የመንግሥቱን መዝሙሮች መስማት የሚቻልበት ጥሩ አጋጣሚ
የአምላክ አገልጋዮች ሙዚቃን ከይሖዋ የተገኘ መልካም ስጦታ አድርገው ይመለከቱታል። (ያዕ. 1:17) ብዙ ጉባኤዎች ከስብሰባ በፊትና በኋላ የመንግሥቱን መዝሙሮች ዝግ ባለ ድምፅ ይከፍታሉ። እነዚህን ሙዚቃዎች መስማታችን ወደ ስብሰባው ስንገባ ደስ የሚል ስሜት እንዲኖረን ያስችለናል። ለምናቀርበው አምልኮ አእምሯችንን እንድናዘጋጅም ይረዳናል። በተጨማሪም በመዝሙር መጽሐፋችን ላይ የሚገኙ አዳዲስ መዝሙሮችን ማዳመጣችን ዜማውን በቃላችን እንድንይዘውና መዝሙሩን በደንብ ለመዘመር ያስችለናል። ከስብሰባ በኋላም ሙዚቃውን ማዳመጥ ደስ የሚል ስሜት እንዲሰፍን ስለሚያደርግ እርስ በርስ ለመበረታታት ያስችላል። በመሆኑም የሽማግሌዎች አካል፣ በፒያኖ ብቻ የተዘጋጀው መዝሙር ከስብሰባ በፊት እና በኋላ በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ እንዲከፈት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። ሆኖም ሽማግሌዎች የሙዚቃው ድምፅ ከመጠን በላይ ጮኾ ሌሎች እንዳይደማመጡ የሚያግድ እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።