የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 183
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጓደኝነት ምን ይላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጓደኝነት ምን ይላል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ጥሩ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ጥሩ ጓደኛሞች እነማን ናቸው?
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል?
  • ፍቅር በጠፋበት ዓለም ውስጥ ወዳጅነትን ጠብቆ መኖር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ጓደኞቼ የሚተዉኝ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—1997
  • ምሳሌ 17:17—“ወዳጅ ምንጊዜም ወዳጅ ነው”
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • ዘላቂ ወዳጅነት መመሥረት ትችላለህ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 183
በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ጓደኛሞች በእሳት ዙሪያ ተቀምጠው። አንዱ የሙዚቃ መሣሪያ ይጫወታል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጓደኝነት ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ጓደኝነት በሕይወታችን ደስተኛና ስኬታማ እንድንሆን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይችላል። ጥሩ ጓደኞች በጎ ተጽዕኖ ያሳድሩብናል፤ እንዲሁም የተሻልን ሰዎች እንድንሆን ይረዱናል።—ምሳሌ 27:17

እርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ጓደኞቻችንን በጥንቃቄ መምረጣችን አስፈላጊ መሆኑን ጎላ አድርጎ ይገልጻል። መጥፎ ጓደኞች መያዝ ለችግር ሊዳርግ እንደሚችል ያስጠነቅቃል። (ምሳሌ 13:20፤ 1 ቆሮንቶስ 15:33) እንዲህ ያሉት ጓደኞች የሞኝነት አካሄድ እንድንከተል ሊያደርጉን ወይም መልካም ባሕርያታችንን ሊያበላሹብን ይችላሉ።

በዚህ ርዕስ ውስጥ

  • ጥሩ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ጥሩ ጓደኛሞች እነማን ናቸው?

  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል?

  • ስለ ጓደኝነት የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ጥሩ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?

ሁለት ሰዎች፣ የሚወዷቸው ወይም የሚያስደስቷቸው ነገሮች ተመሳሳይ መሆናቸው ብቻውን ለጥሩ ጓደኝነት መሠረት እንደማይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ለምሳሌ ያህል፣ መዝሙር 119:63 “አንተንa ለሚፈሩ ሁሉ፣ መመሪያዎችህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ” ይላል። የዚህ ጥቅስ ጸሐፊ ጓደኛ አድርጎ የመረጠው አምላክን ላለማሳዘን የሚፈሩና በአምላክ መሥፈርቶች የመመራት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች እንደሆነ ልብ እንበል።

መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ጓደኛ ሊኖሩት የሚገቡትን ባሕርያትም ይጠቅሳል። ለምሳሌ፦

  • “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”—ምሳሌ 17:17

  • “እርስ በርስ ከመጠፋፋት ወደኋላ የማይሉ ጓደኛሞች አሉ፤ ነገር ግን ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ አለ።”—ምሳሌ 18:24

እነዚህ ጥቅሶች እንደሚገልጹት ጥሩ ጓደኛ ታማኝ፣ አፍቃሪ፣ ደግ እና ለጋስ ነው። እውነተኛ ጓደኛ በሕይወታችን ውስጥ ውጣ ውረዶች ሲያጋጥሙን እንደሚረዳን የምንተማመንበት ሰው ነው። በተጨማሪም እውነተኛ ጓደኛ በተሳሳተ ጎዳና እየሄድን እንደሆነ ወይም መጥፎ ውሳኔ ልናደርግ እንደሆነ ካስተዋለ በድፍረት ከመናገር ወደኋላ አይልም።—ምሳሌ 27:6, 9

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ጥሩ ጓደኛሞች እነማን ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ ዕድሜ፣ አስተዳደግ፣ ባሕል እና ሥልጣን ቢኖራቸውም ጥሩ ጓደኝነት መመሥረት ስለቻሉ ሰዎች ይናገራል። ሦስት ምሳሌዎችን እስቲ እንመልከት።

  • ሩት እና ናኦሚ። ሩት የናኦሚ ምራት ነበረች፤ በመካከላቸው ሰፊ የዕድሜ ልዩነት ሳይኖር አይቀርም። በተጨማሪም ሩትና ናኦሚ ባሕላቸው በጣም የተለያየ ነበር። እነዚህ ልዩነቶች ቢኖሩም በጣም የሚዋደዱና የሚቀራረቡ ጓደኛሞች ሆነዋል።—ሩት 1:16

  • ዳዊት እና ዮናታን። ዮናታን ዳዊትን በ30 ዓመት ገደማ ሳይበልጠው አይቀርም፤ ያም ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስ “ዮናታንና ዳዊት የጠበቀ ወዳጅነት መሠረቱ” ይላል።—1 ሳሙኤል 18:1

  • ኢየሱስ እና ሐዋርያቱ። ኢየሱስ መምህር እና ጌታ እንደመሆኑ መጠን ለሐዋርያቱ የበላያቸው ነበር። (ዮሐንስ 13:13) ሆኖም የእሱ ጓደኞች ለመሆን እንደማይበቁ አድርጎ አልተመለከታቸውም። ከዚህ ይልቅ ትምህርቶቹን ከሚከተሉ ሰዎች ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ነበረው። “ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ ስላሳወቅኳችሁ ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ” ብሏል።—ዮሐንስ 15:14, 15

የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል?

አዎ፣ ሰዎች የአምላክ ወዳጅ መሆን ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ‘አምላክ ከቅኖች ጋር የጠበቀ ወዳጅነት አለው’ ይላል። (ምሳሌ 3:32) ይህም ሲባል አምላክ፣ ሥርዓታማና ሐቀኛ ለመሆን እንዲሁም ትክክል ወይም ስህተት የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ የእሱን መሥፈርቶች ለመከተል ከሚጥሩ ሰዎች ጋር ወዳጅነት ይመሠርታል ማለት ነው። ለምሳሌ ታማኝ ሰው የነበረው አብርሃም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘የአምላክ ወዳጅ’ ተብሎ ተጠርቷል።—2 ዜና መዋዕል 20:7፤ ኢሳይያስ 41:8፤ ያዕቆብ 2:23

a የዚህ መዝሙር አውድ እንደሚያሳየው በዚህ ጥቅስ ላይ “አንተ” የሚለው የሚያመለክተው አምላክን ነው።

ስለ ጓደኝነት የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

መዝሙር 119:63፦ “አንተን ለሚፈሩ ሁሉ፣ መመሪያዎችህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።”

ትርጉሙ፦ ጓደኛ አድርገን ልንመርጥ የሚገባው እንደ እኛ በአምላክ የሚያምኑና የእሱን መሥፈርቶች የሚከተሉ ሰዎችን ነው።

ምሳሌ 3:32፦ “ይሖዋb ተንኮለኛን ሰው ይጸየፋልና፤ ከቅኖች ጋር ግን የጠበቀ ወዳጅነት አለው።”

ትርጉሙ፦ የአምላክ ወዳጅ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ሐቀኞችና ጥሩ ሥነ ምግባር ያላቸው መሆን አለባቸው።

ምሳሌ 13:20፦ “ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል፤ ከሞኞች ጋር የሚገጥም ግን ጉዳት ይደርስበታል።”

ትርጉሙ፦ ጓደኞቻችን አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድሩብናል።

ምሳሌ 17:17፦ “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”

ትርጉሙ፦ እውነተኛ ጓደኞች በክፉውም በደጉም ጊዜ ይደጋገፋሉ።

ምሳሌ 18:24፦ “እርስ በርስ ከመጠፋፋት ወደኋላ የማይሉ ጓደኛሞች አሉ፤ ነገር ግን ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ አለ።”

ትርጉሙ፦ እውነተኛ ጓደኛ ሌሎችን መጠቀሚያ አያደርግም። ከዚህ ይልቅ ታማኝ፣ እምነት የሚጣልበትና አፍቃሪ ነው።

ምሳሌ 27:6፦ “የወዳጅ ማቁሰል ከታማኝነት የሚመነጭ ነው።”

ትርጉሙ፦ ጥሩ ጓደኛ፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ እርማት ከመስጠት ወደኋላ አይልም።

ምሳሌ 27:17፦ “ብረት ብረትን እንደሚስል ሁሉ ሰውም ጓደኛውን ይስለዋል።”

ትርጉሙ፦ ጥሩ ጓደኞች የተሻልን ሰዎች እንድንሆን ይረዱናል።

b መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ ስም ይሖዋ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ