ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | የሐዋርያት ሥራ 4-5
የአምላክን ቃል በድፍረት መናገራቸውን ቀጠሉ
ሐዋርያት አስተማሪ ለመሆን የሚያስፈልገውን ብቃት ያገኙት እንዴት ነው? በእርግጠኝነት እና በድፍረት ለመናገር የረዳቸውስ ምንድን ነው? ከታላቁ አስተማሪ “ከኢየሱስ ጋር” የነበሩ ሲሆን ከእሱም ተምረዋል። (ሥራ 4:13) እኛስ ውጤታማ አስተማሪ ለመሆን የሚረዱን ከኢየሱስ ልንማር የምንችላቸው ነገሮች የትኞቹ ናቸው?