በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ መግለጫዎችን የሚያሳዩ የተለያዩ ፎቶዎችን፣ ሥዕሎችን፣ ድምፅ የሌላቸው ቪዲዮዎችንና አኒሜሽኖችን ይዟል።
ቤተፋጌ፣ የደብረ ዘይት ተራራ እና ኢየሩሳሌም
ይህ አጭር ቪዲዮ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከምትገኘውና በዛሬው ጊዜ ኤት-ቱር ተብላ ከምትጠራው የጥንቷ ቤተፋጌ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም የሚወስደውን መንገድ ያሳያል፤ ቪዲዮው ከቤተፋጌ እስከ ደብረ ዘይት ተራራ ድረስ ያለውን የመንገዱን ክፍል የሚያሳይ ነው። ቢታንያ የምትገኘው ከቤተፋጌ በስተ ምሥራቅ ማለትም በደብረ ዘይት ተራራ ምሥራቃዊ ክፍል ባለው አቀበት ላይ ነው። ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሳሌም በሚቆዩበት ወቅት ምሽቱን የሚያሳልፉት በቢታንያ ሳይሆን አይቀርም፤ ቢታንያ የነበረችው በአሁኑ ጊዜ ኤል-አዛሪያ (ኤል አይዛሪያ) የምትባለው መንደር በምትገኝበት ቦታ ላይ ነው፤ ይህ ስም የአረብኛ ስም ሲሆን ትርጉሙም “የአልዓዛር መኖሪያ” ማለት ነው። ኢየሱስ ያርፍ የነበረው የማርታ፣ የማርያምና የአልዓዛር ቤት ውስጥ እንደነበር ጥርጥር የለውም። (ማቴ 21:17፤ ማር 11:11፤ ሉቃስ 21:37፤ ዮሐ 11:1) ኢየሱስ ከእነሱ ቤት ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም በሚጓዝበት ወቅት በቪዲዮው ላይ የሚታየውን መንገድ ሳይከተል አልቀረም። ኢየሱስ ኒሳን 9, 33 ዓ.ም. በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ በደብረ ዘይት ተራራ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም የሄደው ከቤተፋጌ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም የሚወስደውን ይህን መንገድ ተከትሎ ሳይሆን አይቀርም።
ከቢታንያ ወደ ቤተፋጌ የሚወስደው መንገድ
ቤተፋጌ
የደብረ ዘይት ተራራ
የቄድሮን ሸለቆ
ቤተ መቅደሱ የሚገኝበት ቦታ
ምስማር የተመታበት የእግር አጥንት
ይህ፣ 11.5 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው የብረት ምስማር የተመታበት የሰው እግር አጥንት ነው። ፎቶግራፉ ተመሳስሎ የተሠራውን አጥንት ያሳያል። ዋናው አጥንት የተገኘው በ1968 በሰሜናዊ ኢየሩሳሌም በተደረገ ቁፋሮ ወቅት ሲሆን እግሩ ላይ ምስማር የተመታበት ይህ ሰው በሮማውያን ዘመን እንደኖረ ይገመታል። ይህ አጥንት፣ ሮማውያን ወንጀለኞችን በእንጨት ላይ ለመቸንከር ምስማር ይጠቀሙ እንደነበር የሚያሳይ አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃ ነው። ሮማውያን ወታደሮች ኢየሱስ ክርስቶስን በእንጨት ላይ ለመቸንከር የተጠቀሙት እንዲህ ዓይነት ምስማር ሳይሆን አይቀርም። ይህ አጥንት የተገኘው በአንድ የድንጋይ ሣጥን ውስጥ ነው። በዚያ ዘመን፣ የሞተ ሰው በድን ከበሰበሰ በኋላ አፅሙ ተሰብስቦ እንዲህ ባለው የድንጋይ ሣጥን ውስጥ ይቀመጥ ነበር። ይህ ምስማር የተመታበት አጥንት በዚህ የድንጋይ ሣጥን ውስጥ መገኘቱ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የተገደለ ሰው ሊቀበር እንደሚችል ይጠቁማል።—ማቴ 27:35