ለቅን ሰዎች የሚሆን ምሥራች
1 የምንኖረው ጥፋት እያንዣበበ ባለበት ጊዜ ውስጥ ነው። (ሕዝ. 9:5, 6) በየትም ቦታ የሚኖሩ ቅን ሰዎች ከሚመጣው ጥፋት ለመዳን ዝግጁ እንዲሆኑ መንገር በጣም አጣዳፊ ሥራ ነው። ይሖዋ በፍቅራዊ ደግነቱ ሕዝቦቹ “ለቅን ሰዎች ምሥራች እንዲሰብኩ” አዟቸዋል። (ኢሳ. 61:1, 2 አዓት) መጽሔቶቻችን ይህን ምሥራች በርቀትና በስፋት እንድናውጅ ይረ ዱናል።
2 መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የሚያጠነክረንንና ለሥራ የሚያነሳሳንን ጠንካራ መንፈሳዊ ምግብ ያቀርቡልናል። መጠበቂያ ግንብ የአምላክ መንግሥት በቅርብ ጊዜ ምድርን ወደ ገነት እንደምትቀይር በሚናገረው ምሥራች ቅን ሰዎችን ያጽናናል። ንቁ! መጽሔት ደግሞ ፈጣሪ ሰላምና ደህንነት የሰፈነበት አዲስ ዓለም እንደሚያመጣ በገባው ተስፋ ላይ እምነት ይገነባል። ምሥራቹ ለቅን ሰዎች እንዲደርስ ከሚረዱ ፈጣን መንገዶች አንዱ እነዚህን መጽሔቶች በሰፊው ማሰራጨት ነው። በቅርቡ ከወጡት እትሞች ለመነጋገሪያ የሚሆኑ ምን ነጥቦችን ጎላ ለማድረግ እንችላለን?
3 “በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ መጠቀም” የሚለውን ርዕስ በማሳየትና እንዲህ ብለህ በመጠየቅ የግንቦት 1 “መጠበቂያ ግንብ” ለማበርከት ትችላለህ:-
◼ በጣም አስፈላጊ የሆነ አንድ ጥያቄ አንስተን ለመወያየት መጥተናል። “መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ምን ጥቅም ልናገኝ እንችላለን ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ በሮሜ 15:4 ላይ የዚህን ጥያቄ መልስ እንድናገኝ ይረዳናል። [ሮሜ 15:4ን አንብብ።] በአካባቢያችን የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ አላቸው። ይሁን እንጂ ጊዜ ወስደው ዘወትር የሚያነቡት ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው። ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብቸኛ የተረጋገጠ ተስፋ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሆነ እናምናለን። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ብናነብ እንጠቀማለን።” ተስማሚ የሆኑ ተጨማሪ ሐሳቦችን አክልና መጽሔቱን አበርክት ወይም ኮንትራት እንዲገቡ ጋብዝ።
4 የግንቦት 15 “መጠበቂያ ግንብ” “የቀድሞ አባቶቻችን የሚያገኙት አዲስ ሕይወት” የሚል ማራኪ ርዕስ አለው። በዚህ መግቢያ አማካኝነት ፍላጎት መቀስቀስ ትችል ይሆናል:-
◼ “ብዙ ሰዎች አያቶቻቸው ምን ይመስሉ እንደነበር የማወቅ ጉጉት አላቸው። አንዴ ስለሞቱና እንደገና ልናገኛቸው ስለማንችል ከእነርሱ ጋር የመተዋወቅ አጋጣሚ አይኖረንም ብለው ይደመድማሉ። ከቀድሞ አያቶቻችን ጋር ተገናኝተን ልንተዋወቅ የምንችልበት አጋጣሚ አለ ብለው ያስባሉ?” መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብና አምላክ በገነቲቱ ምድር ላይ አዲስ ሕይወት እንደሚሰጣቸው ስለገባው ቃል አብራራ።
5 ሰዎች ለመስማት ፈቃደኛ በማይሆኑበት ጊዜ “ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት” በሚለው ትራክት አማካኝነት የሚከተለውን ቀላል አቀራረብ መጠቀም ትችል ይሆናል:-
◼ “ምን ዓይነት ተስፋ እንዳለዎት ባላውቅም (በትራክቱ ላይ ወዳለው ሥዕል እያመለከትክ) እኔ ግን እንዲህ ባለ መከራ በሌለበትና ሰላም በሰፈነበት ዓለም ውስጥ ለመኖር ተስፋ አለኝ።”
◼ ሌላው የአቀራረብ መንገድ እንዲህ ሊሆን ይችላል:- “በዚህ ሥዕል ላይ እንዳለው በመሰለ ገነት ውስጥ እንዲኖሩ ግብዣ ቢቀርብልዎት እንዲህ ያለውን ግብዣ እምቢ ይላሉን?” (በሌላ ጽሑፍ ላይ የሚገኝ ሌላ የገነት ሥዕል ልትጠቀም ትችላለህ።)
6 ከግንቦት 14 በፊት መጽሔት በማበርከት ሥራ የምትካፈል ከሆነ የመንግሥት ዜና ቁ. 34 ቅጂዎችን መያዝ አትዘንጋ። አሁንም አንድ ቅጂ ያልደረሰው ሰው ካገኘህ ልታበረክትለት ትችላለህ። ከቤተሰቡ አባሎች መካከል አንዱ ወይም እነርሱን ለመጠየቅ የሚመጡ ዘመዶች ሊያነቡት እንደሚችሉ በመገንዘብ ጽሑፎቻችንን ለማሰራጨት ሁልጊዜ ዝግጁዎች እንሁን። (1 ጢሞ. 6:18) ቅን ለሆኑ ሰዎች የምንወስደው ምሥራች ሕይወታቸውን ሊያድንላቸው ይችላል።— 1 ጢሞ. 4:16