መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“ነጠላ የሆኑ ወላጆች ሁለት ሆነው ልጆቻቸውን ከሚያሳድጉ ወላጆች የበለጠ ችግር ያጋጥማቸዋል ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሰዎች አሳቢነት እንድናሳይ ያበረታታናል። [መዝሙር 41:1ን አንብብ።] በገጽ 22 ላይ የሚገኘው ርዕስ ነጠላ ለሆኑ ወላጆች አሳቢነት ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2010
“ብዙ ሰዎች ‘አምላክ ካለ ዲያብሎስን የማያጠፋው ለምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቃሉ። እርስዎስ እንዲህ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በዚህ መጽሔት ገጽ 10 እና 11 ላይ የሚገኘው ርዕስ ለዚህ ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ይዟል። ከዚህም በተጨማሪ ዲያብሎስ በሚወገድበት ጊዜ ይህ ዓለም ምን ሊመስል እንደሚችል ይናገራል።” ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“በርካታ ሰዎች ስለ ኤደን የአትክልት ስፍራ የሚነገረው ታሪክ ተረት እንደሆነ ይሰማቸዋል። ኢየሱስ አዳምና ሔዋንን በገሃዱ ዓለም የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን በመጥቀስ እንዳስተማረ ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ማቴዎስ 19:4-6ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የኤደንን የአትክልት ስፍራ አስመልክቶ ብዙ ጊዜ ለሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።”
ንቁ! ጥር 2011
የመጽሔቱን የፊት ለፊት ገጽ አሳየውና እንዲህ በማለት ጠይቀው፦ “እርስዎ ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ቅዱሳን መጻሕፍት ሰዎች ሰላማዊ እንዲሆኑ ያበረታታሉ። [ያዕቆብ 3:17ን አንብብ።] ታዲያ ሃይማኖት የሰውን ዘር አንድ ማድረግ ያልቻለው ለምንድን ነው? ሃይማኖት ለሰላም የቆመ ኃይል የሚሆንበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ይህ መጽሔት የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ይዟል።”