የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/97 ገጽ 1
  • ‘ቃሉን እንሰብካለን’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ቃሉን እንሰብካለን’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ቃሉን ስበክ”
    ለይሖዋ ዘምሩ
  • “ቃሉን ስበክ”
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • ምሥራቹ እየተሰበከ ያለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • የእውነትን አምላክ መምሰል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 1/97 ገጽ 1

‘ቃሉን እንሰብካለን’

1 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “መጨረሻው ቀን” ከሚሰጠው ዘገባ ጋር በሚስማማ መንገድ በአሁኑ ጊዜ ‘አብዛኞቹ ሰዎች የአምልኮት መልክ ብቻ ያላቸው’ ናቸው። (2 ጢ⁠ሞ. 3:​1, 5) ይህ የሆነው የሃይማኖት መሪዎች ለመንጎቻቸው እውነተኛ መንፈሳዊ መመሪያ ስለማይሰጡ ነው። የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት መጽሐፍ ቅዱስን ደግፈው የቆሙ አይደሉም። የአምላክን ቃል ከመስበክ ይልቅ ከንቱ የሆኑትን የፈላስፎችንና የሃይማኖት ምሁራንን ትምህርቶች ማስተጋባትን ወይም በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባትን መርጠዋል። ብዙ የሃይማኖት መሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ አያምኑም። መጽሐፍ ቅዱስ ጊዜው ያለፈበት መጽሐፍ እንደሆነ አድርገው ስለሚያስቡ ስለ ታላቁ ፈጣሪ የሚናገረውን ትምህርት ትተው ማስረጃ የሌለውን የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ በይፋ ያስፋፋሉ። አብዛኞቹ ቀሳውስት በአምላክ የግል ስም እንኳ አይጠቀሙም። ስሙ ከዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ ሲወጣ ምንም ዓይነት የተቃውሞ ሐሳብ አላቀረቡም።

2 በኢየሱስ ዘመን እንደነበሩት የሃይማኖት መሪዎች ሁሉ የዘመናችን ቀሳውስት ስብከትም ከንቱ ነው። (ማቴ. 15:​8, 9) ይህም ልክ ነቢዩ አሞጽ አስቀድሞ እንደተናገረው ነው። “የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት” ያልሆነ ረሃብ እንደሚሆን ገልጿል። (አሞጽ 8:​11) ሰዎች ከማንኛውም ነገር በላይ በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘው መንፈሳዊ ምግብ ያስፈልጋቸዋል።

3 የሰዎችን መንፈሳዊ ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው እንዴት ነው? ጳውሎስ ‘መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን’ አጥብቆ እንዲይዝ ጢሞቴዎስን ከመከረው በኋላ “ቃሉን” ለሌሎች “እንዲሰብክ” አሳስቦታል። (2 ጢ⁠ሞ. 3:​14, 15፤ 4:​2) እኛም የይሖዋ ምሥክሮች እንደመሆናችን መጠን “ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም” ብሎ የተናገረውን ምሳሌያችንን ኢየሱስን በመከተል በምንሰብክበት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምራቸው ነገሮች ጋር መስማማት አለብን። (ዮሐ. 7:​16) መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ መለኮታዊ ጥበብ እንደያዘ ስለምናውቅ ለትምህርታችን መሠረት አድርገን እንጠቀምበታለን። በተጨማሪም ሰዎች እያካፈልናቸው ያለው መልእክት ምንጭ ማን መሆኑን እንዲያውቁ እንፈልጋለን።​— 1 ቆ⁠ሮ. 2:​4-7

4 ሰዎች ይሖዋን እንዲያውቁና በእርሱም ላይ እምነት እንዲያሳድሩ በመጀመሪያ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ መስማት ይኖርባቸዋል። ጳውሎስ “ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?” በማለት ምክንያታዊ ሐሳብ ጽፏል። (ሮሜ 10:​14) የአምላክን ቃል በመስበክ ሌሎች በትክክለኛ እውቀት አማካኝነት እምነት እንዲኖራቸው እንረዳቸዋለን። እንዲህ ያለው እውቀት የሰዎችን ሕይወት ሊያሻሽል ይችላል፣ ያሻሽላልም። እንግሊዛዊው ደራሲ ቻርልስ ዲከንስ መጽሐፍ ቅዱስን አስመልክተው ሲጽፉ እንዲህ ብለዋል:- “እስከ ዛሬ ድረስ በዓለም ላይ ከኖሩትም ሆነ ወደፊት ከሚኖሩት መጻሕፍት ሁሉ የሚበልጥ መጽሐፍ ነው። ምክንያቱም እውነተኛና ታማኝ ለመሆን የሚጥር ማንኛውም ሰው ሊመራበት የሚችል ከሁሉ የተሻለ ትምህርት ያስተምራችኋል።”

5 መንፈሳዊ እውነትን ተርበው የነበሩ ሰዎች እውነት የአምላክ ቃል ድጋፍ እንዳለው ለመገንዘብ ችለዋል። ፍሬደሪክ ደብልዩ ፍራንዝ በ1913 ገና ወጣት የኮሌጅ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ሙታን የት ናቸው? (እንግሊዝኛ) የሚል ርዕስ ያለው ቡክሌት ተበረከተለት። መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ በጉጉት ካነበበ በኋላ “ይህ እውነት ነው” በማለት ተናገረ። በሚልዮን የሚቆጠሩ እውነት ፈላጊዎች ተመሳሳይ ወደሆነ መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ቃሉን በትጋትና ቅንዓት በተሞላበት ስሜት መስበካችንን እንቀጥል። እንዲህ ካደረግን ሌሎች ሰዎችም “ይህ እውነት ነው” ብለው ሲናገሩ በመስማት ከደስታው ተካፋይ እንሆናለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ