ክርስቲያናዊ ሕይወት
ከዮናስ መጽሐፍ የምናገኛቸው ትምህርቶች
ይሖዋ፣ በእምነታቸው ምሳሌ የሚሆኑ የተለያዩ ወንዶችና ሴቶችን የሕይወት ታሪክ በቃሉ ውስጥ አስፍሮልናል፤ ይህን ያደረገው ከእነሱ ጠቃሚ ትምህርት እንድናገኝ ሲል ነው። (ሮም 15:4) ከዮናስ መጽሐፍ ምን ትምህርት አግኝተሃል? የቤተሰብ አምልኮ፦ ዮናስ—ከይሖዋ ምሕረት ትምህርት ማግኘት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሦስት አስፋፊዎች ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች አጋጥመዋቸዋል?
ጠንከር ያለ ምክር ቢሰጠን ወይም የአገልግሎት መብታችንን ብናጣ ከዮናስ መጽሐፍ ምን ማበረታቻ እናገኛለን? (1ሳሙ 16:7፤ ዮናስ 3:1, 2)
የዮናስ ታሪክ ለአገልግሎት ክልላችን አዎንታዊ አመለካከት ይዘን ለመቀጠል የሚረዳን እንዴት ነው? (ዮናስ 4:11፤ ማቴ 5:7)
ከባድ የጤና ችግር ሲያጋጥመን የዮናስ ታሪክ የሚያጽናናን እንዴት ነው? (ዮናስ 2:1, 2, 7, 9)
መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ባነበብነው ነገር ላይ ማሰላሰል ያለውን ጥቅም በተመለከተ ከዚህ ቪዲዮ ምን ትምህርት አግኝተሃል?