የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/95 ገጽ 2
  • ደስተኛ ወላጆች!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ደስተኛ ወላጆች!
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወጣቶች ሆይ፣ የይሖዋን ልብ አስደስቱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ለልጆቻችሁ ምን ዓይነት ግቦች አውጥታችሁላቸዋል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ልጆቻችሁ የምሥራቹ አገልጋዮች እንዲሆኑ አሠልጥኗቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • በመንፈሳዊ ጠንካራ የሆነ ቤተሰብ መገንባት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 8/95 ገጽ 2

ደስተኛ ወላጆች!

1 በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ የምትኖር ወጣት ከሆንክ ወላጆችህን ማስደሰት የምትችልበት አንድ ልዩ መንገድ አለ። የጽድቅ አካሄድ የምትከተል ከሆነ ‘አባትህና እናትህ ይደሰታሉ።’ (ምሳሌ 23:22–25) ወላጆችህ ጥሩ ጥሩውን እንደሚመኙልህ የታወቀ ነው። እውነትን የራስህ ስታደርግና ሕይወትህን ለይሖዋ ስትወስን ከማየት የበለጠ ሊያስደስታቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።

2 በእውነት ውስጥ የሚገኙ ወላጆች ስላሉህ አመስጋኝ ልትሆን ትችላለህ። ከተወለድክ ጊዜ ጀምሮ መግበውሃል፣ አልብሰውሃል፣ መኖሪያ ሰጥተውሃል እንዲሁም በታመምክባቸው ጊዜያት ተንከባክበውሃል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ስለ ይሖዋና ስለ ጽድቅ ጎዳናዎቹ በትጋት አስተምረውሃል፤ ይህ ደግሞ የዘላለም ሕይወት እንድታገኝ የሚያስችልህ ማሰልጠኛ ነው። (ኤፌ. 6:1–4) አድናቆትህን እንዴት ልታሳይ ትችላላህ?

3 እውነትን የራስህ አድርግ፦ ወላጆችህ እውነትን በቁም ነገር እንድትይዘው፣ መንፈሳዊ እድገት እንድታደርግና ከይሖዋ ድርጅት ጋር ተጣብቀህ እንድትቀጥል በትጋት አስተምረውሃል። ማንም ሳያስገድድህ በቤተሰቡ ጥናት ላይ በመካፈል አድናቆት ማሳየት ትችላለህ። ቤተሰቡ ልክ በሰዓቱ መድረስ እንዲችል በራስህ አነሳሽነት ወደ ስብሰባ ለመሄድ በመዘጋጀት በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ያለህን ፍላጎት አሳይ። ስብሰባዎቹ ሲካሄዱ ከወላጆችህ ጋር ተቀመጥ፤ እንዲሁም የሚጠኑትን ጽሑፎች በትኩረት ተከታተል። ሐሳብ በመስጠት ለመሳተፍ ጥረት አድርግ። ክፍሎችን በመውሰድና በጥሩ ሁኔታ በመዘጋጀት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ታዛዥ ተማሪ እንደሆንክ አሳይ። በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ የአንተን እገዛ በሚጠይቁ ሥራዎች ለመካፈል ፈቃደኛ ሁን። እነዚህን በመሳሰሉ ሥራዎች መካፈልህ ልብህ ለመንፈሳዊነትህ ጠቃሚ በሆኑ ነገሮች ላይ እንዳተኮረ እንዲቀጥል ያስችልሃል።

4 በየጊዜው እድገት ማድረግ የሚያስችሉህን ግቦች አውጣ፦ አስፋፊ ለመሆን ያለህን ፍላጎት በማሳየት በመስክ አገልግሎት ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማድረግ ተጣጣር። ከሳምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጋር እኩል ተራመድ ወይም በይበልጥ እንደትጠቀም ጠቅላላውን መጽሐፍ ቅዱስ በግልህ አንብበው። ራስን ለመወሰንና ለመጠመቅ የሚያስፈልጉ ብቃቶችን ለማሟላት ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። ወላጆችህ በይሖዋ አገልግሎት ሙሉ ተሳትፎ እንዲኖርህ የሚያስችል ሥልጠና የምታገኝበትን መንገድ በአእምሯቸው በመያዝ ወደፊት የምትከታተለውን ትምህርት በጥንቃቄ እንድትመርጥ ሊረዱህ ይችላሉ። ሌሎች ሰዎች እንደ አቅኚነት ወይም የቤቴል አገልግሎት ላሉት ልዩ መብቶች ብቁ እንደሆንክ እንዲመሰክሩልህ የሚያደርግ መልካም ስም በማፍራት ላይ አተኩር። (ሥራ 16:1, 2) አንዳንድ ግቦች ላይ መድረስህ ‘የተሻለውን ነገር መርምረህ በማወቅ በጽድቅ ፍሬ እንድትሞላ’ ሊያደርግህ ይችላል።— ፊልጵ. 1:10, 11

5 ወጣትነት የመማሪያ፣ ተሞክሮ የመሰብሰቢያና ከሌሎች ጋር አብሮ የመኖር ችሎታችንን የምናዳብርበት ጊዜ ነው። ከዕድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጫናዎችና ኃላፊነቶች ሳይኖሩብህ ተደስተህ መኖር የምትችልበት ጊዜ ነው። ሰሎሞን “አንተ ጎበዝ፣ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፣ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው” ብሏል። (መክ. 11:9) በወጣትነትህ ይሖዋን ለማገልገል ቁርጥ ውሳኔ ካደረግህ ዘላቂ የሆኑ በረከቶችን ታጭዳለህ።— 1 ዜና 28:9

6 “ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት” ይልቅ ‘ጽድቅን የምትከተል’ ከሆነ ወላጆችህን ከከባድ የጭንቀትና የሐዘን ሸክም ታሳርፋቸዋለህ። (2 ጢሞ. 2:22) የራስህንም ልብ ታስደስታለህ። (ምሳሌ 12:25) ከሁሉ በላይ ደግሞ ፈጣሪህ የሆነውን ይሖዋ አምላክን ታስደስተዋለህ።— ምሳሌ 27:11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ