የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 8/15 ገጽ 4-7
  • ጤንነትና ደስታ እንዴት ሊገኝ ይችላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጤንነትና ደስታ እንዴት ሊገኝ ይችላል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጤንነትና ደስታ​—በአንድ ቃል ሲጠቃለል
  • የአምላክ ንጉሣዊ አገዛዝ ወይም መንግሥት
  • አሁን ጤንነትና ደስታ ልናገኝ እንችላለንን?
  • ጤንነትህ ደስታህ ነው
  • ጤንነትና ደስታ​—ሊገኙ የሚችሉ ነገሮች ናቸውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ደስታ ስለሚገኝበት መንገድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ደስታ ለማግኘት የተደረገ ፍለጋ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 8/15 ገጽ 4-7

ጤንነትና ደስታ እንዴት ሊገኝ ይችላል?

ሰው በጤንነትና በደስታ መካከል የተቀራረበ ዝምድና እንዳለ ከተገነዘበ ረዥም ዘመን አልፎአል። “የመድሃኒት አባት” በመባል የሚታወቀው ሂፖክራተስ እንዲህ ብሏል፦ “ጥበበኛ የሆነ ሰው ከሰው ልጆች በረከቶች ሁሉ ትልቁ ጤንነት መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።” የጀርመኑ ፈላስፋ አርተር ሾፐንሃወር “ሁለቱ የሰው ደስታ ጠላቶች ሥቃይና መሰልቸት ናቸው” ብሏል።

አናቶሚ ኦቭ አን ኢልነስ አስ ፐርሲቭድ ባይ ዘ ፔሸንት በተባለው መጽሐፍ ላይ ኖርማን ከዝንስ ለሕይወታቸው ያሰጋ የነበረውን በሽታ ለማሸነፍ እንዴት በሳቅ እንደተጠቀሙ ተሞክሮአቸውን ተናግረዋል። ሊድኑ ከቻሉባቸው ምክንያቶች አንደኛው የሚያስቁ ፊልሞችን በሚመለከቱበት ጊዜ ከአንጀታቸው በመሳቃቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ታዋቂ የሆኑ ዶክተሮችም በምንስቅበት ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ የሚፈስሱት እንደ ኤንዶርፊን የመሰሉት ኬሚካሎች ሊያስገኙ ስለሚችሉት ጥቅም መመርመር ጀምረዋል። ስለዚህም “ደስ ያላት ልብ መልካም መድሃኒት ናት”በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ምሳሌ ጥበብ የተሞላበት ምሳሌ እንደሆነ መመልከት እንችላለን።​—ምሳሌ 17:22

ሆኖም ጥሩ ጤንነት ብቻውን ለደስታ ዋስትና እንደማይሆን ተመራማሪዎች አውቀዋል። ምክንያቱም ብዙ ጤነኛ ሰዎች ደስተኞች አይደሉም። ከ100,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የቀረቡ መጠይቆችና ቃለ ምልልሶች ጆናታን ፍሪድማንን ወዳልተጠበቀ መደምደሚያ አድርሶአቸዋል። ደስታ ከሌላቸው ሰዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት በመሠረቱ ጤናማ ሰዎች ናቸው።

ጤንነትና ደስታ​—በአንድ ቃል ሲጠቃለል

ታዲያ ጤንነትና ደስታ የተዋሃዱበት ሕይወት የት ሊገኝ ይችላል? ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ኮንፊሽየስ የሚከተለውን አስተውሎ ነበር፦ “በቅርብ ያሉት ሰዎች ደስተኞች ሲሆኑ፣ በሩቅ ያሉትም ሲሳቡ ጥሩ መንግሥት አለ ማለት ነው።” በቅርቡ የዘመናችን ርዕሰ ብሔር የነበሩት ቶማስ ጄፈርሰን የመንግሥት ብቸኛ ግብ “ከሥሩ ለሚተዳደረው ጠቅላላ ሕዝብ ከፍተኛ ደስታ ማስፈን ነው” በማለት ተናግረዋል።

በእርግጥም የሰው ልጅ የጤንነትና የደስታ ጥማት የሚረካበት የመጨረሻው መፍትሔ በመንግሥት ላይ ያተኮረ መሆኑን ሁኔታውን በቅርብ የመረመሩ ሰዎች ተገንዝበዋል።

ሰዎች በዘመናት ሁሉ ደስታ ለማግኘት መንግሥታትን ተስፋ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ለምሳሌም ያህል የዩናይትድ ስቴትስ የነፃነት አዋጅ እነዚህን ዝነኛ ቃላት ይዟል፦ “የሚከተሉት እውነቶች ሊሻሩና ጥያቄ ሊነሳባቸው የማይችሉ እውነቶች እንደሆኑ እናምናለን። ሰዎች ሁሉ እኩል ሆነው ተፈጥረዋል። ፈጣሪያቸውም ሊወሰዱባቸው የማይገቡ መሠረታዊ መብቶችን ሰጥቶአቸዋል። ከእነዚህም መብቶች መካከል በሕይወት የመኖር፣ የነጻነትና ደስታ የመፈለግ መብቶች ይገኛሉ።” እዚህ ላይ የተጠቀሰው መንግሥት ለዜጎቹ ደስታን እንዲፈልጉ ብቻ መብት እንደሰጣቸው ልብ በል። ጤናን በተመለከተም ብዙ መንግሥታት የዜጎቻቸውን ጤንነት ለማሻሻል አንዳንድ ፕሮግራሞችን በማራመዳቸው የሚመሰገኑ ናቸው። አሁንም ቢሆን ለአብዛኛው ሕዝብ ጥሩ የሆነ አጠቃላይ ጤንነት ማምጣት ሊገኝ የማይችል ተስፋ ሆኗል።

ይሁን እንጂ ከዚህ የበለጠ ነገር እንደሚያመጣ ቃል የሚገባ መንግሥት ቢኖርስ? ሰዎች ደስታን እንዲፈልጉ ብቻ ሳይሆን ደስታን ራሱን እንደሚያመጣ ቃል ቢገባስ? እንዲሁም የጤና ኢንሹራንስ ጥቅሞችን ሳይሆን ጥሩ ጤናን ለመስጠት ቃል ቢገባስ? የሰው ልጅ የጤንነትና የደስታ ጥማት አሁን መፍትሔ አገኘ ብለህ አትደሰትምን?

ብዙ ሰዎች በዛሬው ጊዜ ይህንን እውን የማይሆን ሕልም ነው ብለው ያስቡ ይሆናል። ሆኖም እንደዚህ ያለው መንግሥት በትንቢት የተነገረለት ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ዝርዝር ሁኔታዎች ተገልጸዋል። ይህንን አስተማማኝ መግለጫ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። መንግሥቱ ደግሞ የአምላክ መሲሐዊ መንግሥት ነው።

የአምላክ ንጉሣዊ አገዛዝ ወይም መንግሥት

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “አምላክ መንግሥት” ብዙ ጊዜ ይናገራል። ይህች መንግሥት ምንድን ነች? የአዲስ ዓለም የዌብስተር የአሜሪካ ቋንቋ መዝገበ ቃላት “ኪንግደም” (መንግሥት) የሚለውን ቃል “በንጉሥ ወይም በንግሥት የሚመራ አስተዳደር ወይም አገር” ሲል ይተረጉመዋል። በቀላል አነጋገር የአምላክ መንግሥት በአምላክ ልጅና በአምላክ በቀባው ንጉሥ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚመራ ንጉሣዊ መስተዳድር ነው። ይህ መንግሥት በአምላክ ዓላማ ውስጥ ምን ዓይነት አስፈላጊ ቦታ ተሰጥቶታል? ኢየሱስ የተናገራቸው ቅላት መልሱን ይስጡን፦ “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት . . . ፈልጉ . . . ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል . . . ስለዚህ ተልኬአለሁና ለሌሎች ከተማዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል . . . የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ በኃይል ይገቡባታል።”​—ማቴዎስ 6:33፤ 24:14፤ ሉቃስ 4:43፤ 16:16

“መንግሥት” የሚለው ቃል ስለ ኢየሱስ ሕይወት በሚገልጽ የወንጌል ታሪኮች ውስጥ ከመቶ ጊዜ በላይ ተጠቅሷል። አንዳንድ ጊዜም በተለይ ከጤናና ከደስታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ተጠቅሷል። ማቴዎስ 9:35 ምን እንደሚል ተመልከት፦ “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፣ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፣ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።” ኢየሱስ ጤናን እንደገና የመመለስን ጉዳይ ስለ መንግሥቱ ካስተማረው ትምህርት ጋር ያያያዘው ቢሆንም የተለያዩ በሽታዎችን የፈወሰው የስብከትና የማስተማር ሥራውን በሚፈጽምበት ጊዜ እግረ መንገዱን ብቻ ነበር። ታዋቂነትን ያተረፈው በአስተማሪነቱ እንጂ በፈዋሽነቱ አልነበረም። (ማቴዎስ 26:18፤ ማርቆስ 14:14፤ ዮሐንስ 1:38) ሥራው ያተኮረው ሰዎችን በመፈወስ ወይም ለበሽተኞች እንክብካቤ በማድረግ ላይ ብቻ አልነበረም። ምንጊዜም ያሳስበው የነበረው የመንግሥቱ ጉዳይ ነበር። ሰዎችን በችግራቸውና በበሽታቸው በመርዳት በጣም ርህሩህ መሆኑን አሳይቶአል። መለኮታዊ ድጋፍ እንዳለውም አረጋግጦአል።

በተጨማሪም ኢየሱስ ያደረጋቸው ፈውሶች የአምላክ መንግሥት ምድርን ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠርበት ጊዜ ለሚኖረው ፈውስና የጤንነት ሁኔታ መቅድም ሆነዋል። ይህም በራእይ 22:1, 2 ላይ በተገለጸው ራእይ ተረጋግጦአል። “በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወት ውኃ ወንዝ አሳየኝ። በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፣ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።”

ይሁን እንጂ ይህንን ልናገኝ የምንችለው የት ነው? ይህን የመሰለ አስደናቂ ፈውስ በዚህች ምድር ላይ ሊፈጸም አይችልም ብለው የሚያስቡ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ አንተው ራስህ በጸሎትህ ሳትጠቅሰው የማትቀረውን “መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” የሚለውን የኢየሱስን ቃል አስታውስ።​—ማቴዎስ 6:10

ስለዚህ ጤንነትና ደስታ የምናገኝበት እውነተኛውና ትምክህት የሚጣልበት ተስፋችን የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው። ቢሆንም አንድ የሚቀረን ጥያቄ አለ።

አሁን ጤንነትና ደስታ ልናገኝ እንችላለንን?

አሁንም ቢሆን የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች መከተላችን የተሻለ ጤንነትና ደስታ እንድናገኝ ያስችለናል። በዚህ መጽሔት ገጾች ላይ በተደጋጋሚ እንደተጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱስን በዕለታዊ ሕይወታቸው የሚሠሩበት ሰዎች የጾታ ብልግና፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከመጠን በላይ መጠጣትና የዕጽ ሱሰኝነት ከሚያስከትሏቸው የጤና ችግሮች ተጠብቀዋል። በተጨማሪም ፀጥ ያለና የተረጋጋ ሕይወት የሚያስከትላቸውን ጥቅሞችን አይተዋል። ከዘመዶቻቸውና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ተሻሽሎላቸዋል።

ጥሩ ጤንነት ማግኘት የግዴታ ዘላቂ የሆነ ደስታ እንደማያመጣ ቀደም ሲል ተመልክተናል። የተሟላ ደስታ ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ቀደም ሲል በተጠቀሰው ጥናት ላይ ጆናታን ፍሪድማን ይህን ጥያቄ በጥልቀት መርምረውት ነበር። በደስታ ላይ ተጽእኖ ሊኖራቸው ስለሚችሉ እንደ “ፍቅርና ጾታ” “ወጣትነትና ሽምግልና” “የዕለት ገቢና ትምህርት” እንዲሁም “ከተማና አገር” የመሳሰሉትን ጉዳዮች መርምረው ነበር። እነዚህ ጉዳዮች በአንድ ሰው መሠረታዊ ደስታ ላይ የሚያስከትሉት ብዙም ውጤት እንደሌለ መረዳታቸውን ማወቅህ ያስገርምህ ይሆናል። ለምሳሌ ያህል ብዙ ቁሳዊ ነገሮች እያሏቸው ደስተኞች ሊሆኑ ያልቻሉትን ሰዎች ሁኔታ በመጥቀስ እንዲህ ብለዋል፦ “የገቢ ምንጭም ሆነ የትምህርት ደረጃ ደስታን በማግኘት ረገድ የጎላ ሚና እንደሌላቸው መገንዘባችን አስገርሞናል።”

ይህ እርሳቸው የደረሱበት መደምደሚያ ጥበበኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚከተለው በማለት የተናገረውን የሚያስተጋባ ነው፦ “በምንም ዓይነት ደረጃ ላይ ብገኝ ባለኝ መርካትን ተምሬአለሁ።” (ፊልጵስዩስ 4:11፣ ኪንግ ጀምስ ቨርሺን) የኢየሱስንም ቃላት አስታውሱ፦ “የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፣ ከመጎምጀትም ሁሉ ተጠበቁ።”​—ሉቃስ 12:15

ፕሮፌሰር ፍሪድማን የሚከተለውን ተገንዝበዋል፦ “የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እያላቸው ደስታ ያጡ ሰዎች በየጊዜው የሚናገሯቸውን ነገሮች ስንመለከት ሕይወታቸው ትርጉምና መመሪያ እንደሚጎድለው ይገልጻሉ።” ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦ “ትልቅ ቦታ ልሰጠው ባልደፍርም መንፈሳዊ መመሪያዎች አንድ ሰው ለሚያጋጥሙት ሁኔታዎች የሚኖረውን ስሜት ብሩሕ ሊያደርጉለት የሚችሉ ይመስላል። በሌላው በኩል ደግሞ መንፈሣዊ መመሪያዎችን ማጣት ማንኛውንም ነገር ይመርዛል ወይም ትክክለኛ አመለካከት እንዳይኖር ያደርጋል።”

በዘመናችን እነዚህ አስተያየቶች ትክክል መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ሁኔታዎችን እንመለከታለን። በዙሪያህ ያለውን ተመልከት። ሁሉም ሰዎች ያላቸውም ሆኑ የሌላቸው ደስታ ለማግኘት ሲሯሯጡና የፈለጉትንም ደስታ ለማግኘት እንዳልቻሉ ትመለከታለህ። እውነት ነው፣ አንዳንዶች ተስፋ ቆርጠው በጭንቀት ይኖራሉ። ሌሎች ብዙ ሰዎች ደግሞ የሚያሳድዱትን ነገር መጨበጥ አቅቶአቸው ሲባዝኑ ይኖራሉ። አንዳንዶች ጎረቤታቸው የሆነ ሰው ደስታ ለማግኘት ብሎ ትዳሩን ሲያፈርስ እየተመለከቱ እነርሱ ደግሞ ደስታ ለማግኘት ብለው ያገባሉ። አንዳንዶች ራሳቸውን በከባድ ሥራ ሲጨርሱ ሌሎቹ ደግሞ ረጅምና ምናልባትም ብዙ ገንዘብ የሚያስወጣ ዕረፍት ለመውሰድ ሲሉ ሥራቸውን ይተዋሉ። የሁሉም ፍላጎት ከሰው ልጆች ፈጽሞ የራቀውን ደስታና ጤንነት ማግኘት ነው። ለመያዝ ግን አግኝተውታልን? አንተስ አግኝተኸዋልን?

ጤንነትህ ደስታህ ነው

በአሁኑ ጊዜ ብዙ ጤንነትና ደስታ ልታገኝ ትችላለህ። ይሁን እንጂ ይህን ጤንነትና ደስታ ልታገኝ የምትችለው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስን ተግባራዊ ምክር በመጠቀም ጤንነትህን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለመከባከብ መሞከር ጥበብ ነው። በተጨማሪም ያለውን ሁኔታ ተቀብሎ መኖር ይረዳል። ፍጽምና በሌለው አካላችን ላይ በሽታ ሊመጣ እንደሚችል አምነን መቀበል ይኖርብናል። እንዲህ ካደረግን በሽታው በሚደርስብን ጊዜ ቅስማችን አይሰበርም። ቅስማችን እንዳይሰበርና ብሩህ የሆነ አመለካከት ይዘን ለመኖር በመጪው አዲስ ዓለም ውስጥ ፍጹም ጤንነት ስለማግኘት በተሰጠው ተስፋ ማተኮር ሊያስፈልገን ይችላል።

በአሁኑ ጊዜ መጠነኛ ደስታ ያለህ መሆኑን ለማወቅ ራስህን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ 1. ሕይወቴን እቆጣጠረዋለሁን? 2. በመሠረቱ ከራሴና በዙሪያዬ ካሉት ሰዎች ጋር ሰላም አለኝን? 3. በመጽሐፍ ቅዱስ ደረጃ ሲመዘን በሕይወቴ ለማከናወን በቻልኩአቸው ነገሮች እደሰታለሁን? 4. ቤተሰቤና እኔ አምላክን ለማገልገል በመቻላችን እንደሰታለንን?

በአብዛኛው ምርጫው የራሳችን ነው። ብዙዎቻችን በመሠረቱ ጤነኞች እንሆን ይሆናል። ደስተኞች የመሆን አማራጭ ደግሞ አለን። ይህን ለማግኘት ግን መንፈሳዊ ግቦች ሊኖሩንና እነዚህንም ግቦች ለማግኘት ጠንክረን መሥራት ይገባናል። “መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናል”የሚሉትን የኢየሱስ ቃላት አስታውሱ። (ማቴዎስ 6:21)ፍጹም በሆነው የመሲሐዊው መንግሥት አገዛዝ ሥር ከዚህ በጣም የሚበልጥ ጤናና ደስታ እንደምናገኝ ተስፋ የምናደርግበት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ምክንያት አለን። በዚያ ጊዜ የተሟላ ጤንነትና ደስታ ልናገኝ እንችላለን።

[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ደስተኛ የሆኑ ሰዎች ፍጹም ጤንነት ለማግኘት ያላቸውን ተስፋ ለሌሎች ለማካፈል ደስተኞች ናቸው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ