ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ራእይ 10-12
‘ሁለቱ ምሥክሮች’ ተገደሉ፤ ከዚያም እንደገና ሕያው ሆኑ
‘ሁለቱ ምሥክሮች’፦ የአምላክ መንግሥት በ1914 ሲቋቋም ለሥራው አመራር ይሰጡ የነበሩትን ቅቡዓን ወንድሞች ያቀፈውን አነስተኛ ቡድን ያመለክታል
ተገደሉ፦ ለሦስት ዓመት ተኩል ያህል “ማቅ ለብሰው” ከሰበኩ በኋላ ‘መገደላቸው’ እስር ቤት ገብተው ከእንቅስቃሴ ውጭ እንዲሆኑ መገደዳቸውን ያመለክታል
ዳግመኛ ሕያው ሆኑ፦ ምሳሌያዊው የሦስት ቀን ተኩል ጊዜ ሲያበቃ ከእስር ተፈተው እንደ ቀድሞው ለስብከቱ ሥራ አመራር መስጠታቸውን እንደቀጠሉ ያሳያል