ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ያዕቆብ 3-5
አምላካዊ ጥበብን አንጸባርቁ
አምላካዊ ጥበብ በብዙ የሕይወታችን ዘርፎች ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ቅራኔ በሚፈጠርበት ጊዜ ሰላማዊ ግንኙነት ለመመሥረት ይረዳናል። አምላካዊ ጥበብን ማዳበራችን በምናሳየው ምግባር ላይ ለውጥ ያመጣል።
ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የአምላካዊ ጥበብ ገጽታዎች መካከል በቅርቡ በሕይወቴ ያንጸባረቅኩት የትኞቹን ነው? አንዳንዶቹን ገጽታዎች በማንጸባረቅ ረገድ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልገኝ ይሆን?’
ንጹሕ
ሰላማዊ
ምክንያታዊ
ለመታዘዝ ዝግጁ የሆነ
ምሕረትና መልካም ፍሬዎች የሞሉበት
አድልዎ የሌለበት
ግብዝነት የሌለበት