነ በትምህርት ቤት ፍሬ ያፈራል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲመርጡ እየረዳችኋቸው ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ወላጆችህን የምትመለከታቸው እንዴት ነው?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
  • ልጆቻችሁን ስታሠለጥኑ ይሖዋን ምሰሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 3/1 ገጽ 22

የመንግሥት አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

ይሖዋ አንድን ታማኝ ወጣት ባረከ

ታማኝ ወጣቶች በይሖዋ ዓይን በጣም ውድ ናቸው። የሚከተለው የአንድ ወጣት ተሞክሮ ሌሎች ወጣቶችም ይሖዋን በሚያገለግሉበት ጊዜ ፍጹም አቋማቸውን ጠብቀው እንዲገኙ ያበረታታቸዋል።

በአርጀንቲና አንድ የ11 ዓመት ልጅና ታናሽ ወንድሙ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራው እውነት የተሰኘውን መጽሐፍ ከሴት አያታቸው ጋር አጠኑ። ወዲያው የልጆቹ ወላጆች መቃወም ጀመሩና ልጆቹ ወደ መንግሥት አዳራሽ እንዳይሄዱ ከለከሉአቸው። ልጆቹም ለጊዜው በስብሰባዎቹ ላይ ለመገኘት ሲሉ በመታጠቢያ ክፍሉ መስኮት በኩል ወደ ጓሮ ዘለው በመውጣት ከዚያም በጎረቤት ጓሮ በኩል አድርገው ወደ መንግሥት አዳራሹ ሄዱ። በኋላም አንድ ሰው ልጆቹ በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች ላይ እንደሚሰበሰቡ ለእናታቸው ነገራት። እናቲቱም እንደምትመታቸው በመዛት አስፈራራቻቸው። ትንሹ ልጅም ፈርቶ ጥናቱን ተወ። ታላቁ ልጅ ግን ቀጠለ። ለአምስት ዓመት ወላጆቹ ሳያውቁ በስብሰባዎች ላይ መገኘት ቻለ።

ዕድሜው 16 ዓመት ሲሆን በትውልድ ከተማው የማይገኝ አንድ በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚሰጥ የትምህርት ዓይነት ለመከታተል ፈለገ። ከቤተሰቡ መራቁ እውነትን ለመከታተል የበለጠ ነፃነት ሊያገኝ ይችላል። ወላጆቹም እንዲሄድ ፈቀዱለትና ለሦስት ወራት ያህል ሁሉም ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ተካሄዱ። ከዚያ በኋላ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ልጁ ለብሔራዊ ባንዴራ ሰላምታ እንደማይሰጥና ብሔራዊ መዝሙርም እንደማይዘምር ለወላጆቹ አስታወቀ። ወጣቱም እነዚህን ነገሮች የማያደርገው በኅሊናው ምክንያት መሆኑን በርዕሰ መምህሩ፣ በወላጆቹ፣ በአንድ ጸሐፊ፣ በአንድ ጠበቃና በአሥር መምህራን ፊት ቆሞ በማስረዳት በጣም ጥሩ ምሥክርነት ሰጠ። (ዘጸአት 20:4, 5) ወላጆቹ ተናደዱ። እናቱም ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ የሴት አያቱ እንደሆነች በመቁጠር ልትገድላት ፈልጋ ሽጉጥ አዘጋጀች። ሆኖም ብቻዋን ሆና ልታገኛት አልቻለችም።

በኋላ የቤተሰቡ ወዳጅ በሆነ አንድ ሰው ምክርና በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ፈቃድ ወላጆቹ ልጁን የአእምሮ ሕክምና እምነቱን ያስተወዋል ብለው በማሰብ ወደ አእምሮ ሕሙማን ክሊኒክ ሊያስገቡት ወሰኑ። የክሊኒኩ ሠራተኞች ልጁን 96 ኪሎ ሜትር ርቆ ወደሚገኝ ቦታ በመኪና ወስደው ራሱን እስኪስት ድረስ ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንሱሊንና ሌሎችንም መድኃኒቶች ሰጡት። ሲነቃ የት እንዳለ እንኳን ማወቅ አልቻለም። ሙሉ በሙሉ ግራ ተጋባ። ማንንም አይለይም። በአእምሮው ላይ በደረሰው ጉዳት የተነሣ የማስታወስ ኃይሉን በከፊል አጣ። ሐኪሞቹ በልጁ ላይ ብዙ ምርመራ ካደረጉ በኋላ ምንም ዓይነት የአእምሮ ሁከት ሊያገኙበት ሳይችሉ ቀሩ። ይሁንና ክሊኒኩ ሕክምናውን ቀጠለ። ልጁ ራሱን ሲያውቅ ይሖዋ እንዳይተወውና ለመጽናት ኃይል እንዲሰጠው ባለማቋረጥ ይጸልይ ነበር። ይሖዋም በእርግጥ ጠበቀው። በመጨረሻም ከክሊኒኩ ወጣ።

በአንድ ወቅት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ልጁ ቃሉን ሊያጥፍ ተዘጋጅቶ እንደሆነ ጠየቀው። ልጁም ቃሉን እንደማያጥፍ ሲነግረው እንዲያውም ከቀድሞው የበለጠ ስላበደ ወደ ክሊኒኩ መልሰው እንዲወስዱት ርዕሰ መምህሩ ለወላጆቹ ነገራቸው። ወላጆቹም አንድ አዳሪ ቤት አስገቡትና ለባለቤቲቱ ልጁ ወደ ይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ እንዳይሄድ እንድትጠብቀው አደራ ብለው ሄዱ። ወላጆቹ ከሄዱ በኋላ ልጁ እንዴት ያለ ያልታሰበ ደስታ አገኘ! የአዳሪ ቤቱ ባለቤቶች የይሖዋ ምሥክሮች ነበሩ! በመጨረሻም ወላጆቹ ሐኪሞቹ እንዳታለሏቸው በማመን ከአእምሮ ሕክምናው አወጡት። በመሃሉ የአርጀንቲና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይሖዋ ምሥክሮች ልጆች ለባንዴራ ሰላምታ ባለመስጠታቸው ምክንያት ከትምህርት ቤት መባረር እንደማይኖርባቸው የሚገልጽ ብይን አስተላለፈ።

እነዚህ ፈተናዎች ይህን ታማኝ ወጣት ጠቅመውታልን? አዎን፣ እንዲህ ብሏል፦ “ለዶክተሮች፣ ለፕሮፌሰሮች፣ ለትምህርት ቤት ጓደኞቼ፣ ለወላጆቼና ለዘመዶቼ እንዲያውም ለመላው ከተማ ምሥክርነት ልሰጥ ችያለሁ። ወላጆቼ ከበፊቱ አቋማቸው ትንሽ ለስልሰዋል። ስለ ምሥክሮቹም የተሻለ ግንዛቤ አላቸው። አሁን መለስ ብዬ ስለልጅነቴ ዘመን ሳስብ አምላካችን ለሱ ታማኝ የሚሆኑትን ሰዎች እንዴት ባለ ርህራሄና ፍቅር እንደሚንከባከብ ለመገንዘብ ችዬአለሁ። ሁኔታው መዝሙራዊው በመዝሙር 27:10፦ “አባቴና እናቴ ቢተዉኝም እንኳን ይሖዋ ግን ይቀበለኛል” (አዓት) ብሎ እንደተናገረው ነው።

አሁን ይህ ወጣት ዕድሜው 23 ዓመት ሆኖአል። ሚስት አግብቷል። በይሖዋ አገልግሎትም በጣም ንቁ ነው። በእርግጥም የይሖዋ ድጋፍ ወሰን የለውም።—መዝሙር 55:22

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ