ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 17–18
ልካቸውን የሚያውቁ ወንዶች አሠልጥነው ኃላፊነት ይሰጣሉ
ተሞክሮ ያላቸው ወንድሞች ወጣቶችን አሠልጥነው ኃላፊነት በመስጠት ልካቸውን እንደሚያውቁ እንዲሁም ፍቅርና ማስተዋል እንዳላቸው ያሳያሉ። ታዲያ ሌሎችን አሠልጥኖ ኃላፊነት መስጠት የሚቻለው እንዴት ነው?
ተጨማሪ ኃላፊነት የመቀበል አቅም ያላቸውን ወንድሞች ምረጡ
አንድን ሥራ ለማከናወን የሚያስችላቸውን መመሪያ በግልጽ ስጧቸው
የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ፣ መሣሪያና እርዳታ ስጧቸው
የሚያከናውኑትን ሥራ በመመልከት እንደምትተማመኑባቸው ግለጹላቸው
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ለሌሎች የትኞቹን ኃላፊነቶች መስጠት እችላለሁ?’