መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“ብዙ ሰዎች፣ አምላክ ጭንቀታችንም ሆነ ሐዘናችን ደንታ እንደማይሰጠው ይሰማቸዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ እርስዎ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም መዝሙር 34:18ን አንብብ።] በዚህ መጽሔት ገጽ 19 ላይ የሚገኘው ርዕስ፣ አምላክ ሐዘናችንን ብሎም የሚሰማንን የጥፋተኝነትና የዋጋ ቢስነት ስሜት እንድናሸንፍ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት 2010
“አንዳንድ ሰዎች አምላክን የትም የሚኖር አንድ ኃይል አድርገው ይመለከቱታል። ሌሎች ደግሞ ስሜት ያለው ሕያው አካል እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህን ትኩረት የሚስብ ሐሳብ ልብ ይበሉ። [1 ጴጥሮስ 5:6, 7ን አንብብ።] በዚህ መጽሔት ገጽ 29 ላይ የሚገኘው ርዕስ፣ ‘አምላክ አካል አለው?’ ለሚለው ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ሁላችንም ረክተን መኖር እንፈልጋለን። ታዲያ ረክተን ለመኖር ገንዘብ የሚያስፈልገን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ትንሽ ነገር እያለውም እንኳ ባለው ነገር ረክቶ መኖርን ተምሯል። [ፊልጵስዩስ 4:11, 12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አንድ ሰው ባለው ረክቶ የመኖርን ሚስጥር እንዲማር የሚያስችሉትን አምስት ቅዱስ ጽሑፋዊ ነጥቦች ያብራራል።”
ንቁ! ኅዳር 2010
“አምላክ የለሽ የሆኑ አንዳንድ ሰዎች በአምላክ ስም የሚደረጉ በርካታ መጥፎ ነገሮችን በመጥቀስ ዓለም ከሃይማኖት ነፃ ብትሆን የተሻለ ስፍራ እንደምትሆን ያላቸውን ስሜት ይገልጻሉ። ይህን ጉዳይ በተመለከተ እርስዎ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የሐሰት ሃይማኖት በሰዎች ላይ ሥቃይ የሚያስከትለው ለምን እንደሆነ የሚገልጽ አንድ ምክንያት ላንብብልዎት። [2 ጢሞቴዎስ 4:3, 4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ አምላክ የለሾች የሚያቀርቧቸው ሐሳቦች ተቀባይነት እንዲያጡ የሚያደርጓቸው አንዳንድ ምክንያቶች የትኞቹ እንደሆኑ ይጠቁማል።”