በስብሰባዎቻችን ላይ ለይሖዋ ለመዘመር ተዘጋጅታችኋል?
1 በስብሰባዎቻችን ላይ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀት የውዳሴ መዝሙሮችን ለመዘመር መዘጋጀትንም ይጨምራል። ከዚህ በታች የቀረቡትን ሐሳቦች ተመልከቱ።
2 የግጥሞቹን መልእክት ተረዱ፦ የመዝሙሩ ጭብጥ የተመሠረተበት ጥቅስም ሆነ ከእያንዳንዱ መዝሙር በታች ያሉት ተጨማሪ ጥቅሶች ግጥሞቹ የተመሠረቱባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ለማጉላት ይረዳሉ።
3 ተለማመዷቸው፦ ከአዲሶቹ መዝሙሮች ጋር በሚገባ ለመተዋወቅ በየሳምንቱ ከምታደርጉት የቤተሰብ አምልኮ ላይ የተወሰነ ሰዓት ለልምምድ መመደብ ትችላላችሁ። በእያንዳንዱ ስብሰባ ወቅት ከሚደመጠው ፒያኖ ጋር አንድ ላይ ዘምሩ።
4 የፊታችን እሁድ ከምናደርገው የመጠበቂያ ግንብ ጥናት አንስቶ ለይሖዋ ዘምሩ ከሚለው መጽሐፍ ላይ መዘመር እንጀምራለን፤ ታዲያ በዚያ ወቅት ለመዘመር ዝግጁ ናችሁ? የመዝሙሮቹን ትርጉም ለመረዳትና መዝሙሮቹን ለመለማመድ ጊዜ የምትመድቡ ከሆነ ዝግጁ እንደምትሆኑ ግልጽ ነው።