የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“እስቲ አንድ ትኩረት የሚስብ ጥያቄ ላሳይዎት። [በኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ጥያቄ አንብብለት።] ምን ይመስልዎታል? [በጥያቄው ሥር ያሉትን ሁለት አንቀጾችና በአንቀጹ ላይ ካሉት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አንብብለት።] ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ያስነሳው ለምን እንደሆነና ይህን ማወቅዎ ለእርስዎ ምን ጥቅም እንዳለው ሌላ ጊዜ መጥቼ ብንወያይበት ምን ይመስልዎታል?”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“በዓለም ላይ በጣም ብዙ አሳዛኝ ነገሮች የሚከሰቱት ለምን እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ በራእይ 12:9 ላይ ምክንያቱን ይነግረናል። [ጥቅሱን አንብብ።] ቁጥር 12 ግን የሚያጽናና ሐሳብ ይዟል። [ራእይ 12:12ን አንብብ።] በቅርቡ ሰይጣን የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ይወገዳል። ‘ሰይጣንን ልንፈራው ይገባል?’ የሚለው ይህ ርዕስ በአሁኑ ጊዜ ራሳችንን ከሰይጣን ተጽዕኖ መጠበቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነና ሰይጣን ምን እንደሚደርስበት ያብራራል። መጽሔቱን ወስደው ሊያነቡት ይችላሉ።”
ንቁ! ኅዳር
“ደስተኛ መሆን የማይፈልግ ሰው የለም፤ ብዙዎች ግን ደስተኛ አይደሉም። እውነተኛ ደስታ የሚገኘው እንዴት ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በሕይወታቸው ደስታ እንዲያገኙ እንደረዳቸው ተመልክቼያለሁ። ለምሳሌ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ላሳይዎት። [ዕብራውያን 13:5ን አንብብ።] ይህ መጽሔት እውነተኛ ደስታ ለማግኘት ቁልፍ የሆኑ አራት የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮችን ያብራራል።”