የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ሐምሌ ገጽ 9
  • የሰዎችን ልብ መንካት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሰዎችን ልብ መንካት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥያቄዎችን ተጠቀሙ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የአምላክን ቃል ተጠቀሙ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • በጸሎት አማካኝነት የይሖዋን እርዳታ ተቀበሉ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ መጥፎ ልማዶችን እንዲያስወግዱ እርዷቸው
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ሐምሌ ገጽ 9

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

የሰዎችን ልብ መንካት

አምላክን መታዘዝ የሚመነጨው ከልብ ነው። (ምሳሌ 3:1) በመሆኑም በምናስተምርበት ወቅት የሚሰሙንን ሰዎች ልብ ለመንካት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። ታዲያ ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ለጥናታችሁ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች በማስተማር ብቻ አትወሰኑ፤ እነዚህን እውነቶች ከራሱ ሕይወት እንዲሁም ከይሖዋ ጋር ካለው ዝምድና ጋር እንዲያዛምድ እርዱት። የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች የአምላክን ፍቅር፣ ጥሩነትና ጽድቅ የሚያሳዩት እንዴት እንደሆነ እንዲገነዘብ እርዱት። ስለሚማረው ነገር ያለውን ስሜት እንዲያጤን ለመርዳት በዘዴ ጥያቄዎች ጠይቁት። ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ወይም ልማድ ማስተካከሉ ስለሚያስገኝለት ጥቅም እንዲያመዛዝን እርዱት። ጥናታችሁ ለይሖዋ ያለው ልባዊ ፍቅር እንዳደገ ስትመለከቱ በአገልግሎት የምታገኙት ደስታ ይጨምራል።

ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—የሰዎችን ልብ መንካት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—አሻሽሉ—የሰዎችን ልብ መንካት’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ኒታ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸው ወቅት ጄድን ጥያቄ ስትጠይቃት።

    ኒታ ጄድን “ሰኞ ባወራነው ነገር ላይ አሰብሽበት?” ብላ የጠየቀቻት ለምንድን ነው?

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—አሻሽሉ—የሰዎችን ልብ መንካት’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ኒታ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅማ ስታስረዳ።

    ጄድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች ይሖዋ ለእሷ ያለውን ፍቅር እንደሚያሳዩ እንድትገነዘብ ኒታ የረዳቻት እንዴት ነው?

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—አሻሽሉ—የሰዎችን ልብ መንካት’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ጄድ ኒታን ስታዳምጣት።

    የጥናቶቻችንን ልብ መንካት ከቻልን እድገት ለማድረግ ይነሳሳሉ

    ጄድ ለአምላክ ያላትን ፍቅር ማሳየት የምትችልበትን መንገድ እንድታመዛዝን ኒታ የረዳቻት እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ