የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/99 ገጽ 1
  • ምሥራቹን በጉጉት ስበኩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምሥራቹን በጉጉት ስበኩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የተሟላ ምሥክርነት ስጡ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • በሚያዝያ 2000 ከምንጊዜውም የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንችል ይሆን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ምሥራቹን በጉጉት አውጁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 4/99 ገጽ 1

ምሥራቹን በጉጉት ስበኩ

1 “ላያችሁ እናፍቃለሁና . . . ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ ተዘጋጅቼአለሁ [“ጓጉቻለሁ፣” NW]።” ሐዋርያው ጳውሎስ በሮም ለሚገኙ ወንድሞች በጻፈው ደብዳቤ መክፈቻ ላይ ከላይ እንዳለው በማለት ስለራሱ ተናግሯል። ጳውሎስ እነርሱን ለማየት የጓጓው ለምን ነበር? “በእናንተም ፍሬ አገኝ ዘንድ . . . በወንጌል አላፍርምና፤ . . . ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና” ብሏል።—ሮሜ 1:11-16

2 ጳውሎስ በኤፌሶን የሚገኙ ሽማግሌዎችን ለማነጋገር ተመሳሳይ የሆነ ጉጉት አሳይቶ ነበር። እንዲህ ሲል አስታውሷቸዋል:- ‘ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፣ . . . ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም አስተማርኋችሁ እንጂ አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም።’ (ሥራ 20:18-21) ጳውሎስ በተመደበበት የአገልግሎት ክልል ሁሉ የመዳንን ምሥራች ለማዳረስና የመንግሥቱን ፍሬ ለማግኘት ታጥቆ ተነስቶ ነበር። ይህ ልንኮርጀው የሚገባ ግሩም ዝንባሌ ነው!

3 ራሳችንን እንዲህ እያልን ልንጠይቅ እንችል ይሆናል:- ‘በምኖርበት አካባቢ ምሥራቹን በመስበክ ረገድ እንዲህ ዓይነት ጉጉት አሳያለሁን? የስብከቱን ሥራ እንደ ግዳጅ ከመቁጠር ይልቅ ምሥራቹን በተቻለኝ መጠን ለብዙ ሰዎች የማካፈል ጉጉት አለኝን? የግል ሁኔታዎቼን በሐቀኝነት አመዛዝኛለሁ? ከቤት ወደ ቤት፣ በመንገድ ላይ፣ በገበያ ቦታዎች፣ በስልክና መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመስከርን የመሳሰሉ በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ የሚገኙ አማራጮችን በሙሉ ሞክሬያለሁን?

4 በሚያዝያ ምሥራቹን በጉጉት ስበኩ፦ የሚያዝያ ወር በስብከቱ ሥራ የምናደርገውን የግል ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል አመቺ አጋጣሚ ነው። እንድናሟላ የሚጠበቅብን የሰዓት ግብ መቀነሱ ብዙዎች ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ነው። በሚያዝያና በግንቦት በረዳት አቅኚነት ለማገልገል ሁኔታችሁ ይፈቅድላችኋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ወይም ማሻሻያ ከተደረገበት የሰዓት ግብ አንጻር የዘወትር አቅኚ መሆን ትችሉ ይሆናል። የጉባኤ አስፋፊ ከሆንክ አቅኚ ለሆኑት ድጋፍ በመስጠት በዚህና በሚቀጥለው ወር በአገልግሎት ከወትሮው የበለጠ ሰዓት ማሳለፍ ትችላለህ? እንዲህ ማድረግህ የይሖዋን ልብ ደስ ያሰኛል!

5 ጳውሎስ እንዳደረገው ሁሉ የመንግሥቱ አስፋፊዎች ተጨማሪ ጥረት በማድረግ በጉጉት ስሜት መስበካቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል። የአቅማችንን ያህል በአገልግሎት መሳተፋችን እውነተኛ ደስታ ያስገኝልናል። ጳውሎስ ከቅዱስ አገልግሎቱ ይህን ዓይነት ደስታ አግኝቷል። ግሩም ምሳሌውን መኮረጃችን ጠቃሚ ነው።—ሮሜ 11:13፤ 1 ቆሮ. 4:16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ