-
“ይህ ሊሆን ግድ ነውና”መጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 1
-
-
በዘመኑ የሚኖሩት ሰዎች መከራውን ያያሉ
11. ኢየሱስ “ይህ ትውልድ” ብሎ ስለጠቀሰው የሰዎች ቡድን ምን ተናግሯል?
11 ብዙ አይሁዶች ቤተ መቅደሱን ማዕከል ያደረገው የአምልኮ ሥርዓታቸው ላልተወሰነ ጊዜ ይቀጥላል ብለው ያስቡ ነበር። ሆኖም ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ነበር:- “ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቊጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።”—ማቴዎስ 24:32-35 በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።
12, 13. ኢየሱስ “ይህ ትውልድ” ብሎ ሲጠቅስ ደቀ መዛሙርቱ እንዴት ተረድተውት ሊሆን ይችላል?
12 ከ66 እዘአ ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት ክርስቲያኖች ድርብ ተፈጻሚነት ያለውን የዚህን ምልክት የመጀመሪያ ፍጻሜ ማለትም ጦርነት፣ ረሃብና የመንግሥቱ ምሥራች በስፋት መሰበኩን ሳይቀር ተመልክተው ነበር። (ሥራ 11:28፤ ቆላስይስ 1:23) ይሁንና መጨረሻው የሚመጣው መቼ ነው? ኢየሱስ “ይህ ትውልድ [በግሪክኛ ዬኔአ] አያልፍም” ብሎ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር? ብዙውን ጊዜ ኢየሱስ ሃይማኖታዊ መሪዎችን ጨምሮ በዚያን ዘመን ይኖሩ የነበሩ አይሁዳውያን ተቃዋሚ ወገኖችን “ክፉና አመንዝራ ትውልድ” ብሎ ይጠራቸው ነበር። (ማቴዎስ 11:16፤ 12:39, 45፤ 16:4፤ 17:17፤ 23:36) ስለዚህ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በድጋሚ “ይህ ትውልድ” ሲል በታሪክ ዘመናት በሙሉ የነበረውን ጠቅላላውን የአይሁድ ብሔር ወይም “የተመረጠ ትውልድ” ተብለው የተጠሩትን ተከታዮቹን ማመልከቱ እንዳልሆነ የተረጋገጠ ነው። (1 ጴጥሮስ 2:9) ወይም ደግሞ ኢየሱስ “ይህ ትውልድ” የተወሰነ የጊዜ ርዝማኔን ያመለክታል ማለቱ አልነበረም።
13 ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ በአእምሮው ይዞ የነበረው የሰጠው ምልክት ሲፈጸም የሚመለከቱትን ተቃዋሚ አይሁዶች ነበር። በሉቃስ 21:32 ላይ “ይህ ትውልድ” ተብሎ የተጠቀሰውን ሐሳብ በሚመለከት ፕሮፌሰር ጆኤል ቢ ግሪን እንዲህ ብለዋል:- “በሦስተኛው ወንጌል ላይ የሚገኘው ‘ይህ ትውልድ’ የሚለው ሐረግ (እና ሌሎች ተመሳሳይ መግለጫዎች) አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክተው የአምላክን ዓላማ የሚቃወመውን የሰዎች ክፍል ነው። . . . አውቀውና ሆነ ብለው ለመለኮታዊው ዓላማ ጀርባቸውን የሚሰጡ ሰዎችን [ያመለክታል።]”b
14. በዚያን ጊዜ የነበረው “ትውልድ” ምን ደረሰበት? ሆኖም ክርስቲያኖች ያጋጠማቸው ነገር የተለየ የሆነው እንዴት ነበር?
14 የምልክቱን መፈጸም ለማስተዋል የሚችልበት አጋጣሚ የነበረው የተቃዋሚ አይሁዶች ክፉ ትውልድ መጨረሻውን ማየት ነበረበት። (ማቴዎስ 24:6, 13, 14) ደግሞም አይቷል! በ70 እዘአ በንጉሠ ነገሥት ቬስፓሲያን ልጅ በቲቶ የሚመራው የሮማ ሠራዊት ተመልሶ መጣ። አሁንም እዚያው ከተማዋ ውስጥ እንዳሉ የታገቱት አይሁዶች የደረሰባቸው መከራ ለማመን የሚያዳግት ነበር።c የዓይን ምሥክር የነበረው ፍላቪየስ ጆሴፈስ ሪፖርት እንዳደረገው ሮማውያን ከተማዋን በደመሰሱ ጊዜ ወደ 1,100,000 አይሁዶች የሞቱ ሲሆን ወደ 100,000 የሚጠጉ ደግሞ በምርኮ ተወስደዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ብዙም ሳይቆዩ በረሃብ ወይም በሮማውያን ቲያትር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ አልቀዋል። በእርግጥም ከ66-70 እዘአ የነበረው መከራ ኢየሩሳሌምና የአይሁድ ሥርዓት እስከዚያን ጊዜ ድረስ ካጋጠማቸውም ሆነ ወደፊት ሊያጋጥማቸው ከሚችለው መከራ እጅግ የከፋ ነበር። የኢየሱስን ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ ሰምተው በ66 እዘአ የሮማ ሠራዊት ከሄደ በኋላ ኢየሩሳሌምን ትተው ለወጡት ክርስቲያኖች ግን ሁኔታው ምንኛ የተለየ ነበር! ‘የተመረጡት’ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በ70 እዘአ ከደረሰው ጥፋት ‘ድነዋል’ ወይም ደኅንነታቸው ተጠብቋል።—ማቴዎስ 24:16, 22
-
-
“ይህ ሊሆን ግድ ነውና”መጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 1
-
-
b ብሪታኒያዊው ምሁር ጂ አር ቢዝሊ-መርኢ እንዲህ ብለዋል:- “‘ይህ ትውልድ’ የሚለው ሐረግ በትርጉም ረገድ ምንም ዓይነት ችግር ሊፈጥር አይገባም። በጥንቱ ግሪክ ዬኔአ ማለት ልደት፣ ተወላጆች ብሎም ዘር የሚል ትርጉም ስላለው [በግሪክኛው ሴፕቱጀንት] ላይ አብዛኛውን ጊዜ . . . እድሜ፣ የሰው ልጅ እድሜ ወይም በአንድ ወቅት የሚኖሩ ሰዎችን ትውልድ የሚያመለክተውን ዶር የሚለውን የዕብራይስጥ ቃል ለመተርጎም አገልግሏል። . . . ኢየሱስ ተናግሯቸዋል በሚባሉ ሐሳቦች ላይ ቃሉ ድርብ ትርጉም የሚያስተላልፍ ሲሆን በአንድ በኩል በዘመኑ የነበሩ ሰዎችን ለማመልከት ብቻ የተሠራበት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ነቀፋ አዘል መሆኑን የሚያሳይ ነበር።”
-