የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/09 ገጽ 1
  • እንዴት ይሰማሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንዴት ይሰማሉ?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምሥራቹን ያለማሰለስ ማወጅ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • በተደጋጋሚ የምንሄደው ለምንድን ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ያለማሰለስ ስበኩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ‘በጌታ የተቀበልከውን አገልግሎት ለመፈጸም ትኩረት ስጥ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
km 1/09 ገጽ 1

እንዴት ይሰማሉ?

1. የስብከቱን ሥራ ተፈታታኝ ሊያደርግብን የሚችለው ምንድን ነው? በጽናት የምንቀጥለውስ ለምንድን ነው?

1 የይሖዋ ቀን በጣም እየቀረበ ባለበት በዚህ ወቅት በርካታ ሰዎች ስለ አምላክና እሱ ለሰው ልጆች ስላለው ዓላማ ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ መርዳታችን እጅግ አንገብጋቢ ነው። (ዮሐ. 17:3፤ 2 ጴጥ. 3:9, 10) አብዛኞቹ ሰዎች ቸልተኞች ስለሆኑ ወይም በስብከቱ ሥራችን ምክንያት ሊያፌዙብን ስለሚችሉ አንዳንድ ጊዜ በሥራው መቀጠል አስቸጋሪ ይሆንብናል። (2 ጴጥ. 3:3, 4) ይሁንና ምሥራቹን ቢሰሙ መልእክቱን ሊቀበሉ የሚችሉ ብዙ ሰዎች በክልላችን ውስጥ አሉ ብለን እንድናምን የሚያደርገን በቂ ምክንያት አለን። ታዲያ እንዲህ ያሉት ሰዎች የሚሰብክላቸው ሳይኖር እንዴት ይሰማሉ?—ሮም 10:14, 15

2. የሐዋርያው ጳውሎስ ምሳሌ የሚያበረታታን እንዴት ነው?

2 ተቃውሞን መጋፈጥ፦ የመንግሥቱን መልእክት መስማት የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች ስላሉ የሚያጋጥመን ተቃውሞ ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባም። ሐዋርያው ጳውሎስ አውሮፓ ውስጥ ምሥራቹን የሰበከባት የመጀመሪያዋ ከተማ ፊልጵስዩስ ነበረች። በዚያን ወቅት ጳውሎስና ሲላስ በሐሰት የተወነጀሉ ከመሆኑም በተጨማሪ በበትር ተደብድበው እስር ቤት ተጣሉ። (ሥራ 16:16-24) ይሁን እንጂ ጳውሎስ የደረሰበት እንዲህ ያለው ሥቃይ ፈርቶ ወደኋላ እንዲል አላደረገውም። ጳውሎስ ሚስዮናዊ ጉዞውን በመቀጠል ወደ ተሰሎንቄ በሄደበት ወቅት ‘በአምላክ እርዳታ ድፍረት አግኝቶ’ ነበር። (1 ተሰ. 2:2) ጳውሎስ የተወው ይህ ምሳሌ ‘ተስፋ መቁረጥ’ የማይኖርብን ለምን እንደሆነ አያሳይም?—ገላ. 6:9

3. ቀደም ሲል መልእክታችንን የመስማት ፍላጎት ያልነበራቸው አንዳንድ ሰዎች አመለካከታቸውን እንዲቀይሩ ያደረጋቸው ምን ሊሆን ይችላል?

3 ለበርካታ ዓመታት የመንግሥቱን መልእክት ለመስማት ፈቃደኛ ያልነበሩ ብዙ ሰዎች የአመለካከት ለውጥ አድርገዋል። እንዲህ ያለ ለውጥ ያደረጉት በኢኮኖሚ መዋዠቅ፣ በሕመም፣ የቤተሰባቸውን አባል በሞት በማጣታቸው ወይም በዓለም ላይ በሚታዩ አስጨናቂ ነገሮች የተነሳ ሊሆን ይችላል። (1 ቆሮ. 7:31) ተቃዋሚ ወላጆች የነበሯቸው አንዳንድ ልጆች አሁን አድገው ምሥራቹን ለመስማት ፈቃደኞች ሆነዋል። በስብከቱ ሥራ መቀጠላችን፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች ጊዜው ከማለፉ በፊት ‘የይሖዋን ስም ለመጥራት’ የሚያስችል አጋጣሚ ይከፍትላቸዋል።—ሮም 10:13

4. በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ “ያለማሰለስ” እንድንካፈል የሚያነሳሳን ምንድን ነው?

4 “ያለማሰለስ” ስበኩ፦ ለአምላክም ሆነ ለሰዎች ያለን ፍቅር በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበሩት ሐዋርያት ሁሉ እኛም በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ “ያለማሰለስ” ወደፊት እንድንገፋ ያነሳሳናል። (ሥራ 5:42) ብዙ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸመ ባለው ‘ጸያፍ ተግባር ያዝናሉ፤ እንዲሁም ያለቅሳሉ።’ (ሕዝ. 9:4) እነዚህ ሰዎች ምሥራቹን ሲሰሙ እንዴት ያለ ተስፋና እፎይታ ያገኛሉ! አብዛኞቹ ሰዎች ለመስማት ፈቃደኞች በማይሆኑበት ጊዜም እንኳ ይሖዋ በምናደርገው ጥረት እንደሚደሰት የሚያሳይ ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃ አለን።—ዕብ. 13:15, 16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ