ትክክለኛ ዝንባሌ ያላቸውን ሰዎች ፈልጉ
1 የስብከቱ ሥራ አንዱ ዓላማ “ለዘላለም ሕይወት ትክክለኛ ዝንባሌ ያላቸውን” ሰዎች ማግኘት ነው። (ሥራ 13:48 አዓት) ወቅታዊ መጽሔቶቻችን የመንግሥቱን ተስፋ ለሰዎች ስለሚያስታውቁ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የተባሉትን መጽሔቶች ማሰራጨቱ ይህንን ሥራ ለማከናወን የሚያስችሉ ግሩም መንገዶች ሆነው ተገኝተዋል። በሚያዝያ ወር መጽሔቶችን እናበረክታለን። ሰዎች ፍላጎት ሲያሳዩ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም ለዘላለም መኖር በተባሉት መጽሐፎች አለዚያም በደስታ ኑር! በተባለው ብሮሹር አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እናስጀምራለን ብለን ተስፋ እናደርጋልን። ከዚህ በታች የሰፈሩት አቀራረቦች ሊጠቅሙህ ይችላሉ:-
2 የሚያዝያ 1ን “መጠበቂያ ግንብ” ስትጠቀም ባለፈው ዓመት የአውራጃ ስብሰባ በቀረበው የሕዝብ ንግግር ላይ የሚያተኩረውን “የዘላለሙን ንጉሥ አወድሱ!” የሚለውን ርዕስ በማሳየት እንዲህ ማለት ትችላለህ:-
◼ “ብዙዎቹ የምናነጋግራቸው ሰዎች በአምላክ ያምናሉ። ሌሎቹ ደግሞ በአምላክ ማመን አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አንድ አምላክ መኖር እንዳለበት የሚያረጋግጡ ተጨባጭ ማስረጃዎች በአካባቢያችን ሞልተዋል። [መዝሙር 104:24ን አንብብ።] አንድ ካሜራ ወይም ኮምፒዩተር ስንመለከት ያለማመንታት አንድ የማሰብ ችሎታ ያለው ንድፍ አውጪ ሠርቶታል ብለን እናምናለን። ታዲያ ከዚህ ይበልጥ በጣም ውስብስብ የሆኑ እንደ ምድርና ሰው የመሳሰሉት በአጋጣሚ ተገኙ ብሎ ማሰቡ ምክንያታዊ ነው?” በርዕሱ ውስጥ በሚገኝ አንድ አንቀጽ ተጠቅመህ በአምላክ የምናምነው ለምን እንደሆነ አሳማኝ ምክንያቶች አቅርብ። ከዚያም የሚበረከቱ ሁለት መጽሔቶች አሳየው።
3 የሚያዝያ 15 “መጠበቂያ ግንብ” “አምላክ እውነተኛውን አምልኮ የሚባርክበት ምክንያት” የሚል ርዕስ አለው። ይህንን ርዕስ ከማስተዋወቅህ በፊት እንዲህ ብለህ መጠየቅ ትችላለህ:-
◼ “በዓለም ላይ ያሉትን እነዚህን ሁሉ ሃይማኖቶች አምላክ የሚቀበላቸው ይመስልዎታል? [ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አብዛኞቹ ሃይማኖታዊ ሰዎች አምላክ ይቀበለናል ቢሉም የአምላክን ፈቃድ የማያደርጉ ሰዎችን አምላክ እንደማይቀበላቸው ኢየሱስ ተንብዮአል። [ማቴዎስ 7:21-23ን አንብብ።] ኢየሱስ ያስተማረውን እውነተኛ ሃይማኖት ለይተን ማወቃችን አስፈላጊ ነው።” በገጽ 16 ላይ የሚጀምረውን “እውነተኛው ሃይማኖት ምን ዓይነት ፍሬ ማፍራት አለበት?” የሚለውን ንዑስ ርዕስ አውጣና ነጥቡን ለማስረዳት አንድ ምሳሌ ጥቀስ።
4 “ጦርነት የማይኖርበት ጊዜ” የሚለውን ከሚያዝያ— ሰኔ ንቁ! ላይ የሚገኘውን ዋና ርዕስ ስታስተዋውቅ እንዲህ ማለት ትችላለህ:-
◼ “በዚህ መቶ ዘመን ሁለቱን የዓለም ጦርነቶች ጨምሮ በመቶ የሚቆጠሩ ጦርነቶች ተደርገዋል። ሆኖም ሁሉም የዓለም መሪዎች ሰላም እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። እኔ የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ፍላጎታቸው ይኸው ነው። ታዲያ ሁሉም ሰው ሰላም የሚፈልግ ከሆነ ሰላም ያልተገኘው ለምንድን ነው? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በምድር ላይ እውነተኛ ሰላም እንዲሰፍን ምን የሚያስፈልገን ይመስልዎታል?” የምታነጋግረው ሰው ሐሳቡን ከገለጸ በኋላ ገጽ 8, 9 አውጣና እንደ መዝሙር 46:8, 9 ያሉ ጥቅሶችን አንብብ። መጽሔቱ ላይ ያሉትን ሥዕሎችና ጥቅሶች በመጠቀም የአምላክ መንግሥት በመላው ዓለም ዘላቂ የሆነ ሰላም የሚያመጣው እንዴት እንደሆነ አሳየው። ከዚያም የሚበረከቱ ሁለት መጽሔቶች አሳየውና ለተመላልሶ መጠየቅ ቀጠሮ ያዝ።
5 ሥራ በዝቶብኛል የሚሉ ሰዎች ካጋጠሙህ የሚከተለውን አቀራረብ መሞከር ትችላለህ:-
◼ “ሥራ የሚበዛባቸውና ለመንፈሳዊነታቸው ጊዜ የሌላቸውን ሰዎች መርዳት እንፈልጋለን። መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የተባሉት ወቅታዊ መጽሔቶቻችን እርስዎንና ቤተሰብዎን ስለሚነኩ አንገብጋቢ ጉዳዮች እጥር ምጥን ያሉ መረጃዎች ለማቅረብ ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። እነዚህን ቅጂዎች እንዲያነቧቸው ብተውልዎ ደስ ይለኛል።”
6 መጽሔቶቹን የወሰዱ ሰዎች መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የተባሉትን ‘የመልካም ወሬ ምሥራች’ የያዙ መጽሔቶች በማንበብ እንደሚጠቀሙ አያጠራጥርም።— ኢሳ. 52:7