የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ግንቦት ገጽ 9
  • “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ለሚያጋጥሙ ነገሮች ዝግጁ ሁኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ለሚያጋጥሙ ነገሮች ዝግጁ ሁኑ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዝግጁ ናችሁ?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ሕዝባዊ ዓመፅ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ለኢኮኖሚ ቀውስ ተዘጋጅታችኋል?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • የተፈጥሮ አደጋ ቢደርስ ዝግጁ ናችሁ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ግንቦት ገጽ 9
የአንድ ቤተሰብ አባላት ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ምግብ፣ ውኃና ሌሎች ቁሳቁሶችን ቤታቸው ውስጥ ሲያስቀምጡ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ለሚያጋጥሙ ነገሮች ዝግጁ ሁኑ

የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ እንደመሆኑ መጠን የሚያጋጥሙን ችግሮች እየተባባሱ እንደሚሄዱ እንጠብቃለን። (2ጢሞ 3:1፤ ማቴ 24:8) አደጋ በሚከሰትበት ወቅት የይሖዋ ሕዝቦች ብዙውን ጊዜ ወቅታዊና ሕይወት አድን መመሪያ ይሰጣቸዋል። በዚያ ጊዜ በሕይወት መትረፋችን የተመካው የሚሰጠንን መመሪያ በመታዘዝ ከአሁኑ ዝግጁ በመሆናችን ላይ ነው፤ በመንፈሳዊም ሆነ በቁሳዊ ዝግጁ መሆን አለብን።—ሉቃስ 16:10

  • በመንፈሳዊ ዝግጁ መሆን፦ ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ አዳብሩ። በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች መካፈልን ተለማመዱ። በጉባኤያችሁ ካሉ አስፋፊዎች ጋር ለተወሰነ ጊዜ መገናኘት ባትችሉ አትደናገጡ። (ኢሳ 30:15) መቼም ቢሆን ከይሖዋና ከኢየሱስ ልትለዩ እንደማትችሉ አስታውሱ።—od 176 አን. 15-17

  • በቁሳዊ ዝግጁ መሆን፦ ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ቦርሳ አዘጋጁ፤ ከዚህም በተጨማሪ ረዘም ላለ ጊዜ በአንድ ቦታ ተጠልላችሁ ለመኖር ብትገደዱ ለዚያ የሚያስፈልጋችሁን ምግብ፣ ውኃ፣ መድኃኒትና ሌሎች መሰል ነገሮችን ምክንያታዊ በሆነ መጠን አስቀምጡ።—ምሳሌ 22:3፤ g17.5 4, 6

የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። አንድ ወንድም መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነብ።

    ለአደጋ ጊዜ ራሳችንን በመንፈሳዊ ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ‘የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። የአደጋ ጊዜ ቦርሳ፣ አድራሻ የተጻፈበት ወረቀትና አደጋ ቢፈጠር ቤተሰቡ የሚገናኝበትን ቦታ የሚያሳይ ካርታ።

    የሚከተሉትን ነገሮች ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

    • ከሽማግሌዎች ጋር ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ

    • ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ቦርሳ ማዘጋጀት

    • ምን ዓይነት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉና በእያንዳንዱ ሁኔታ ሥር ምን ማድረግ እንዳለብን መወያየት

  • ‘የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ምስሎች፦ አደጋ የገጠማቸው ወንድሞቻችንን መርዳት የምንችልባቸው መንገዶች። 1. አንድ ወንድም ሲጸልይላቸው። 2. ወንድሞች በእርዳታ ሥራ እገዛ ሲያበረክቱ። 3. አንድ ወንድም ለዓለም አቀፉ ሥራ የገንዘብ መዋጮ ሲያደርግ።

    አደጋ ያጋጠማቸውን መርዳት የምንችልባቸው ሦስት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘ለአደጋ ዝግጁ መሆንን በተመለከተ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምን ትምህርት አግኝቻለሁ?’

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ