የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 1 ገጽ 8-9
  • አምላክ አንዳንድ ጸሎቶችን የማይሰማው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ አንዳንድ ጸሎቶችን የማይሰማው ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በጸሎት እርዳታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • መልስ የሚያገኙት የእነማን ጸሎቶች ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 1 ገጽ 8-9

አምላክ አንዳንድ ጸሎቶችን የማይሰማው ለምንድን ነው?

በሰማይ ያለው አባታችንና አምላካችን ይሖዋ ከልብ በመነጨ ስሜት የምናቀርበውን ጸሎት ለመስማት ፈቃደኛ ነው፤ በተጨማሪም የእኛን ጸሎት መስማት ያስደስተዋል። ሆኖም ለጸሎታችን መልስ የማይሰጥባቸው አንዳንድ ምክንያቶች አሉ። እነዚህ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? በምንጸልይበት ጊዜስ ምን ነገር ልናስታውስ ይገባል? ከዚህ ቀጥሎ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ቀርበዋል።

ቤተ ክርስቲያን ሄደው ከጸሎት መጽሐፍ ላይ ጸሎት እየደገሙ ያሉ ሰዎች

“በምትጸልዩበት ጊዜ . . . አንድ ዓይነት ነገር ደጋግማችሁ አታነብንቡ።”—ማቴዎስ 6:7

ይሖዋ የተሸመደዱ ጸሎቶችን እንድንደጋግም ወይም ከጸሎት መጽሐፍ ላይ እያነበብን እንድንጸልይ አይፈልግም። ከዚህ ይልቅ የልባችንን አውጥተን እንድንነግረው ይፈልጋል። ነጋ ጠባ አንድ ዓይነት ነገር የሚደጋግም ጓደኛ ቢኖርህ ምን ያህል አሰልቺ እንደሚሆንብህ አስበው። ጥሩ ጓደኞች እውነተኛ ስሜታቸውን በግልጽ ይናገራሉ። በራሳችን ቃላት ተጠቅመን መጸለያችን በሰማይ ያለውን አባታችንን እንደ ጓደኛ እንደምንቀርበው ያሳያል።

የሎተሪ ቲኬት እየፋቀ ወደ ላይ የሚመለከት ሰው

“በምትጠይቁበት ጊዜም አታገኙም፤ ምክንያቱም የምትጠይቁት ለተሳሳተ ዓላማ . . . ነው።”—ያዕቆብ 4:3

አምላክ እንድናደርግ ወይም እንዲኖረን የማይፈልጋቸውን ነገሮች እየጠየቅን ለጸሎታችን መልስ እናገኛለን ብለን መጠበቅ የለብንም። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋ ስግብግብነትንና በዕድል ማመንን በግልጽ አውግዟል። ታዲያ አንድ ቁማርተኛ ዕድል እንዲቀናው ያቀረበውን ጸሎት ሊሰማው ይችላል? (ኢሳይያስ 65:11፤ ሉቃስ 12:15) ይሖዋ እንዲህ ያሉ ጸሎቶችን ይሰማል ብሎ መጠበቅ ምክንያታዊነት የጎደለው ነው! አምላክ ጸሎታችንን እንዲሰማ ከፈለግን፣ የምናቀርበው ጥያቄ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኘው የአምላክ ትእዛዝ ጋር የሚስማማ መሆን አለበት።

ለወታደሮች እየጸለየ ያለ ቄስ

“ሕግን ለመስማት አሻፈረኝ የሚል ሰው፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።”—ምሳሌ 28:9

በጥንት ዘመን አምላክ የጽድቅ ሕጎቹን የሚጥሱ ሰዎች ለሚያቀርቡት ጸሎት መልስ አይሰጥም ነበር። (ኢሳይያስ 1:15, 16) ዛሬም ቢሆን አመለካከቱ አልተለወጠም። (ሚልክያስ 3:6) አምላክ ጸሎታችንን እንዲሰማ ከፈለግን የእሱን ሕጎች ለመታዘዝ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን። ሆኖም ከዚህ በፊት አንዳንድ ስህተቶችን ሠርተን የነበረ ቢሆንስ? ይሖዋ ጸሎታችንን ጨርሶ አይሰማም ማለት ነው? በፍጹም! አካሄዳችንን ለማስተካከልና እሱን ለማስደሰት አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ የምናደርግ ከሆነ አምላክ በፍቅር ተነሳስቶ ይቅር ይለናል።—የሐዋርያት ሥራ 3:19

“ወደ አምላክ የሚቀርብ ሁሉ እሱ መኖሩንና ከልብ ለሚፈልጉትም ወሮታ ከፋይ መሆኑን ማመን ይኖርበታል።”—ዕብራውያን 11:6

መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበች ያለች ሴት

ጸሎት ጭንቀት ውስጥ ስንገባ ተንፈስ ለማለት ብቻ የምንጠቀምበት አማራጭ አይደለም። ከዚህ ይልቅ እምነታችንን የምናሳይበት የአምልኳችን ክፍል ነው። ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ ‘በእምነት መለመናችንን ካልቀጠልን ከይሖዋ አንዳች ነገር አገኛለሁ ብለን መጠበቅ እንደሌለብን’ ተናግሯል። (ያዕቆብ 1:6, 7) በአምላክ ላይ እምነት ለመገንባት ጊዜ መድበን መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ስለ እሱ ለማወቅ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። እንዲህ ማድረጋችን የአምላክን ፈቃድ እንድናውቅና እንደሚሰማን ተማምነን እንድንጸልይ ይረዳናል።

ተስፋ አትቁረጥ!

አምላክ ለአንዳንድ ጸሎቶች መልስ ባይሰጥም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከልብ በመነጨ ስሜት የሚያቀርቡትን ጸሎት ሰምቶ መልስ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን የሚያስደስት ጸሎት ለማቅረብ ምን ማድረግ እንዳለብህ ይገልጻል። ቀጣዩ ርዕስ ይህን ያብራራል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ