የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 11—1 ነገሥት
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 7
    • 25 በአንደኛ ነገሥት ውስጥ የተነገሩት ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ማግኘታቸው የይሖዋን ትንቢት የመናገር ችሎታ በግልጽ የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ ያህል ኢዮርብዓም በቤቴል የገነባውን መሠዊያ የሚያፈራርሰው ኢዮስያስ እንደሚሆን 300 ከሚበልጡ ዓመታት ቀደም ብሎ የተነገረ አንድ አስደናቂ ትንቢት አለ። ልክ እንደተባለውም ኢዮስያስ ትንቢቱን ፈጽሟል! (1 ነገ. 13:​1-3፤ 2 ነገ. 23:​15) ይሁን እንጂ ከሁሉ ይበልጥ ጉልህ ሥፍራ የሚሰጣቸው ሰሎሞን ከሠራው ከይሖዋ ቤት ጋር በተያያዘ የተነገሩት ትንቢቶች ናቸው። ይሖዋ ወደ ሃሰት አማልክት ዞር ካሉ እስራኤላውያንን ከምድር እንደሚያጠፋቸውና ለስሙ የቀደሰውንም ቤት እንደሚተወው ለሰሎሞን ነግሮታል። (1 ነገ. 9:​7, 8) ይህ ትንቢት ምንም ዝንፍ ሳይል ሙሉ በሙሉ ፍጻሜውን ማግኘቱን 2 ዜና መዋዕል 36:​17-21 ላይ እናነባለን። ከዚህም በላይ ታላቁ ሄሮድስ በዚያው ቦታ ላይ የሠራው ኋለኛው ቤተ መቅደስ በተመሳሳይ ምክንያት ተመሳሳይ ዕጣ እንደሚገጥመው ኢየሱስ ተናግሯል። (ሉቃስ 21:​6) ይህም ቢሆን ፍጻሜውን አግኝቷል! እነዚህን መቅሰፍቶችና መቅሰፍቶቹ የደረሱበትን ምክንያት ማስታወስ ይኖርብናል። በእውነተኛው አምላክ መንገዶችም ሁልጊዜ መጓዝ እንዳለብን ሊያስታውሱን ይገባል።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 33—ሚክያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • 4 የሚክያስ መጽሐፍ ትክክለኛ መሆኑን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። አይሁዳውያን የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል መሆኑን ተጠራጥረው አያውቁም። ኤርምያስ 26:18, 19 የሚክያስን ቃላት በቀጥታ በመጥቀስ “ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች” ይላል። (ሚክ. 3:12) በ607 ከክርስቶስ ልደት በፊት የባቢሎን ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ድምጥማጧን ‘ባጠፋት’ ጊዜ ይህ ትንቢት በትክክል ተፈጽሟል። (2 ዜና 36:19) በተመሳሳይም ሰማርያ “የፍርስራሽ ክምር” እንደምትሆን የተነገረው ትንቢት ተፈጽሟል። (ሚክ. 1:6, 7) አሦራውያን በ740 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሰማርያን አጥፍተው የሰሜኑን የእስራኤል መንግሥት በግዞት ወስደዋል። (2 ነገ. 17:5, 6) ቆየት ብሎም በአራተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ሰማርያ በታላቁ እስክንድር የተወረረች ሲሆን በሁለተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በቀዳማዊ ጆን ሂርካነስ መሪነት አይሁዳውያን ወርረው አውድመዋታል። ዘ ኒው ዌስትሚኒስተር ዲክሽነሪ ኦቭ ዘ ባይብል፣ 1970 በገጽ 822 ላይ ሰማርያ ለመጨረሻ ጊዜ ስለጠፋችበት ሁኔታ ሲናገር “ድል አድራጊዎቹ በዚያ ኮረብታ ላይ የተመሸገ ከተማ እንደነበረ የሚያሳይ አንዳች ማስረጃ እንዳይቀር በማሰብ አውድመዋታል” ይላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ