-
የቱ እንደሚያፈራ አታውቁም!መጠበቂያ ግንብ—2008 | ሐምሌ 15
-
-
የመረቡ ምሳሌ
15, 16. (ሀ) ስለ መረቡ የሚናገረውን ምሳሌ በአጭሩ ግለጽ። (ለ) መረቡ ምን ያመለክታል? ይህ ምሳሌ ለአምላክ መንግሥት ምሥራች ምላሽ ከሰጡት ሰዎች ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ የትኛውን ነጥብ በተዘዋዋሪ ይገልጻል?
15 የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ከሚፈልጉት ሰዎች ቁጥር መብዛት ይልቅ አስፈላጊ የሆነው ነገር እነዚህ ሰዎች እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆን አለመሆናቸው ነው። ለአምላክ መንግሥት ምሥራች ምላሽ ከሰጡት ሰዎች ቁጥር መጨመር ጋር የተያያዘውን ይህንን ነጥብ ኢየሱስ ስለ መረብ የሚገልጽ ሌላ ምሳሌ በተናገረበት ወቅት በተዘዋዋሪ ጠቅሷል። ኢየሱስ “ደግሞም መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር ተጥሎ የዓሣ ዓይነቶችን የያዘ መረብ ትመስላለች” ብሏል።—ማቴ. 13:47
16 የአምላክን መንግሥት የስብከት ሥራ የሚያመለክተው መረብ ሁሉንም የዓሣ ዓይነቶች ይዟል። ኢየሱስ በመቀጠል እንዲህ ብሏል:- “ዓሣ አጥማጆቹ መረቡ ሲሞላላቸው ጎትተው ወደ ባሕሩ ዳር አወጡት፤ ከዚያም ተቀምጠው ጥሩ ጥሩውን እየለዩ በቅርጫት ውስጥ ጨመሩ፤ መጥፎ መጥፎውን ግን ጣሉት። በዓለም መጨረሻም ልክ እንደዚሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኀጢአተኞችን ከጻድቃን በመለየት፣ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።”—ማቴ. 13:48-50
17. ስለ መረቡ በሚገልጸው ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው የመለየት ሥራ የሚከናወነው በየትኛው ጊዜ ውስጥ ነው?
17 ኢየሱስ በክብሩ በሚገኝበት ጊዜ በበጎችና በፍየሎች ላይ የመጨረሻ ፍርድ እንደሚበይን ተናግሮ ነበር፤ ታዲያ ከላይ የተገለጸው የመለየት ሥራ ይህንን የሚያመለክት ነው? (ማቴ. 25:31-33) አይደለም። ይህ የመጨረሻ ፍርድ የሚበየነው ኢየሱስ በታላቁ መከራ ወቅት ሲመጣ ነው። ከዚህ በተለየ መልኩ፣ ስለ መረቡ በሚገልጸው ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው የመለየት ሥራ የሚከናወነው ‘የዓለም መጨረሻ’ ወይም የዚህ ሥርዓት መደመደሚያ ተብሎ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ነው።b ይህ ደግሞ በታላቁ መከራ የሚደመደመውን የምንኖርበትን ዘመን ያመለክታል። ታዲያ በአሁኑ ጊዜ የመለየት ሥራ እየተከናወነ ያለው እንዴት ነው?
18, 19. (ሀ) በአሁኑ ጊዜ የመለየት ሥራ እየተከናወነ ያለው እንዴት ነው? (ለ) ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል? (በገጽ 21 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻም ተመልከት።)
18 በዘመናችን ከሰው ዘር ባሕር ውስጥ የወጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምሳሌያዊ ዓሣዎች ወደ ይሖዋ ድርጅት ምድራዊ ክፍል ቃል በቃል እየተሳቡ ነው። አንዳንዶች በመታሰቢያው በዓል ላይ ሌሎች ደግሞ በጉባኤ ስብሰባዎቻችን ላይ ይገኛሉ፤ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት እንኳ ፈቃደኞች ናቸው። ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው ማለት ይቻላል? ዓሣ አጥማጆቹ እነዚህን ሰዎች፣ ‘ወደ ባሕሩ ዳር አውጥተዋቸው’ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በቅርጫት ወደተመሰሉት የክርስቲያን ጉባኤዎች የሚሰበሰቡት ‘ጥሩዎቹ’ ብቻ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናግሯል። በመጥፎዎቹ ዓሣዎች የተመሰሉት ሰዎች የሚጣሉ ሲሆን በመጨረሻም፣ ወደፊት የሚመጣውን ጥፋት ወደሚያመለክተው ምሳሌያዊ እቶን እሳት ይወረወራሉ።
19 መጥፎ በመሆናቸው ምክንያት እንደተጣሉት ዓሣዎች ሁሉ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያጠኑ የነበሩ በርካታ ሰዎችም ማጥናታቸውን አቁመዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያን የሆኑ ወላጆች ያሏቸው አንዳንዶች የኢየሱስን ፈለግ ለመከተል እውነተኛ ፍላጎት የላቸውም። እነዚህ ግለሰቦች ይሖዋን ለማገልገል መወሰን አይፈልጉም፤ ሌሎቹ ደግሞ ለተወሰነ ጊዜ ይሖዋን ሲያገለግሉት ከቆዩ በኋላ እሱን ማገልገላቸውን አቁመዋል።c (ሕዝ. 33:32, 33) ይሁን እንጂ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ሁሉ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ከመምጣቱ በፊት በቅርጫት ወደተመሰሉት ጉባኤዎች መሰብሰባቸውና ጥበቃ በሚያገኙበት ቦታ መቆየታቸው በጣም አስፈላጊ ነው።
-
-
የቱ እንደሚያፈራ አታውቁም!መጠበቂያ ግንብ—2008 | ሐምሌ 15
-
-
20, 21. (ሀ) ኢየሱስ እድገት ማድረግን በተመለከተ የተናገራቸውን ምሳሌዎች በመመርመራችን ምን ትምህርት አግኝተናል? (ለ) አንተስ ምን ለማድረግ ቆርጠሃል?
20 ኢየሱስ እድገት ማድረግን በተመለከተ የተናገራቸውን ምሳሌዎች በአጭሩ በመመርመራችን ምን ትምህርት አግኝተናል? አንደኛ፣ የሰናፍጩ ዘር ካደረገው እድገት ጋር በሚመሳሰል መልኩ ለአምላክ መንግሥት ምሥራች ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል። የይሖዋ ሥራ እንዳይከናወን ሊያግደው የሚችል ምንም ነገር የለም! (ኢሳ. 54:17) ከዚህም በተጨማሪ በዛፉ ‘ጥላ ሥር ለመስፈር’ የፈለጉ ሁሉ መንፈሳዊ ጥበቃ አግኝተዋል። ሁለተኛው ትምህርት ደግሞ የሚያሳድገው አምላክ መሆኑ ነው። ዱቄት ውስጥ የተሸሸገው እርሾ ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ እንዳደረገው ሁሉ ከመንግሥቱ ሥራ ጋር በተያያዘ የተከናወነውን እድገትም ሁልጊዜ ማስተዋል ወይም መረዳት ባንችልም እድገቱ ግን እየተካሄደ ነው! ሦስተኛ፣ ለመንግሥቱ ምሥራች ምላሽ የሰጡ ሰዎች ሁሉ ጥሩ ዓሣዎች ናቸው ማለት አይደለም። አንዳንዶች በኢየሱስ ምሳሌ ላይ እንደተጠቀሱት መጥፎ ዓሣዎች ሆነዋል።
-
-
የቱ እንደሚያፈራ አታውቁም!መጠበቂያ ግንብ—2008 | ሐምሌ 15
-
-
b ማቴዎስ 13:39-43 ከመንግሥቱ ስብከት ሥራ ጋር በተያያዘ ስለ ሌላ ነጥብ የሚገልጽ ቢሆንም ይህ ምሳሌ የሚፈጸምበት ጊዜ ስለ መረቡ የተሰጠው ምሳሌ ከሚፈጸምበት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ሁለቱም ምሳሌዎች ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት ‘የዓለም መጨረሻ’ ወይም የዚህ ሥርዓት መደመደሚያ ተብሎ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ነው። የመዝራቱና መከሩን የመሰብሰቡ ሥራ የሥርዓቱ መደምደሚያ በተባለው ጊዜ ውስጥ ያለማቋረጥ እንደሚከናወን ሁሉ ምሳሌያዊውን ዓሣ የመለየቱ ሥራም ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው።—የጥቅምት 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25-26፤ እውነተኛውን አንድ አምላክ አምልክ ገጽ 178-181 አንቀጽ 8-11
-