የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 ነሐሴ ገጽ 8
  • በቅርቡ ረዳት አቅኚ መሆን የምችለው መቼ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በቅርቡ ረዳት አቅኚ መሆን የምችለው መቼ ነው?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ድሃ ብትሆንም ደስተኛና ብሩህ ተስፋ ያላት ሴት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ልታወጣው የምትችለው ጠቃሚ ግብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ይሖዋን ለማወደስ የሚያስችሉ ተጨማሪ አጋጣሚዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 ነሐሴ ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በቅርቡ ረዳት አቅኚ መሆን የምችለው መቼ ነው?

ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ያየው ራእይ የይሖዋ ሕዝቦች በፈቃደኝነት መሥዋዕት እንደሚያቀርቡ ያሳያል። የምሥጋና መሥዋዕት በማቅረብ ረገድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት የምንችለው እንዴት ነው?—ዕብ 13:15, 16

ይህን ማድረግ የሚቻልበት አንዱ መንገድ ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል ነው። በ2018 የአገልግሎት ዓመት ውስጥ አምስት ቅዳሜ ወይም አምስት እሁድ ያላቸው በርካታ ወራት አሉ። ይህም በተለይ የሙሉ ጊዜ ሰብዓዊ ሥራ ለሚሠሩና አብዛኛውን ጊዜ ቅዳሜና እሁድ ብቻ አገልግሎት ለሚወጡ አስፋፊዎች ጠቃሚ ነው። ከዚህም በተጨማሪ አስፋፊዎች በመጋቢትና በሚያዝያ ወራት፣ እንዲሁም የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን በሚጎበኝበት ወር ከ30 ወይም ከ50 ሰዓት አንዱን በመምረጥ ረዳት አቅኚ ሆነው ማገልገል ይችላሉ።

ሁኔታችን ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል የማይፈቅድልን ቢሆንስ? የአገልግሎታችንን ጥራት፣ ከተቻለ ደግሞ መጠኑን ከፍ ለማድረግ ጥረት ማድረግ እንችላለን። ሁኔታችን ምንም ይሁን ምን፣ ለይሖዋ ያለን ፍቅር በ2018 የአገልግሎት ዓመት ለእሱ ምርጣችንን እንድንሰጠው እንዲያነሳሳን ምኞታችን ነው!—ሆሴዕ 14:2

ሳቢና ኧርናንዴዝ እስክሪብቶ በአፏ በመያዝ የረዳት አቅኚ ማመልከቻ ስትሞላ

እንደ ሳቢና ኧርናንዴዝ ቅንዓት ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?

በይሖዋ እርዳታ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ሳቢና በይሖዋ አገልግሎት የምታደርገውን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ያነሳሳት ምንድን ነው?

  • ሳቢና የተወችው ምሳሌ አንተን የሚያበረታታህ እንዴት ነው?

  • በ2018 የአገልግሎት ዓመት ረዳት አቅኚ ሆነህ ማገልገል የምትችለው በየትኞቹ ወራት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ