ወደፊት በምትኖረው ንጹሕ ምድር ተደሰት!
የሥርዓትና የንጽሕና አምላክ የሆነው ይሖዋ መላዋን ምድር ገነት ለማድረግ የነበረውን የመጀመሪያ ዓላማ ወደፊት የሚፈጽመው በመሆኑ ምን ያህል ልንደሰት እንችላለን! (ኢሳይያስ 11:6–9) “ከአፌ የሚወጣ ቃሌ . . . የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም” በማለት ቃል ገብቷል። ‘አምላክ ሊዋሽ አይችልም።’ ስለዚህ እነዚህ ቃላት ትርጉም የለሽ ቃላት አይደሉም። — ኢሳይያስ 55:11፤ ዕብራውያን 6:18
ሰዎች መመለሻ እስከማይገኝለት ነጥብ ድረስ ከመሄዳቸውና ጠቅላላው ኢኮሎጂካል (ሥነ ምሕዳራዊ) ውድቀት ሊከላከሉት የማይቻል እስከሚሆን ድረስ ሳይጠብቅ ይሖዋ ጣልቃ በመግባት ፍቅራዊ እርምጃ እንደሚወስድ በማወቃችን እፎይ ልንል እንችላለን! — ራእይ 11:18
ይሖዋ ሆን ብለው ብክለት የሚያደርሱትንና በሥርዓትና በንጽሕና መሠረታዊ ሥርዓቶቹ ላይ በማመፅ ቸል የሚሉትን ንሥሐ የማይገቡ ሰዎች ያስወግዳቸዋል። እንደገና የተቋቋመችውን ገነት ማንም ሰው አደጋ ላይ እንዲጥል አይፈቀድለትም። — ምሳሌ 2:20–22
የአምላክ መንግሥት በምትገዛበት ወቅት በክርስቶስ ኢየሱስ አመራር ሰዎች ለአካላዊ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ ማናቸውንም ርዝራዦች እንዴት ነቅለው ማውጣት እንደሚችሉ ይማራሉ። ታይቶ ለማያውቀው ዓለም አቀፋዊ የጽዳት ዘመቻ በግልም ሆነ በጥቅል ተሳትፎ የማድረግ ግዴታ የሚኖረው ዛሬ ሳይሆን በዚያን ጊዜ ነው። — ከሕዝቅኤል 39:8–16 ጋር አወዳድር።
አሁን ያለው ክፉ የነገሮች ሥርዓት ሲጠፋ ከዚያ ዕልቂት የሚተርፉት ሰዎች ይህንን አካላዊ የጽዳት ፕሮግራም የሚደግፉት በዛሬው ጊዜ ባለው መንፈሳዊ የጽዳት ዘመቻ ሲካፈሉ በሚያሳዩት ከፍተኛ የሥራ ፍቅርና የጋለ ስሜት ነው። — መዝሙር 110:3 አዓት
በአምላክ መንግሥት አማካኝነት የሚፈጸመውን ታይቶ የማይታወቅና ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ታላቅ የሆነውን የጽዳት ዘመቻ ተከትሎ ንጹሕ የሆነች ምድር እንደምትመጣ የተረጋገጠ ነው። ምንም ዓይነት የብክለት ርዝራዥ አይኖርም። በግድግዳዎች ላይ የተጻፉ ወይም የተለጠፉ ምንም ዓይነት ጽሑፎች በየትም ቦታ አይኖሩም። የተጣሉ ጠርሙሶች፣ ቆርቆሮዎች፣ ፕላስቲክ የዕቃ መያዣዎች፣ የማስቲካ ወይም የከረሜላ መጠቅለያዎች፣ ጋዜጣዎችና መጽሔቶች የትኛውንም የባሕር ዳርቻ ወይም ገነታዊ ቦታ አያቆሽሹም።
ወደፊት በምትኖረው ንጹሕ ምድር ተደሰት!
[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ወደፊት በሚደረገው ዓለም አቀፋዊ የጽዳት ዘመቻ ተሳታፊ ትሆናለህን?