የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 መስከረም ገጽ 3-16
  • “ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን ጽሑፍ በአገልግሎት ላይ ተጠቀሙበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን ጽሑፍ በአገልግሎት ላይ ተጠቀሙበት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ለዘላለም በደስታ ኑር!” ተጠቅመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት—እንዴት?
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ተጠምቀው ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት አድርገው እንዲጠመቁ መርዳት—ክፍል አንድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 መስከረም ገጽ 3-16
አንድ ባልና ሚስት “ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን ብሮሹር ተጠቅመው አውቶብስ ፌርማታ ጋ አንድ ሰው ሲያነጋግሩ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ጽሑፍ በአገልግሎት ላይ ተጠቀሙበት

መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናበት አዲስ ብሮሹርና መጽሐፍ በማግኘታችን በጣም ተደስተናል! ይሖዋ፣ ተጨማሪ ደቀ መዛሙርት ለማፍራት የምናደርገውን ጥረት እንዲባርክልን እንጸልያለን። (ማቴ 28:18-20፤ 1ቆሮ 3:6-9) እነዚህን አዳዲስ መሣሪያዎች የምንጠቀምባቸው እንዴት ነው?

ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለው አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ፣ አዲስ ዓይነት የማስተማር ስልት የሚከተል ነው፤ በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት ስትዘጋጁም ሆነ ጥናቱን ስትመሩ እነዚህን መሠረታዊ መመሪያዎች ተከተሉ።a

  • ሐሳቡን አንብቡና በጥያቄዎቹ ላይ ተወያዩ

  • “አንብብ” የሚሉትን ጥቅሶች አንብቡ፤ ከዚያም ተማሪው ጥቅሱ የተጠቀሰበትን ዓላማ እንዲያስተውል እርዱት

  • ቪዲዮዎቹን ተመልክታችሁ ተወያዩባቸው፤ ለውይይት የቀረቡ ጥያቄዎች ካሉ እነሱን ተጠቀሙ

  • አንዱን ምዕራፍ በአንድ የጥናት ክፍለ ጊዜ ለመሸፈን ጥረት አድርጉ

በአገልግሎት ላይ፣ ግለሰቡ ፍላጎት እንዳለውና እንደሌለው ለማወቅ በመጀመሪያ ብሮሹሩን አበርክቱ። (“በምንመሠክርበት ጊዜ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ማበርከት የምንችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) ብሮሹሩን አጥንታችሁ ከጨረሳችሁና ተማሪው ጥናቱን የመቀጠል ፍላጎት ካለው መጽሐፉን አበርክታችሁለት ከምዕራፍ 04 ጀምራችሁ ጥናታችሁን ቀጥሉ። ምን ያስተምረናል? ወይም በአምላክ ፍቅር ኑሩ የሚሉትን መጻሕፍት የሚያጠና ጥናት ካላችሁ ለዘላለም በደስታ ኑር! ወደተባለው መጽሐፍ እንዲዛወር አድርጉ፤ እንዲሁም ከየትኛው ምዕራፍ ቢጀምር የተሻለ እንደሆነ ወስኑ።

እነዚሁ ባልና ሚስት “ለዘላለም በደስታ ኑር!” በተባለው ብሮሹር ሰውየውን ቤቱ ውስጥ ሲያስጠኑ።

ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራምህ እንኳን ደህና መጣህ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ጥናቶች አዲሱን መጽሐፍ በማጥናት ምን ትምህርት ያገኛሉ?

  • ይህን ቪዲዮ ለአዲስ ጥናቶች ማሳየት ያለባችሁ ለምንድን ነው?

  • ተማሪው ደረጃ በደረጃ የትኞቹን ግቦች እንዲያወጣና የትኞቹ ግቦች ላይ እንዲደርስ ልታበረታቱት ትችላላችሁ?—“የእያንዳንዱ ክፍል ፍሬ ሐሳብና ግብ” የሚለውን ሠንጠረዥ ተመልከት

a ማሳሰቢያ፦ “ምርምር አድርግ” የሚለውን ክፍል በጥናቱ ወቅት መሸፈን ለምርጫ የተተወ ቢሆንም፣ በምትዘጋጁበት ጊዜ የተጠቀሱትን ቪዲዮዎች ለመመልከትና ርዕሶቹን ለማንበብ ጊዜ መመደብ ይኖርባችኋል። እንዲህ ማድረጋችሁ፣ ጥናታችሁ ካለበት ሁኔታ አንጻር የሚጠቅመው ሐሳብ ለማግኘት ይረዳችኋል። በኤሌክትሮኒክ ፎርማት የተዘጋጀው ጽሑፍ ላይ ቪዲዮዎቹና ርዕሶቹ ሊንክ ተደርጎላቸዋል።

የእያንዳንዱ ክፍል ፍሬ ሐሳብና ግብ

 

ምዕራፍ

ፍሬ ሐሳብ

የተማሪው ግብ

1

01-12

መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ የሚጠቅምህ እንዴት እንደሆነና መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈውን አምላክ ማወቅ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተማር

ተማሪው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነብ፣ ለጥናቱ እንዲዘጋጅና በስብሰባዎች ላይ መገኘት እንዲጀምር አበረታታ

2

13-33

አምላክ ለእኛ ሲል ያደረጋቸውን ነገሮችና እሱን የሚያስደስተው ምን ዓይነት አምልኮ እንደሆነ ተማር

ተማሪው እውነትን ለሌሎች እንዲናገርና አስፋፊ እንዲሆን አነሳሳው

3

34-47

አምላክ ከአገልጋዮቹ ምን እንደሚጠብቅ ተማር

ተማሪው ራሱን ለይሖዋ እንዲወስንና እንዲጠመቅ አነሳሳው

4

48-60

ከአምላክ ፍቅር ሳትወጣ መኖር የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተማር

ተማሪው ትክክልና ስህተት የሆነውን እንዲለይ እንዲሁም መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርግ አሠልጥነው

በምንመሠክርበት ጊዜ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ማበርከት የምንችለው እንዴት ነው?

ልክ እንደ ትራክቶቻችን፣ ይህ ብሮሹርም ጀርባው ላይ ትኩረት የሚስብ ጥያቄ ይዟል። እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦

  • ጥያቄውን ጠይቃችሁ የቀረቡትን አማራጭ መልሶች አስመርጡት

  • መዝሙር 37:29 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ አንብቡለት

  • “ይህን ማወቅህ ለአንተ ምን ጥቅም አለው?” በሚለው ሥር ያሉትን ነጥቦች አወያዩት። ጊዜ ካላችሁ፣ ጥቅሶቹን አንብቡ እንዲሁም በሥዕላዊ መግለጫዎቹ ተጠቅማችሁ አብራሩለት

  • “መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው ተስፋ ላይ እምነት መጣል እንችላለን?” የሚለውን ጥያቄ መልስ ማወቅ ይፈልግ እንደሆነ ጠይቁት፤ ከዚያም በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ውይይት ጀምሩ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ