ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 1-10
ከይሖዋ ጋር ሰላም እንዲኖረን ልጁን ኢየሱስን ልናከብር ይገባል
ብሔራት የይሖዋና የኢየሱስ ጠላት እንደሚሆኑ በትንቢት ተነግሯል
ብሔራት የኢየሱስን ሥልጣን ከመቀበል ይልቅ የራሳቸውን ሥልጣን የሙጥኝ እንደሚሉ በትንቢት ተነግሯል
ይህ ትንቢት ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ፍጻሜውን አግኝቶ ነበር፤ በዘመናችን ደግሞ የላቀ ፍጻሜ አለው
መዝሙራዊው፣ ብሔራት ከንቱ ነገር እንደሚያጉተመትሙ ይናገራል፤ ይህም ዓላማቸው እንደማይሳካና ውድቅ መሆኑ እንደማይቀር ያሳያል
ሕይወት የሚያገኙት ይሖዋ ለቀባው ንጉሥ አክብሮት ያላቸው ብቻ ናቸው
መሲሐዊውን ንጉሥ የሚቃወሙ ሁሉ ይጠፋሉ
የአምላክ ልጅ የሆነውን ኢየሱስን የሚያከብሩ ሰዎች ደኅንነትና ሰላም ያገኛሉ