የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 4/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ አንብበን እንድንረዳው ተብሎ የተጻፈ መጽሐፍ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • አምላክን መስማት የምንችለው እንዴት ነው?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • መጽሐፍ ቅዱስን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ያለው አደጋ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ከአምላክ ቃል ተማር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 4/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ይቻላል?

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው። አፍቃሪ ከሆነ አባት የተላከ ደብዳቤ ነው ማለት ይቻላል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) አምላክ እሱን እንዴት ማስደሰት እንደምንችል፣ ክፋት እንዲኖር ለምን እንደፈቀደ እንዲሁም ወደፊት ለሰው ልጆች ምን እንደሚያደርግ በቃሉ ላይ ገልጿል። ይሁንና የሃይማኖት አስተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት አዛብተዋል፤ በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ጨርሶ መረዳት እንደማይቻል ይሰማቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 20:29, 30

ይሖዋ አምላክ ስለ እሱ እውነቱን እንድናውቅ ይፈልጋል። በመሆኑም ልንረዳው የምንችል መጽሐፍ ሰጥቶናል።—1 ጢሞቴዎስ 2:3, 4⁠ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የምትችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ፣ መጽሐፍ ቅዱስን መስጠት ብቻ ሳይሆን ይህን መጽሐፍ መረዳት የምንችልበት ዝግጅትም አድርጎልናል። ቃሉን እንዲያስተምረን ኢየሱስን ወደ ምድር ልኮታል። (ሉቃስ 4:16-21) ኢየሱስ የተለያዩ ጥቅሶችን በመጥቀስ አድማጮቹ የቅዱሳን መጻሕፍትን ሐሳብ እንዲረዱ አስችሏቸዋል።—ሉቃስ 24:27, 32, 45⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ፣ እሱ የጀመረው ሥራ እንዲቀጥል ለማድረግ የክርስቲያን ጉባኤን አቋቁሟል። (ማቴዎስ 28:19, 20) በዛሬው ጊዜም የኢየሱስ እውነተኛ ተከታዮች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ የሚያስተምረውን ትምህርት እንዲያውቁ ሰዎችን ይረዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የምትፈልግ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው።—የሐዋርያት ሥራ 8:30, 31⁠ን አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ