የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 ግንቦት ገጽ 3
  • ለራሳችሁ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ይኑራችሁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለራሳችሁ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ይኑራችሁ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • የማታውቋቸው ነገሮች እንዳሉ አምናችሁ በመቀበል ልካችሁን እንደምታውቁ አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ይሖዋ እንደሚወድህ አምነህ ተቀበል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ይሖዋ “የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይጠግናል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 ግንቦት ገጽ 3

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለራሳችሁ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ይኑራችሁ

“ይሖዋ በሕዝቡ ደስ ይሰኛል።” (መዝ 149:4) ፍጹማን ባንሆንም እንኳ መልካም ባሕርያችንን እና ችሎታችንን ይመለከታል። ይሁንና አንዳንድ ጊዜ ለራሳችን እንዲህ ያለ ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ ሊከብደን ይችላል። ሰዎች እኛን የሚይዙበት መንገድ ለራሳችን ዝቅተኛ አመለካከት እንዲኖረን ሊያደርግ ይችላል። ወይም ደግሞ ቀደም ሲል በሠራናቸው ስህተቶች የተነሳ ይሖዋ በእርግጥ የሚወደን መሆኑን ልንጠራጠር እንችላለን። እንዲህ ዓይነት ስሜት ሲሰማን ምን ሊረዳን ይችላል?

ይሖዋ የሚያየው ሰው በሚያይበት መንገድ እንዳልሆነ አስታውሱ። (1ሳሙ 16:7) ይህም ሲባል ይሖዋ የሚያየን እኛ ራሳችንን በምናይበት መንገድ አይደለም ማለት ነው። ደስ የሚለው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ ለእኛ ያለውን አመለካከት እንድናስተውል ይረዳናል። ይሖዋ አገልጋዮቹን ምን ያህል እንደሚወዳቸው የሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና ዘገባዎችን በመመርመር የይሖዋን አመለካከት መረዳት እንችላለን።

ልባችሁ በይሖዋ ፊት እንዲረጋጋ አድርጉ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ስለ አንድ ሯጭና ስለ አባቱ ከሚገልጸው ምሳሌ ይሖዋ ለእኛ ስላለው አመለካከት ምን እንማራለን?

  • ከባድ ኃጢአት የፈጸመ ሰው ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና ለማደስ አስፈላጊውን እርምጃ ከወሰደ ልቡ በይሖዋ ፊት እንዲረጋጋ ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው?—1ዮሐ 3:19, 20

  • ወንድም ስለ ዳዊትና ስለ ኢዮሳፍጥ የሚገልጹትን ዘገባዎች ማንበቡና በዚያ ላይ ማሰላሰሉ የጠቀመው እንዴት ነው?

ከሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች የምናገኛቸው ትምህርቶች

ሌሎች ለእኛ ያላቸው አመለካከት ምንም ይሁን ምን ይሖዋ ይወደናል

  • ሄኖክ (ዘፍ 5:24፤ ዕብ 11:5፤ ይሁዳ 14, 15)

  • ሐና (1ሳሙ 1:1–2:11, 18-21, 26)

ይሖዋ ንስሐ የገቡ ኃጢአተኞችን ሙሉ በሙሉ ይቅር ይላል

  • ምናሴ (2ዜና 33:1-7, 12, 13)

  • ጳውሎስ (1ጢሞ 1:12-16)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ