የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 9/15 ገጽ 30-31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዕዳ በሚኖርባችሁ ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የገንዘብ ችግርና ዕዳ​—መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳህ ይችላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ዕዳ መግባት ያዋጣልን?
    ንቁ!—1995
  • ለመሰል ክርስቲያኖች ገነዘብ ማበደር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 9/15 ገጽ 30-31

የአንባብያን ጥያቄዎች

አስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ባለበት በዚህ ጊዜ ከዕለት ወደ ዕለት ብዙ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ከስረናል ብለው በማስታወቅ ላይ ናቸው። ታዲያ አንድ ክርስቲያን ከስሬአለሁ ብሎ ቢያስታውቅ ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ ይኖረዋልን?

ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ የአምላክ ቃል በዘመናችን ብቻ ላሉ አንዳንድ ሁኔታዎች እንዴት ጠቃሚ መመሪያዎች እንደሚሰጠን የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። ብዙ አገሮች ኪሳራ ማስታወቅን የሚቆጣጠሩ ሕጎች አሏቸው። ሕጎቹ ከአገር ወደ አገር ይለያያሉ፤ ይህን በተመለከተ ሕጋዊ ምክር መስጠት የክርስቲያን ጉባኤ ኃላፊነት አይደለም። ሆኖም የአንዳንድ አገሮች ሕግ ኪሳራ በማስታወቅ ረገድ የሚሰጣቸውን አጠቃላይ መብቶችና ግዴታዎች እንመልከት።

ግለሰቦችም ሆኑ የንግድ ድርጅቶች ከስረናል ብለው እንዲያስታውቁ መንግሥታት የሚፈቅዱበት አንዱ ምክንያት አበዳሪዎችን ተበዳሪዎቻቸው የወሰዱትን ዕዳ ለመክፈል ባለመቻላቸው ምክንያት ከሚደርስባቸው ኪሳራ በመጠኑም ቢሆን ለማዳን ነው። አበዳሪዎች ሊያደርጉ የሚችሉት ብቸኛ አማራጭ ለፍርድ ቤት አመልክተው ተበዳሪው መክሰሩን እንዲያስታውቅ ማድረግና የተበዳሪው ንብረት ተሸጦ ለአበዳሪዎቹ እንዲከፋፈል ማድረግ ሊሆን ይችላል።

ኪሳራ የማስታወቅ ሕግ የሚያገለግልበት ሌላው መንገድ የሚፈለግበትን ዕዳ መክፈል ላልቻለ ተበዳሪ ከለላ መስጠት ነው። ተበዳሪው መክሰሩን እንዲያስታውቅና አንዳንድ ንብረቶችን ለአበዳሪዎች እንዲከፍል ሊፈቀድ ይችላል። ቢሆንም ተበዳሪው ቤቱ ወይም አነስተኛ የሆኑ ቁሳቁሶቹ እንዳይወሰዱበት ሕጉ ሊፈቅድለት ይችላል። በዚህም አበዳሪዎቼ ድንገት ንብረቴን በሙሉ ይወስዱብኝ ይሆናል ከሚለው የዘወትር ስጋት ተላቆ ኑሮውን ሊቀጥል ይችላል።

እንግዲያው ይህ ሕግ በገንዘብም ሆነ በዕቃዎች ልውውጥ ለሁለቱም ወገን የተወሰነ ከለላ ለመስጠት ታቅዶ የወጣ እንደሆነ ግልጽ ነው። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ጠቃሚ ምክር እንመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስን ከዳር እስከ ዳር ያነበበ ማንኛውም ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ብድር ውስጥ መግባትን እንደማያበረታታ መረዳት አያስቸግረውም። “ባለጠጋ ድሆችን ይገዛል፣ ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው” የሚለውን በምሳሌ 22:7 ላይ የሚገኘውን የሚመስሉ ማስጠንቀቂያዎች እናገኛለን።

በተጨማሪም ኢየሱስ ብዙ ዕዳ ያለበትን ባሪያ አስመልክቶ በማቴዎስ 18:23–34 ላይ የሰጠውን ምሳሌም አስታውሱ። “እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።” ሆኖም ጌታው ማለትም ንጉሡ አዘነለትና ማረው። በኋላም ይህ ባሪያ ምሕረት ሳያሳይ በመቅረቱ ‘ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለወኅኒ አሳልፎ ሰጠው።’ ስለዚህ ገንዘብ ከመበደር መቆጠብ ከሁሉ የተሻለና የሚደገፍ ነገር ነው።

ጥንት በእስራኤል የነበሩ የአምላክ አገልጋዮች አንዳንድ የንግድ ልውውጦችን ያደርጉ ነበር። በዚህም ምክንያት መበደርና ማበደር የተለመደ ነገር ነበር። ታዲያ ይሖዋ ይህን በተመለከተ ምን እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር? አንድ ሰው ንግድ ለመጀመር ወይም ንግዱን ለማስፋት ገንዘብ መበደር ከፈለገ አበዳሪው የሆነው ዕብራዊ ወለድ መጠየቁ ሕጋዊና የተለመደ ነበር። ይሁን እንጂ አምላክ ሕዝቦቹ ለአንድ ለተቸገረ እስራኤላዊ በሚያበድሩበት ጊዜ ራስ ወዳዶች እንዳይሆኑ አጥብቆ አሳስቧቸዋል። ወለድ በመጠየቅ ሰውዬው ከደረሰበት ችግር ትርፍ ማግኘት የለባቸውም ነበር። (ዘጸአት 22:25) ዘዳግም 15:7, 8 እንዲህ ይላል፦ “አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢደኸይ፣ . . . በድሀው ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ። ነገር ግን እጅህን ለእርሱ ክፈት፣ የለመነህንም አስፈላጊውን ነገር አበድረው።”

አበዳሪዎች የተበዳሪውን የዕለት መተዳደሪያ እንዳይወስዱበት የሚከለክለው ሕግም ቢሆን ተመሳሳይ የሆነ ደግነት ወይም አሳቢነት የሚያንጸባርቅ ነው። አበዳሪው የቤተሰቡን ወፍጮ ወይም ሰውዬው ብርድ የሚከላከልበትን የሌሊት ልብሱን እንዳይወስድ ይከለክል ነበር።—ዘዳግም 24:6, 10–13፤ ሕዝቅኤል 18:5–9

እርግጥ ነው፣ እነዚህን ከታላቁ ፈራጃቸውና ሕግ ሰጪአቸው የተሰጧቸውን ፍቅራዊ ሕጎች ተቀብለው በሥራ ላይ ያዋሉት ሁሉም አይሁዶች አልነበሩም። (ኢሳይያስ 33:22) አንዳንድ ስግብግብ አይሁዶች ወንድሞቻቸውን በጭካኔ አንገላተዋቸዋል። ዛሬም አንዳንድ አበዳሪዎች ባጋጠሙት አንዳንድ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች የተነሣ ዕዳውን ለመክፈል ላልቻለ ቅን ክርስቲያን እንኳ ሳይቀር ጨካኞችና ምክንያታዊ ያልሆነ ነገር እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ሊሆኑ ይችላሉ። (መክብብ 9:11) እንዲህ ያለው ተበዳሪ ዓለማዊ አበዳሪዎች ሐሳበ ግትሮችና ስግብግቦች በመሆን የሚያሳድሩበትን ጫና ለመከላከል ሕጋዊ ከለላ ለመፈለግ ሊገደድ ይችላል። ይህን ከለላ እንዴት ያገኛል? በአንዳንድ ሁኔታዎች ተበዳሪው ሊወስደው የሚችለው አበዳሪዎች የሚቀበሉት ሕጋዊ እርምጃ ከስሬአለሁ ብሎ ማስታወቅ ብቻ ይሆናል። ስለዚህ ያለበትን ዕዳ በመክፈል ረገድ ስግብግብ ወይም ቸልተኛ ያልሆነ አንድ ክርስቲያን ሕጋዊ ከለላ ለማግኘት ሲል በአንዳንድ አገሮች ባለው ሕግ መሠረት መክሰሩን ለማስታወቅ ይገደድ ይሆናል።

ሆኖም የጉዳዩን ሌላ ገጽታ ማገናዘብ ይኖርብናል። አንድ ክርስቲያን ዕዳ ውስጥ የገባው ገንዘቡን ለምን ወይም ምን ያህል በማውጣት ረገድ ራሱን ባለመግዛቱ ወይም ንግዱን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ሲያደርግ አርቆ ተመልካች ባለመሆኑ ሊሆን ይችላል። ታዲያ የገባበትን ዕዳ በግዴለሽነት በመመልከት መክሰሩን አስታውቆ ከዕዳው ለመገላገል መፈለግና በእርሱ ደካማ የማመዛዘን ችሎታ ምክንያት ሌሎችን መጉዳት ይኖርበታልን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ዓይነቱን ጥንቃቄ የጎደለው የገንዘብ አያያዝ አይደግፍም። የአምላክ አገልጋይ ቃሉ አዎን አዎን እንዲሆን አጥብቆ ያሳስባል። (ማቴዎስ 5:37) በተጨማሪም ኢየሱስ ግንብ ለመገንባት ከመጀመር በፊት የሚፈጀውን ወጪ ስለማስላት የተናገረውን አስታውሱ። (ሉቃስ 14:28–30) ከዚህ ጋር በሚስማማ መንገድ አንድ ክርስቲያን የገንዘብ ዕዳ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሊከተሉ የሚችሉትን አንዳንድ የማይፈለጉ ሁኔታዎች አውጥቶ አውርዶ ሊያስብባቸው ይገባል። አንዴ ባለዕዳ ከሆነ በኋላ ግን ላበደረው ግለሰብ ወይም ድርጅት መልሶ የመክፈል ኃላፊነት እንዳለበት ማወቅ ይኖርበታል። አንድ ክርስቲያን ብዙ ሰዎች ግዴለሽና ትምክህት የማይጣልበት እንደሆነ አድርገው ከተመለከቱት ሲጥርለት የነበረውን መልካም ስሙን ሊያጎድፍና በውጭ ካሉ ሰዎች ጥሩ ምሥክርነትን ሳያገኝ ሊቀር ይችላል።—1 ጢሞቴዎስ 3:2, 7

መዝሙር 15:4 [አዓት] ይሖዋ ስለሚቀበላቸው ሰዎች የሚናገረውን አስታውሱ። “[አምላክ የሚቀበለው ሰው] ምንም ያህል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል የሚፈጽም ነው” ይላል። አዎን፣ ክርስቲያኖች ለእነሱ እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትን ለአበዳሪዎቻቸውም እንዲሁ እንዲያደርጉ አምላክ ይጠብቅባቸዋል።—ማቴዎስ 7:12

ስለዚህ ነገሩን ለማጠቃለል መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ክርስቲያን ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥመው ኪሳራ ስለማሳወቅ ቄሳር ባወጣው ሕግ ተጠቅሞ ሕጋዊ ከለላ ማግኘት አይችልም ብሎ አይደመድምም። ይሁን እንጂ ሐቀኝነትንና ታማኝነትን በተመለከተ ክርስቲያኖች ተለይተው የሚታወቁ መሆን አለባቸው። ስለዚህ የገቡትን የገንዘብ ግዴታ ለመፈጸም ባላቸው ጥልቅ ፍላጎት ረገድ ጥሩ ምሳሌ መሆን አለባቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ