መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ሰዎች ደስተኛ እንዲሆኑ ምን የሚያስፈልጋቸው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ማቴዎስ 5:3ን አውጣለት።] ይህ ሐሳብ ኢየሱስ ደስታን አስመልክቶ ከተናገራቸው ሐሳቦች አንዱ ብቻ ነው። ይህ ርዕስ ኢየሱስ እውነተኛ ደስታ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ከተናገረው ሐሳብ ምን ትምህርት ልናገኝ እንደምንችል ያብራራል።” ገጽ 16 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ነሐሴ 2010
“በዛሬው ጊዜ ስለ አጋንንት፣ ስለ አስማተኞችና ስለ ጠንቋዮች የሚናገሩ በርካታ ፊልሞች ይሠራሉ። እርስዎስ በእርግጥ አጋንንት አሉ ብለው ያምናሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም 1 ቆሮንቶስ 10:20ን አንብብ።] ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አጋንንት ምን እንደሚልና ራሳችንን ከአጋንንት ጥቃት እንዴት መጠበቅ እንደምንችል ያብራራል።” ገጽ 20 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
በአካባቢህ ያሉ ሰዎችን የሚያሳስብ በዜና ላይ የቀረበ አንድ ርዕስ ተናገር። ከዚያም እንዲህ በል፦ “ሰዎች እንዲህ የመሰሉ መጥፎ ድርጊቶችን የሚፈጽሙት ለምንድን ነው ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ በቅርቡ የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጣል። [2 ጴጥሮስ 3:13ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክፋት መንስኤ ምን እንደሚልና አምላክ በቅርቡ የክፋት ድርጊቶችን እንዴት እንደሚያስወግድ ይህ መጽሔት ያብራራል።”
ንቁ! መስከረም 2010
“የሞባይል ስልኮች፣ ኢ-ሜይል፣ ቻት ሩምና ዘመኑ ያፈራቸው ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች ሰዎችን ከብቸኝነት ስሜት አላቀዋል ወይስ ችግሩን አባብሰዋል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የብቸኝነትን ስሜት ለማሸነፍ የሚረዳ አንድ ሐሳብ እዚህ ጥቅስ ላይ ይመልከቱ። [የሐዋርያት ሥራ 20:35ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ የሚሰጠውን ጠቃሚ የሆነ ተጨማሪ ምክር ይዟል።”