የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 7/1 ገጽ 3-4
  • ተስፋ መቁረጥ የበዛው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተስፋ መቁረጥ የበዛው ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከጭንቀት ለመገላገል ሲባል የሚወሰደው የመጨረሻ እርምጃ
  • ተስፋ መቁረጥን የሚያሸንፈው ተስፋ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • የተስፋ መቁረጥን ስሜት መቋቋም የሚቻልበት መንገድ
    ንቁ!—2000
  • በቅርቡ ተስፋ መቁረጥ የሌለበት ዓለም ይመጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ለምን ሞቼ አልገላገልም?
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 7/1 ገጽ 3-4

ተስፋ መቁረጥ የበዛው ለምንድን ነው?

ምሥራቅ ጀርመን ተብላ ትጠራ በነበረችው አገር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች በ1989 የበርሊን ግንብ በፈረሰ ጊዜ የተሻለ ሕይወት የመኖር ተስፋቸው እውን የሆነ መስሎአቸው ነበር። ይሁን እንጂ ግንቡ ከፈረሰ በኋላ አንድ ዓመት እንኳን ሳይሞላቸው “ጨካኝ የሆነው የካፒታሊስት አገሮች የዲሞክራሲ ኑሮ በበርሊን ግንብ ይጠበቅ ከነበረው ኑሮአቸው የከፋ ሆኖ አገኙት።” ውጤቱስ ምን ሆነ? የጭንቀትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት በጣም ተስፋፋ።

በቤት ውስጥና በኅብረተሰቦች መካከል በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ሰዎች የተሻለ ኑሮ ለማግኘት ሲሉ አገራቸውን ትተው ለመሰደድ ይገደዳሉ። ሆኖም ያሰቡትን የሚያገኙት ጥቂቶች ብቻ ናቸው። እንዲያውም አንዳንዶች መኖሪያ ቤት አጥተው መንገድ አዳሪዎች ይሆናሉ። በአንዳንድ አገሮች ሊወጡ የማይችሉት የመንግሥት ሕግ ይደቀንባቸዋል። ሥራ ስለሌላቸው ቤት ለመከራየት አይችሉም። የመኖሪያ አድራሻ ስለሌላቸው ደግሞ ሥራ ተቀጥረው ሊሠሩ አይችሉም። መንግሥታዊ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እርዳታ ለመስጠት ይጥራሉ። ይሁን እንጂ ችግሩን ለማስወገድ በርካታ ጊዜ ይወስድባቸዋል። በዚህ ምክንያት ተስፋ መቁረጥና ጭንቀት እየበዛ ይሄዳል።

ብዙ ሴቶች ጭንቀት ውስጥ በመውደቃቸው አደገኛ እርምጃዎችን ወስደዋል “ሴቶችና ወንጀል በ1990” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ዶክተር ሱዛን ኤድዋርድስ ሲገልጹ “ወጣት ሴቶች በዝሙት አዳሪነት ሥራ ላይ የሚሠማሩት ራሳቸውን መግዛት የማይችሉ ስለሆኑ ወይም ጥሩ ቤተሰብ ስላልነበራቸው ሳይሆን የሚያጋጥማቸው የኢኮኖሚ ችግር ስለሚያስገድዳቸው ነው” ብለዋል። በተመሳሳይም ሥራ ለመፈለግ ሲሉ ቤታቸውን ለቀው የሚሄዱ ወጣት ወንዶች ምንም ዓይነት ሥራ ሳያገኙ ይቀሩና የእለት ጉርስና መጠለያ ለማግኘት ሲሉ ለግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች ገላቸውን እያከራዩ መኖር ይጀምራሉ ወይም ሙሉ በሙሉ በወንጀለኞች ቡድን ቁጥጥር ውስጥ ይወድቃሉ።

አስከፊ የፖለቲካ ሁኔታዎች፣ አመጽና የኑሮ ውድነትም ለጭንቀትና ለተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚሆኑ ችግሮች ናቸው። ከፍተኛ ትምህርት ያላቸው ሰዎች እንኳን ከዚህ ችግር ሊያመልጡ አልቻሉም። የኑሮ ውድነት እየናረ ሲሄድ የነበራቸውን ሻል ያለ የኑሮ ደረጃ ጠብቀው ለመኖር በጣም ከባድ ይሆንባቸዋል። ውጤቱስ? “ግፍ ጠቢቡን ያሳብደዋል” በማለት የጥንቱ ንጉሥ ሰለሞን እንደተናገረው ይሆናል።a (መክብብ 7:7) በእርግጥም ብዙ ሰዎች ራሳቸውን በመግደል ከችግራቸው የሚላቀቁበትን የመጨረሻ እርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው።

ከጭንቀት ለመገላገል ሲባል የሚወሰደው የመጨረሻ እርምጃ

ራሳቸውን የሚገድሉ ወጣቶች ቁጥር እየበዛ መሄዱ ወጣቶችም እንኳን ከዚህ ተስፋ የመቁረጥና የጭንቀት ቸነፈር ሊያመልጡ አለመቻላቸውን ያመለክታል። አንድ የብሪታንያ የዜና ዓምድ ፀሐፊ “በጊዜያችን የወጣቶች ጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ እየበዛ የሄደበት ምክንያት ምንድን ነው?” ሲሉ ጠይቀዋል። የሎንደን የሳይካትሪ ኢንስቲቲዩት ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ኤሪክ ቴይለር መርዝ ጠጥተው ራሳቸውን ለመግደል ሙከራ ካደረጉ በኋላ ወደ ሆስፒታል በተወሰዱ ከ8 እስከ 16 ዓመት የሚሆናቸው ወጣቶች ላይ ስለተደረገ ጥናት ሲዘግቡ፦ “አንደኛው አስደናቂ ነገር የጭንቀትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያደረባቸው ልጆች ቁጥር በጣም መብዛቱ ነው” ብለዋል። በብሪታንያ በየዓመቱ 100,000 የሚያክሉ ወጣቶች ከጭንቀት ለመገላገል ሲሉ መርዝ በመጠጣት ራሳቸውን የመግደል ሙከራ ያደርጋሉ። እነዚህ ሁሉ አፋጣኝ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የሚያሳውቁ ናቸው።

አንድ የብሪታኒያ በጎ አድራጊ ድርጅት ጭንቀትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያደረባቸውን ሰዎች ችግር ለማዳመጥና ለመርዳት አንድ ዘመቻ ጀምሮአል። በዚህ መንገድ የድርጅቱ ምክር ሰጪዎች “ከሞት የተሻለ አማራጭ” መኖሩን ልናስገነዝባቸው ችለናል ይላሉ። ሆኖም ሰዎች ተስፋ ቢስ እንዲሆን የሚያስገድዱአቸውን ችግሮች ለመፍታት እንዳልቻሉ ይናገራሉ።

ሳንደይ ኮረስፖንደንት የተባለው ጋዜጣ ራስን በራስ መግደል እየተስፋፋ መሄዱ የሚያመለክተው “የብቸኝነት ኑሮና የኅብረተሰብ መራራቅ በጣም እየተባባሰ መሄዱን ነው” ብሎአል። በጊዜያችን ራስን በራስ ማጥፋት የበዛው ለምንድን ነው? ጋዜጣው ምክንያቶቹን ሲጠቅስ “የቤት እጦት፣ የአልኮል መጠጥ ጠጪዎች መጨመር፣ የኤይድስ በሽታ እና የአእምሮ ሆስፒታሎች መዘጋት ነው” ብሏል። ሰዎች ይህን የመሰለ እርምጃ እንዲወስዱ የሚያደርጋቸው አንዱ ምክንያት ለችግሮች መፍትሔ የሚያስገኝላቸው ብቸኛው መንገድ ራሳቸውን መግደል እንደሆነ አድርገው ስለሚገምቱ ነው።

ተስፋ የመቁረጥን ስሜት ለማስወገድ የሚቻልበት ተስፋ አለን? አዎ፣ ኢየሱስ “አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሱ” በማለት ተናግሮአል። (ሉቃስ 21:28) ኢየሱስ ምን ማለቱ ነበር? ምን ዓይነት ተስፋስ ሊኖር ይችላል?

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በሃሪስ አርከርና በዋልትከ የተዘጋጀው ዘ ቲዎሎጅካል ወርድቡክ ኦፍ ዘ ኦልድ ተስታመንት እንደሚለው “ግፍ” ተብሎ የተተረጎመው የጥንቱ ቃል “መጫንን፣ መርገጥን፣ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ማድቀቅን ያመለክታል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ