የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 4/15 ገጽ 32
  • ከዕንቁ ይበልጥ ትወደዳለች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዕንቁ ይበልጥ ትወደዳለች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 4/15 ገጽ 32

ከዕንቁ ይበልጥ ትወደዳለች

ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄድ ጎብኚዎች እንዲህ ባሉት ከቀይ ባሕር ውኃ ሥር በሚታዩት ነገሮች በጣም ይደሰታሉ።

ቁጥር ሥፍር የሌላቸው በሕብረቀለማት ያሸበረቁ ዓሦች ጥርት ባለው ውኃ ውስጥ የሚዋኙትን ዋናተኞች ያፈዝዟቸዋል። ደማቅ ቀለም ያላቸውን ዕንቁዎች ጨምሮ እዚህ ላይ በሚታየው ባለቀለም ዓሣ ዙሪያ ያሉትን ለዓይን የሚማርኩ ሌሎች በባሕር ውስጥ ያሉ ድንቅ ነገሮችም ተመልከት።

የሚያማምሩት ዕንቁዎች ብዙ ዓይነት ቅርጽና ቀለም አላቸው። እጹብ ድንቅ የሚባሉት እንቁዎች በጥንት ዘመን እንኳን ከፍተኛ ዋጋ ያወጡ እንደነበረ መገመት ትችላለህ። ቅርጻ ቅርጽ የሚሠሩ ሙያተኞች ቆንጆ ቆንጆ ጌጣ ጌጦችን ይሠሩባቸው ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችም ዕንቁዎችን ከወርቅ፣ ከብርና ከቀይ ዕንቁ ጋር ጠቅሰዋቸዋል። (ምሳሌ 3:14, 15፤ ሕዝቅኤል 27:16) ሆኖም ጸሐፊዎቹ ከዕንቁዎች ውበትና ዋጋ የሚበልጠውን ነገር እንድናስተውል ይረዱናል።

አንዳንድ ነገሮች ከዕንቁ ይበልጥ በጣም ውድ ስለሆኑ የራሳችን አድርገን ይበልጥ በጥንቃቄ ልንጠብቃቸው እንደሚገባን አጉልተው ገልጸዋል። ጥሩና ባለሞያ ሚስት ከነዚህ አንዷ ነች። እንዲህ እናነባለን፦ “ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ እጅግ ይበልጣል።” (ምሳሌ 31:10) ባለ ትዳር ነህን? እንግዲያው እዚህ ላይ የሚታዩትን ውብ ዕንቁዎች እንደገና ተመልከታቸውና ሚስቴን የሚገባትን ያህል አደንቃታለሁ ወይ ብለህ አስብ።

ወንድም ሆንን ሴት፣ ባለትዳርም ሆንን ነጠላ ግሩም ድንቅ የሆኑ ዕንቁዎችን መመልከት አምላካዊ ጥበብ፣ ማስተዋልና እውቀት ከዚህ ይበልጥ ዋጋ ያላቸው መሆናቸውን እንድንገነዘብ ይረዳናል። የአምላክ ቃል እንዲህ ይላል፦ “ጥበብን የሚያገኝ ማስተዋልንም የሚያተርፍ ሰው [ደስተኛ ነው። አዓት] ምክንያቱም ከብር ከሚገኝ ጥቅም፣ ከጥበብ የሚገኝ ጥቅም ይበልጣል፤ ከወርቅ ከሚገኘውም ትርፍ ከጥበብ የሚገኝ ትርፍ ይሻላል። ጥበብ ከውድ ዕንቁ ትበልጣለች፣ አንተ ለማግኘት ከምትመኛቸው ነገሮች ሁሉ ከጥበብ ጋር የሚወዳደር አንድ እንኳ የለም።”—ምሳሌ 3:13–15 የ1980 ትርጉም ፤ 8:11

ስለዚህ በምንዋኝበትም ጊዜ ይሁን በፎቶግራፍ ስንመለከታቸው በቀይ ባሕር ውስጥ ያሉት ዕንቁዎች ውበትንና ልናሰላስልበት የሚገባንን ጠቃሚ ነገር ሊያስታውሱን ይገባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ