ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሉቃስ 12-13
“እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ”
ኢየሱስ በሉቃስ 12:6, 7 ላይ የተናገረው ሐሳብ አውድ ምንድን ነው? በቁጥር 4 ላይ እንደምናነበው ኢየሱስ ተከታዮቹ፣ ሊቃወሟቸው አልፎ ተርፎም ሊገድሏቸው የሚችሉ ሰዎችን መፍራት እንደሌለባቸው ነግሯቸዋል። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደፊት ለሚጠብቃቸው ተቃውሞ እያዘጋጃቸው ነበር። ይሖዋ ሁሉንም አገልጋዮቹን ከፍ አድርጎ እንደሚመለከታቸውና ዘላቂ ጉዳት እንዲደርስባቸው እንደማይፈቅድ አረጋግጦላቸዋል።
ስደት እየደረሰባቸው ላሉ ወንድሞችና እህቶች አሳቢነት በማሳየት ረገድ ይሖዋን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?
በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ ወንድሞችንና እህቶችን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?
በአሁኑ ጊዜ በየት የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች በእስር ላይ ይገኛሉ?