የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp22 ቁጥር 1 ገጽ 10-11
  • 3 | ጥላቻን ከአእምሮህ ነቅለህ አውጣ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 3 | ጥላቻን ከአእምሮህ ነቅለህ አውጣ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦
  • ምን ማለት ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ‘ጸጋና ኃይል የተሞላው እስጢፋኖስ’
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወገረ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ጥላቻን ድል ማድረግ እንችላለን!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
wp22 ቁጥር 1 ገጽ 10-11
አንድ ሰው ሌላ ዘር ካለው ሰው ጋር ሲጨባበጥ በዓይነ ሕሊናው ሲያይ። የሰዎቹ ጥላ መፈክር ይዘው ሲጨቃጨቁ ያሳያል።

የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?

3 | ጥላቻን ከአእምሮህ ነቅለህ አውጣ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

“ጥሩ የሆነውን፣ ተቀባይነት ያለውንና ፍጹም የሆነውን የአምላክ ፈቃድ መርምራችሁ ማረጋገጥ ትችሉ ዘንድ አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ።”—ሮም 12:2

ምን ማለት ነው?

አምላክ የምናስብበት መንገድ ያሳስበዋል። (ኤርምያስ 17:10) ጥላቻ የሚንጸባረቅበት ነገር መናገር ወይም ማድረግ እንደሌለብን ግልጽ ነው፤ ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም። የጥላቻ ሰንሰለት የሚጀምረው በአእምሮና በልብ ውስጥ ነው። ስለዚህ ጥላቻን ከአስተሳሰባችንም ሆነ ከስሜታችን ነቅለን ማውጣት ይኖርብናል። እውነተኛ ‘ለውጥ’ ማድረግና የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የምንችለው እንዲህ ካደረግን ብቻ ነው።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ስለ ሌሎች፣ በተለይም ሌላ ዘር ወይም ዜግነት ስላላቸው ሰዎች ያለህን አመለካከትና ስሜት በሐቀኝነት መርምር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘ስለ እነሱ ምን አመለካከት አለኝ? አመለካከቴ የተመሠረተው ስለ እነሱ በትክክል በማውቀው ነገር ላይ ነው? ወይስ በብዙኃኑ አመለካከት ላይ?’ ጥላቻንና ዓመፅን ከሚያንጸባርቁ ማኅበራዊ ሚዲያዎች፣ ፊልሞችና መዝናኛዎች ራቅ።

የአምላክ ቃል ጥላቻን ከልባችንና ከአእምሯችን ለማስወገድ ይረዳናል

የራሳችንን አስተሳሰብና ስሜት ሚዛናዊ ሆነን መገምገም ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ሆኖም የአምላክ ቃል ‘የልባችንን ሐሳብና ዓላማ ለመረዳት’ ያስችለናል። (ዕብራውያን 4:12) ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህን ቀጥል። አስተሳሰብህን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች አንጻር ገምግም፤ እንዲሁም አስተሳሰብህን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ጋር ለማስማማት የቻልከውን ሁሉ ጥረት አድርግ። የአምላክ ቃል በአእምሯችንና በልባችን ውስጥ ‘የተመሸገውን’ ጥላቻ ለማስወገድ ይረዳናል።—2 ቆሮንቶስ 10:4, 5

እውነተኛ ታሪክ—ስቲቨን

አስተሳሰቡን ቀይሯል

ስቲቨን።

ስቲቨንና ቤተሰቡ በነጮች በደል ደርሶባቸው ነበር። በመሆኑም ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የዓመፅ እርምጃዎችን የሚወስድ አንድ የፖለቲካ ቡድን ትኩረቱን ሳበው። በኋላ ላይ እሱም በጥላቻ ወንጀሎች መካፈል ጀመረ። ስቲቨን እንዲህ ብሏል፦ “በአንድ ወቅት እኔና ጓደኞቼ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በአፍሪካውያን ባሮች ላይ ይፈጸም ስለነበረው ግፍ የሚያሳዩ ፊልሞች ተመለከትን። በፊልሙ ላይ ባየነው ግፍ ስለተበሳጨን እዚያው ፊልም ቤት ውስጥ የነበሩትን ነጭ ወጣቶች መደብደብ ጀመርን። ከዚያም ሌሎች ነጮችን ለመደብደብ እነሱ ወደሚኖሩበት ሰፈር ሄድን።”

ስቲቨን መጽሐፍ ቅዱስን ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ማጥናት ሲጀምር አመለካከቱ በእጅጉ ተቀየረ። ስቲቨን የዘር ጥላቻ ሰለባ ስለነበር በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ያየው ነገር በጣም እንዳስገረመው ገልጿል። እንዲህ ብሏል፦ “ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ነጭ የይሖዋ ምሥክር ወደ ውጭ አገር ሲሄድ ልጆቹን እንዲጠብቁለት አደራ የሰጠው ለአንድ ጥቁር ቤተሰብ ነበር። እንዲሁም አንድ ነጭ ቤተሰብ መኖሪያ የሌለውን አንድ ጥቁር ወጣት ከእነሱ ጋር እንዲኖር አድርገዋል።” ስቲቨን የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር እንደሚያሳዩ ተገነዘበ፤ በመሆኑም ኢየሱስ በተናገረው መሠረት በፍቅራቸው የሚታወቁት እውነተኛ ክርስቲያኖች እነሱ እንደሆኑ ተረዳ።—ዮሐንስ 13:35

ስቲቨን ጥላቻውንና ዓመፁን እንዲተው የረዳው ምንድን ነው? ሮም 12:2 ረድቶታል። እንዲህ ብሏል፦ “አስተሳሰቤን መለወጥ እንደሚያስፈልገኝ ተገነዘብኩ። አስተሳሰቤን የለወጥኩት እንዲሁ ሰላማዊ መሆን ስላለብኝ ብቻ ሳይሆን ከሁሉ የተሻለው የሕይወት መንገድ ይህ መሆኑንም ስለተገነዘብኩ ነው።” ስቲቨን ከ40 ለሚበልጡ ዓመታት ከጥላቻ የጸዳ ሕይወት ሲመራ ቆይቷል።

የስቲቨን ታሪክ በሐምሌ 1, 2015 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 10-11 ላይ ወጥቷል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ