ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘካርያስ 9-14
‘በተራሮች መካከል ካለው ሸለቆ’ አትውጡ
ይሖዋ በጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነቱ ሥር ያለ መስተዳድር የሆነውን መሲሐዊውን መንግሥት በ1914 ሲያቋቁም በምሳሌያዊ ሁኔታ ‘ተራራው ተከፍሎ እጅግ ትልቅ ሸለቆ’ ተፈጥሯል። ከ1919 አንስቶ የአምላክ ሕዝቦች ‘በተራሮች መካከል ባለው በዚህ ሸለቆ’ ውስጥ ጥበቃ አግኝተዋል
ሰዎች የይሖዋ ጥበቃ ወደሚገኝበት ‘ሸለቆ መሸሽ’ የሚችሉት እንዴት ነው?
ከዚህ ምሳሌያዊ ሸለቆ ውጭ ያሉ ሰዎች በሙሉ በአርማጌዶን ይጠፋሉ
የይሖዋ ጥበቃ በሚገኝበት ሸለቆ ውስጥ መቆየት የምችለው እንዴት ነው?