የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 4/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • አፖሎጂስቶች—የክርስትና ጠበቆች ወይስ ፈላስፎች?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ምድሪቱን ጎብኙ፤ በጎቹን ጎብኙ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • “እውነትንና ሰላምን ውደዱ”!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 4/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡት የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ተግባራዊ ጥቅም ያላቸው ሆነው አግኝተሃቸዋልን? ከሆነ ለምን በሚከተሉት ጥያቄዎች የማስታወስ ችሎታህን አትፈትንም?

▫ ኢየሱስ ያከናወናቸው ፈውሶች ዋና ዓላማ ምን ነበር?

አርማጌዶንን የሚያልፉ ሰዎች ብዙም ሳይቆዩ ወዲያው እንደሚፈወሱ ያመለክታሉ። ይህም በዘመናችን የሚኖሩትን በግ መሰል እጅግ ብዙ ሰዎች ያጽናናቸዋል። (ኢሳይያስ 33:24፤ 35:5, 6)—12/15, ገጽ 12

▫ “በጸሎት ጽኑ” የሚለውን ምክር ዘወትር ማስታወስ የሚያስፈልገን ለምንድነው? (ሮሜ 12:12)

አንዳንድ የሕይወት ገጽታዎችና ኃላፊነቶች በኃይል ይጫኑንና መጸለይ እስከመርሳት ልንደርስ ስለምንችል በችግር ተሸንፈን ከመንግሥቱ ተስፋ የምናገኘውን ደስታ ልናጣና ጸሎት እስከማቆም ልንደርስ እንችላለን። ስለዚህ እንድንጸልይና በጸሎት አማካኝነት ወደ ይሖዋ የበለጠ እየቀረብን እንድንሄድ የሚያበረታታን ማሳሰቢያ ያስፈልገናል።—ታኅሣሥ 15, 91 ገጽ 14

▫ የኖህ ዘመን የውኃ መጥለቅለቅ በሰው ዘሮች ላይ የማይፋቅ ስሜት ፈጥሮ እንዳለፈ የሚያሳይ ምን ማረጋገጫ አለ?

ከ250 በሚበልጡ ጐሣዎችና ሕዝቦች የሚነገሩ ከ500 የሚበልጡ ስለ ውኃ መጥለቅለቅ የሚገልጹ አፈ ታሪኮች እንዳሉ ይገመታል። እነዚህ አፈ ታሪኮች በሙሉ የሚመሳሰሉባቸው አንዳንድ መሠረታዊ ነጥቦች አሉ።—ጥር 15, 92፣ ገጽ 5

▫ በጊዜአችን ያሉት የሐሰት ነቢያት በኤርምያስ ዘመን ከነበሩት ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው?

በዘመናችን ያሉት የሐሰት ነቢያት በውሸት አምላክን እንወክላለን ይላሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረው እርግጠኛ ነገር ይልቅ ሰዎች ከአምላክ ቃል የሚያርቀውን ነገር በመስበክ የአምላክን ቃል ይሰርቃሉ። በተለይ ለዚህ አድራጎታቸው ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ስለመንግሥቱ የሚሰጡት ትምህርት ነው። (ኤርምያስ 23:30)—የካቲት 1, 92፣ ገጽ 4

▫ አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቁ ምን ያመለክታል?

አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቁ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለመተባበርና መንፈሱ በይሖዋ ሕዝቦች መካከል የሚሠራውን ሥራ የሚከለክል ምንም ነገር ላለማድረግ እንደወሰነ ያመለክታል። ስለዚህ ከታማኝና ልባም ባሪያና ከጉባኤ ሽማግሌዎች ዝግጅት ጋር መተባበር ይኖርበታል። (ዕብራውያን 13:7, 17፤ 1 ጴጥሮስ 5:1-4)—የካቲት 1, 91, ገጽ 18

▫ የምስል አምልኮት አምላኪውን በጣም ሊያጎድፍ የሚችለው ለምንድን ነው?

ይሖዋ አምላክ ምስሎችን እንደሚጸየፍና ምስሎቹም የሚያመልኳቸውን ሰዎች ወደ አምላክ እንዲቀርቡ ለመርዳት እንደማይጠቅሙ መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል። (ዘዳግም 7:25፤ መዝሙር 115:4-8) ሰይጣን ዲያብሎስ የሰዎችን “ሐሳብ ስላሳወረ” የእውነት ብርሃን አይታያቸውም። (2 ቆሮንቶስ 4:4) ስለዚህ አንድ ሰው ምስሎችን እንደ ቅዱስ ነገር ቆጥሮ የሚያከብር ከሆነ በእርግጥም የአጋንንትን ፍላጎት ያገለግላል ማለት ነው። (1 ቆሮንቶስ 10:19, 20)—የካቲት 15, 92, ገጽ 6-7

▫ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን በጐች እንደ ውድ ንብረት ይቆጠሩ የነበረው ለምን ነበር?

ሱፋቸው ወይም ጸጉራቸው ሁልጊዜ የሚታደስ ሀብት ስለሆነ ለቤተሰብ የሚሆን ልብስ ሊሠራበት ወይም ለሽያጭ ሊቀርብ ይችል ነበር። የበጐች ቀንድ ኢዩቤልዩ መድረሱን ለማመልከት ወይም የማስጠንቀቂያ ድምጽ ለማሰማት ወይም የጦርነት እንቅስቃሴዎችን ለመምራት ይነፋ ነበር። በጐች እሥራኤላውያን ሊመገቧቸው ከሚችሉት ንጹሕ እንስሶች መሃል የሚቆጠሩ ስለነበሩ አስተማማኝ የምግብ ምንጭ ነበሩ። በተጨማሪም ለመጠጥ ወይም አይብ ለመሥራት የሚያገለግል ወተት ይሰጡ ነበር።—መጋቢት 1, 92 ገጽ 24-5

▫ የአምላክ ወዳጆች የአምላክ መንግሥት እንድትመጣ በሚጸልዩበት ጊዜ ምን መጠየቃቸው ነበር?

(ማቴዎስ 6:10) የአምላክ ሰማያዊ መንግሥት ሰላምና ዋስትና ያለው ሕይወት ለማምጣት የገቡትን ቃል ለመፈጸም ያልቻሉን ሰው ሠራሽ መንግሥታዊ ሥርዓቶች እንድታጠፋ መጠየቃቸው ነው። (ዳንኤል 2:44)—መጋቢት 15, 92 ገጽ 6

▫ አፖሎጂስቶች እነማን ነበሩ?

የስላሴን ትምህርት ደግፈዋልን? አፖሎጂስቶች በሁለተኛው መቶ ዘመን መጨረሻ ላይ ይኖሩ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች የሚያውቁን ክርስትና በሮም ዓለም ውስጥ መስፋፋት ከጀመረው ተጻራሪ ፍልስፍና ለመከላከል የተለያዩ ጽሑፎችን ጽፈዋል። ከእነርሱ መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ ስላሴን አላስተማሩም።—ሚያዝያ 1, 92 ገጽ 24-9

▫ ሉቃስ 1:62 የሚያመለክት እንደሚመስለው የመጥምቁ ዮሐንስ አባት የሆነው ዘካርያስ ደንቆሮና ዲዳ እንዲሆን ተደርጎ ነበርን?

ገብርኤል የተናገረው የዘካርያስ የንግግር ችሎታ እክል እንደሚደርስበት ነው እንጂ የመስማት ችሎታው እንደሚታወክ አይደለም። (ሉቃስ 1:18-20) ሉቃስ 1:64 “ያን ጊዜም አፉ (የዘካርያስ) ተከፈተ ምላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ” ይላል። እዚህ ላይ የመስማት ችሎታው በምንም መንገድ እክል ደርሶበት እንደነበር የሚጠቁም ሐሳብ እንደሌለ እናስተውል። በሉቃስ 1:62 የተገለጸው “ጥቅሻ” የሚያመለክተው የዘካርያስን ውሳኔ ለመጠየቅ የተደረገ የሰውነት እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል።—ሚያዝያ 1, 92 ገጽ 31

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ