-
ስመ ጥፉ በሆነችው አመንዝራ ላይ መፍረድራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
1. ከሰባቱ መላእክት አንዱ ለዮሐንስ ምን ገለጸለት?
የይሖዋ የጽድቅ ቁጣ ጽዋ ሙሉ በሙሉ ማለትም ሰባቱም ጽዋ መፍሰስ ይኖርበታል። ስድስተኛው መልአክ የራሱን ጽዋ በጥንትዋ ባቢሎን ላይ ማፍሰሱ ሁኔታዎች ወደ መጨረሻ የአርማጌዶን ጦርነት በሚገሰግሱበት ጊዜ በታላቂቱ ባቢሎን ላይ ለሚደርሰው መቅሰፍት ምሳሌ መሆኑ ተገቢ ነበር። (ራእይ 16:1, 12, 16) አሁንም ይሖዋ የጽድቅ ፍርዱን ለምንና እንዴት እንደሚፈጽም የገለጸው ይኸው መልአክ ሳይሆን አይቀርም። ዮሐንስ ከዚህ ቀጥሎ በተመለከተውና በሰማው ነገር በጣም ተደንቆአል። “ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ:- ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።”—ራእይ 17:1, 2
2. “ታላቂቱ ጋለሞታ” (ሀ) የጥንትዋ ሮም እንዳልሆነች (ለ) ታላቅ የንግድ ድርጅት እንዳልሆነች (ሐ) ሃይማኖታዊ ድርጅት እንደሆነች የሚያረጋግጥ ምን ማስረጃ አለን?
2 “ታላቂቱ ጋለሞታ!” ይህን የመሰለ አስደንጋጭ ስም የተሰጣት ለምንድን ነው? እርስዋስ ማን ናት? አንዳንዶች ይህች ምሳሌያዊት አመንዝራ የጥንትዋ ሮም ናት ይላሉ። ይሁን እንጂ ሮማ የፖለቲካ ኃይል ነበረች። ይህች አመንዝራ ከምድር ነገሥታት ጋር የምትሴስን ናት። ከእነዚህም ነገሥታት መካከል የሮማ ነገሥታት እንደሚገኙበት የታወቀ ነው። ከዚህም በላይ ከጠፋች በኋላ “የምድር ነገሥታት” ስለጥፋትዋ ያለቅሱላታል። ስለዚህ የፖለቲካ ኃይል ልትሆን አትችልም። (ራእይ 18:9, 10) በተጨማሪም የምድር ነጋዴዎችም ስላዘኑላት ታላላቅ የንግድ ድርጅቶችን የምታመለክት ልትሆን አትችልም። (ራእይ 18:15, 16) ይሁን እንጂ ‘በአስማትዋ የምድር አሕዛብን ሁሉ እንዳሳተች’ እናነባለን። (ራእይ 18:23) ይህም ታላቋ አመንዝራ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ድርጅት እንደሆነች እንድንገነዘብ ያስችለናል።
3. (ሀ) ታላቂቱ ጋለሞታ ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ወይም ከሕዝበ ክርስትና የበለጠ ነገር ማመልከት የሚኖርባት ለምንድን ነው? (ለ) በአብዛኞቹ የምሥራቃውያን ሃይማኖቶችም ሆነ በሕዝበ ክርስትና ኑፋቄዎች ውስጥ እንዴት ያሉ ባቢሎናዊ መሠረተ ትምህርቶች ይገኛሉ? (ሐ) የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ የነበሩት ጆን ሄንሪ ኒውማን ስለ ብዙዎቹ የሕዝበ ክርስትና መሠረተ ትምህርቶች፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችና ልማዶች አመጣጥ ምን አምነዋል? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት)
3 ይሁን እንጂ የምታመለክተው የትኛውን ሃይማኖታዊ ድርጅት ነው? አንዳንዶች እንደሚሉት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናትን? ወይም መላዋን ሕዝበ ክርስትና የምታመለክት ናትን? አሕዛብን በሙሉ ያሳተች ድርጅት ከሆነች ከዚህ የበለጠ ስፋት ያላት መሆን ይኖርባታል። መላውን የሐሰት ሃይማኖት ግዛት የምታጠቃልል መሆን ይኖርባታል። በምድር በሙሉ በሚገኙ ባቢሎናዊ መሠረተ ትምህርቶች በብዛት መኖራቸው ይህች ድርጅት ከባቢሎን ምሥጢሮች የመነጨች መሆኗን ያመለክታል። ለምሳሌ ያህል የሰው ነፍስ ዘላለማዊነት፣ የሲኦል ሥቃይና የአማልክት ሥላሴነት እምነት በአብዛኞቹ የሩቅ ምሥራቅ ሃይማኖችም ሆነ በሕዝበ ክርስትና ሃይማኖቶች ውስጥ ይገኛሉ። ከ4,000 ዓመታት በፊት በጥንትዋ የባቢሎን ከተማ ውስጥ የተጸነሰው የሐሰት ሃይማኖት በጣም አድጐ ትልቅ ድርጅት በመሆኑ ታላቂቱ ባቢሎን የሚል ስያሜ ማግኘቱ የተገባ ነው።a ይሁን እንጂ ቀፋፊ በሆነው “ታላቂቱ ጋለሞታ” በሚለው ስም የተጠራችው ለምንድን ነው?
4. (ሀ) የጥንትዋ እስራኤል ግልሙትና ትፈጽም የነበረው እንዴት ነው? (ለ) ታላቂቱ ባቢሎን የገለሞተችው በምን ጉልህ መንገድ ነው?
4 ባቢሎን (ወይም ዝብርቅ የሚል ትርጉም ያላት ባቤል) ታላቅነት ደረጃ ላይ የደረሰችው በናቡከደናፆር ዘመን ነበር። የጥንትዋ ባቢሎን ከሺህ የሚበልጡ ቤተ መቅደሶችና የጸሎት ቤቶች የነበሩአት ሃይማኖትና ፖለቲካ የተጣመረባት መንግሥት ነበረች። ቀሳውስቶችዋ ከፍተኛ ሥልጣን ነበራቸው። ባቢሎን የዓለም ኃያል መንግሥት መሆንዋ ከቀረ ብዙ ጊዜ የሆነው ቢሆንም ዛሬ ደግሞ የፖለቲካ ጉዳዮችን ለመምራትና ለመቆጣጠር የምትፈልግ ሃይማኖታዊት ታላቅ ባቢሎን አለች። ይሁን እንጂ ሃይማኖት በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ መግባቱን አምላክ ይደግፋልን? በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ እስራኤል በሐሰት አምልኮ በምትካፈልበትና በይሖዋ ከመታመን ይልቅ ከብሔራት ጋር ሽርክና በምትመሰርትበት ጊዜ አመንዝራ እንደሆነች ተገልጾአል። (ኤርምያስ 3:6, 8, 9፤ ሕዝቅኤል 16:28-30) ታላቂቱ ባቢሎንም አመንዝራለች። በምድር ነገሥታትና ገዥዎች ላይ ሥልጣን ለማግኘት ስትል የመሰላትን ሁሉ አድርጋለች።—1 ጢሞቴዎስ 4:1
5. (ሀ) ሃይማኖታዊ ቀሳውስት እንዴት ያለ ዝናና የከበሬታ ቦታ ይፈልጋሉ? (ለ) ዓለማዊ ከበሬታ ለማግኘት መፈለግ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናረውን በቀጥታ የሚቃወመው እንዴት ነው?
5 በዛሬው ጊዜ ሃይማኖታዊ መሪዎች ከፍተኛ የመንግሥት ሹመት ለማግኘት ይጣጣራሉ። እንዲያውም በአንዳንድ አገሮች የካቢኔ ሹመት በመቀበል በመንግሥት ሥልጣን ይካፈላሉ። በ1988 ሁለት የታወቁ የፕሮቴስታንት ቀሳውስት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ለመሆን ተወዳድረው ነበር። የታላቂቱ ባቢሎን መሪዎች ዝና ወዳዶች ሆነዋል። ከታላላቅ የፖለቲካ ሰዎች ጋር ሆነው የተነሱአቸው ፎቶግራፎች በታላላቅ ጋዜጦች ገጾች ላይ ብዙ ጊዜ ይወጣሉ። ኢየሱስ ግን ከዚህ በተለየ መንገድ ለደቀ መዛሙርቱ “እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም” በማለት በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ ከመግባት እምቢተኛ ሆኖአል።—ዮሐንስ 6:15፤ 17:16፤ ማቴዎስ 4:8-10፤ በተጨማሪም ያዕቆብ 4:4 ተመልከት።
ዘመናዊ ‘ግልሙትና’
6, 7. (ሀ) የሂትለር ናዚ ፓርቲ በጀርመን አገር ሥልጣን ላይ የወጣው እንዴት ነው? (ለ) ቫቲካን ከሂትለር ናዚ ፓርቲ ጋር የተፈራረመችው የስምምነት ውል ሂትለር ዓለምን ለመግዛት ላደረገው ጥረት ድጋፍ የሆነው እንዴት ነው?
6 ታላቋ አመንዝራ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ጣልቃ በመግባትዋ ለሰው ልጆች ይህ ነው የማይባል ሥቃይ አምጥታለች። ለምሳሌ ያህል አንዳንዶች ከታሪክ መጻሕፍት ፍቀው ሊያጠፉት የሚፈልጉትን በጀርመን አገር ሂትለር ወደ ሥልጣን የወጣበትን የሚያስጠላ ሁኔታ እንመልከት። በግንቦት 1924 የናዚ ፓርቲ ራይክስታግ በተባለው የጀርመን ምክር ቤት ውስጥ 32 መቀመጫዎች ነበሩት። በግንቦት 1928 ግን የነበረው መቀመጫ ብዛት አንሶ 12 ደርሶ ነበር። ይሁን እንጂ ታላቁ የኢኮኖሚ ውድቀት በ1930 ዓለምን ዋጣት፣ ከዚህ ዓመት በኋላ ናዚዎች በአስደናቂ ሁኔታ አንሰራርተው በሐምሌ 1932 በተደረገው የጀርመን ምርጫ ከ608 መቀመጫዎች መካከል 230 መቀመጫ አገኙ። ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከሊቀ ጳጳሱ የጀግንነት ማዕረግ የተቀበለው የቀድሞው የጀርመን ቻንስለር ፍራንዝ ፎን ፓፔን ናዚዎችን መርዳት ጀመረ። የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት ፎን ፓፔን አዲስ ቅድስት የሮማ ግዛት የማቋቋም ሕልም ነበረው። ለአጭር ጊዜ የቆየበት የቻንስለርነት ሹመቱ ምንም ውጤት ስላላስገኘለት አሁን ደግሞ በናዚዎች በኩል ሥልጣን ለማግኘት ጥረት ማድረግ ጀመረ። እስከ ጥር 1933 ድረስ ለሂትለር የኢንዱስትሪ ከበርቴዎችን ድጋፍ አስገኝቶለት ነበር። ከዚህም በላይ ሂትለር በከፍተኛ ተንኮልና ሤራ ጥር 30 ቀን 1933 የጀርመን ቻንስለር እንዲሆን አስችሎታል። ፎን ፓፔን ራሱ ምክትል ቻንስለር ሆነና ሂትለር የጀርመን ካቶሊኮችን ድጋፍ እንዲያገኝ ዋነኛ መሣሪያ ሆኖ ማገልገል ጀመረ። ሂትለር ሥልጣን ላይ በወጣ ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ፓርላማውን አሰናበተ፣ በሺህ የሚቆጠሩ ተቃዋሚ መሪዎችን ወደ ማጎሪያ ካምፖች አስገባ። አይሁዳውያንን ለመጫንና ለመጨቆን የሚያስችለውንም ዘመቻ በይፋ ማንቀሳቀስ ጀመረ።
7 ቫቲካን ኃይል እያገኘ ከሄደው ከናዚዝም እንቅስቃሴ ጋር ሽርክና ለመፍጠር ያላት ፍላጐት ሐምሌ 20, 1933 ካርዲናል ፓቼሊ (በኋላ ሊቀ ጳጳስ ፓየስ 12ኛ የሆኑት ናቸው) በቫቲካንና በናዚ ጀርመን መካከል የተደረገውን ስምምነት በሮማ ከተማ በፈረሙ ጊዜ በግልጽ ታይቶአል። የሂትለር ወኪል በመሆን ስምምነቱን የፈረመው ፎን ፓፔን ሲሆን በዚህ ጊዜ ፓቼሊ ለፎን ፓፔን ከፍተኛውን የፓየስ መስቀል ኒሻን ሸልመውታል።b ቲቦር ኮኤቨስ ሴታን ኢን ቶፕ ሃት በተባለው መጽሐፋቸው ስለዚህ ጉዳይ ሲጽፉ እንዲህ ብለዋል:- “ስምምነቱ ለሂትለር ከፍተኛ ድል ነበር። ሂትለር ከውጪው ዓለም ካገኘው የሞራል ድጋፍ ይህ የመጀመሪያው ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ክብር ከሚሰጠው አካል የተገኘ ድጋፍ ነበር።” በስምምነቱ መሠረት ቫቲካን ለጀርመን የካቶሊክ ማዕከላዊ ፓርቲ ትሰጥ የነበረውን ድጋፍ ለማንሳት ተስማማች። ይህን በማድረጓም የሂትለርን ባለ አንድ ፓርቲ “ፍጹማዊ መንግሥት” አድርጋ መቀበሏን አረጋገጠች።c ከዚህም በላይ ይህ ስምምነት በ14ኛው አንቀጽ ላይ የሚከተለውን አስፍሮ ነበር:- “የሊቃነ ጳጳሳት፣ የመሳሰሉት ሹመቶች የሚጸድቁት ራይኩ (የናዚ መንግሥት) የሾመው ገዥ አጠቃላይ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የማይቃወም መሆኑን መርምሮ ካረጋገጠ በኋላ ነው።” በ1933 ፍጻሜ ላይ (ፓፓ ፓየስ 11ኛ “ቅዱስ ዓመት” ብለው የሰየሙት ዓመት ነበር) ሂትለር መላውን ዓለም ለመግዛት በሚያደርገው ጥረት የቫቲካን ድጋፍ ግንባር ቀደሙን ቦታ ይዞ ነበር።
8, 9. (ሀ) ቫቲካን እንዲሁም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና ቀሳውስትዋ የናዚን የጭቆና ግዛት እንዴት ተቀበሉት? (ለ) ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጀመረበት ጊዜ የጀርመን ካቶሊክ ጳጳሳት ምን መግለጫ አውጥተው ነበር? (ሐ) የሃይማኖትና የፖለቲካ ሽርክና እንዴት ያለ ውጤት አስከትሎአል?
8 የሂትለርን ጭካኔ የተቃወሙና በመቃወማቸውም ምክንያት መከራ የተቀበሉ በጣት የሚቆጠሩ ቀሳውስትና መነኮሳት ቢኖሩም ቫቲካንም ሆነች የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከቀሳውስት ጭፍሮችዋ ጋር የኮምኒዝምን መስፋፋት እንደሚገታ ታላቅ ኃይል አድርገው የተመለከቱትን የናዚ ጭካኔ ደግፈዋል። በቫቲካን የተመቻቸ ሥልጣን የያዙት ፓፓ ፓየስ 12ኛ በአይሁዳውያን ላይ የተፈጸመው እልቂትና በይሖዋ ምሥክሮችና በሌሎች ሰዎች ላይ ይፈጸም የነበረው ስደት አለምንም ወቀሳ እንዲቀጥል ፈቅደዋል። ፓፓ ጆን ዳግማዊ በግንቦት ወር 1987 ጀርመንን በጎበኙ ጊዜ አንድ ቄስ ያሳየውን ፀረ ናዚ አቋም አሞግሰው መናገራቸው ግራ የሚገባ ነበር። በሂትለር የሰቆቃ አገዛዝ ዘመን የቀሩት በሺህ የሚቆጠሩ የጀርመን ቀሳውስት ምን ያደርጉ ነበር? የጀርመን ካቶሊክ ጳጳሳት ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፈነዳበት በመስከረም ወር 1939 የጻፉት ደብዳቤ በዚህ ረገድ የፈጸሙትን ይገልጽልናል። ደብዳቤው በከፊል እንደሚከተለው ይነበባል:- “በዚህ ወሳኝ ሰዓት ካቶሊክ ወታደሮቻችን ፊውረሩን (ሂትለርን) በመታዘዝ ግዳጃቸውን እንዲፈጽሙና መላውን ስብዕናቸውን መሥዋዕት እንዲያደርጉ እንማጠናቸዋለን። ታማኞቻችን በሙሉ ይህ ጦርነት የተባረከ ውጤት እንዲያገኝ ጸሎት በማቅረብ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን።”
9 ይህን የመሰለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዲፕሎማሲ ሃይማኖት ባለፉት 4,000 ዓመታት ከፖለቲካ መንግሥታት ሥልጣንና ጥቅም ለማግኘት ዝሙት ሲፈጽም እንዴት እንደቆየ ያሳየናል። ይህ ዓይነቱ የሃይማኖትና የፖለቲካ ጥምረት ጦርነትን፣ ስደትንና ብዙ ዓይነት መከራዎችን በሰው ልጆች ላይ ሲያስፋፋ ቆይቶአል። ይሖዋ በዚህች ታላቅ አመንዝራ የሚፈርድበት ጊዜ በጣም በመቃረቡ መላው የሰው ልጅ በጣም ሊደሰት ይገባዋል። ይኸው ፍርድ ፈጥኖ እንዲፈጸም ምኞታችን ነው!
በብዙ ውኃዎች ላይ ተቀምጣለች
10. ታላቂቱ ባቢሎን ለመከላከያዋ የምትተማመንባቸው “ብዙ ውኃዎች” ምንድን ናቸው? እነርሱስ ምን እየደረሰባቸው ነው?
10 የጥንትዋ ባቢሎን በብዙ ውኃዎች ላይ ማለትም በኤፍራጥስ ወንዝና በብዙ ቦዮች ላይ ተቀምጣ ነበር። እነዚህ ውኃዎች እስከ ደረቁበት ጊዜ ድረስ ለመከላከያዋና ብዙ ሀብት ለምታገኝበት የንግድ እንቅስቃሴዋ ያገለግሉአት ነበር። (ኤርምያስ 50:38፤ 51:9, 12, 13) ታላቂቱ ባቢሎንም ለብልጽግናዋና ለመከላከያዋ የምትተማመንባቸው ብዙ ውኃዎች አሉአት። እነዚህ ምሳሌያዊ ውኃዎች “ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም” ናቸው። እነዚህም እርስዋ የሰለጠነችባቸውና የገንዘብ ድጋፍ ያገኘችባቸው በሺህ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው ማለት ነው። ይሁን እንጂ እነዚህም ውኃዎች በመድረቅ ላይ ወይም ድጋፋቸውን በማንሳት ላይ ናቸው።—ራእይ 17:15፤ ከመዝሙር 18:4ና ከኢሳይያስ 8:7 ጋር አወዳድር።
11. (ሀ) የጥንትዋ ባቢሎን ‘ምድርን ሁሉ ያሰከረችው’ እንዴት ነበር? (ለ) ታላቂቱ ባቢሎን ‘ምድርን በሙሉ ያሰከረችው’ እንዴት ነው?
11 ከዚህም በላይ የጥንትዋ ባቢሎን “በእግዚአብሔር [“በይሖዋ፣” NW] እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ” እንደሆነች ተነግሮአል። (ኤርምያስ 51:7) የጥንትዋ ባቢሎን አጎራባች አገሮችን በጦር ኃይልዋ በወረረችበት ጊዜ የይሖዋን የቁጣ ጽዋ እንዲጠጡ አስገድዳ ነበር። እንደ ሰከረ ሰው ደካሞች እንዲሆኑ አድርጋ ነበር። በዚህ ረገድ የይሖዋ መሣሪያ ሆና አገልግላለች። ታላቂቱ ባቢሎንም ዓለም አቀፍ ግዛት እስክትሆን ድረስ በወረራ ብዙ ድሎችን አግኝታለች፤ ቢሆንም የአምላክ መሣሪያ እንዳልሆነች ግልጽ ነው። ያገለገለችው ከአምላክ ይልቅ አብረዋት ሃይማኖታዊ ምንዝር የፈጸሙትን “የምድር ነገሥታት” ነው። በሐሰት መሠረተ ትምህርቶችዋና ሰዎችን በባርነት በሚያስገዙ ሃይማኖታዊ ልማዶች በመጠቀም “በምድር የሚኖሩትን” ሰፊ ሕዝቦች እንደ ሰከረ ሰው ደካማና የገዥዎቻቸውን ፈቃድ በጭፍን የሚፈጽሙ በማድረግ እነዚህን ነገሥታት አስደስታለች።
12. (ሀ) በጃፓን አገር ያለው የታላቂቱ ባቢሎን ክፍል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ብዙ ደም እንዲፈስስ ያደረገው እንዴት ነው? (ለ) በጃፓን አገር ታላቂቱ ባቢሎንን ይደግፉ የነበሩ “ውኃዎች” ድጋፋቸውን ያቋረጡት እንዴት ነው? ይህስ ምን ውጤት አስከትሎአል?
12 በዚህ ረገድ የጃፓኑ የሺንቶ ሃይማኖት ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል። በዚህ ሃይማኖት አዕምሮው የታጠበበት ጃፓናዊ ወታደር የሁሉ የበላይ የሆነ የሺንቶ አምላክ ለሆነው ለንጉሠ ነገሥቱ ሕይወቱን መሠዋቱን እንደ ታላቅ ክብር ይቆጥረዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት 1,500,000 የሚያክሉ ጃፓናውያን ወታደሮች በጦር ሜዳ ላይ ተገድለዋል። እነዚህ ወታደሮች በሙሉ እጅ መስጠትን እንደ ታላቅ ውርደት ይቆጥሩ ነበር። ይሁን እንጂ ጃፓን በጦርነቱ በመሸነፍዋ ምክንያት ንጉሠ ነገሥት ሂሮሂቶ የመለኮትነት ባሕርይ የሌላቸው መሆናቸውን ለመቀበል ተገደዋል። በዚህም ምክንያት የታላቂቱ ባቢሎን የሺንቶ ክፍል ድጋፍ ያስገኙለት የነበሩትን ብዙ “ውኃዎች” አጥቶአል። ይህ የሆነው ሺንቶይዝም በፓስፊክ የጦርነት መድረክ ላይ ብዙ ደም እንዲፈስስ ካደረገ በኋላ መሆኑ በጣም ያሳዝናል! በተጨማሪም የሺንቶ ተጽዕኖ መዳከሙ በ1991 በመጨረሻ ላይ ከ200,000 የሚበልጡ ጃፓናውያን የልዑሉ አምላክ የይሖዋ ውስንና የተጠመቁ አገልጋዮች እንዲሆኑ አስችሎአቸዋል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ከዚህ በፊት ሺንቶይስቶችና ቡድሂስቶች የነበሩ ናቸው።
-
-
ስመ ጥፉ በሆነችው አመንዝራ ላይ መፍረድራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
a በ19ኛው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ጆን ሄንሪ ኒውማን ስለ ክርስትና መሠረተ ትምህርቶች የተዘጋጀ ድርሰት በተባለው መጽሐፋቸው ላይ አብዛኞቹ የሕዝበ ክርስትና መሠረተ ትምህርቶች፣ ክብረ በዓሎችና የአምልኮ ሥርዓቶች ከአረማውያን የመጡ መሆናቸውን ሲያመለክቱ የሚከተለውን ጽፈዋል:- “በቤተ መቅደሶች ማገልገል፣ ቤተ መቅደሶችን በተለዩ ቅዱሳን ስም መሰየም፣ በዛፍ ቅርንጫፎች ማስጌጥ፣ ዕጣን ማጨስ፣ መብራቶችና ጧፎች ማብራት፣ ከበሽታ ሲዳን የስዕለት ቁርባን ማቅረብ፣ ጠበል፣ በዓላትና ዓውደ ዓመታት፣ የቀን መቁጠሪያዎች፣ እርሻዎችን መባረክ፣ የቅዱሳን ሥርዓተ ንግሥ፣ ልብሰ ተክህኖ፣ በጋብቻ ሥርዓት ቀለበት ማድረግ፣ ወደ ምሥራቅ መዞር፣ ከጊዜ በኋላም ሥዕልና ምስል፣ ምናልባትም የቅዳሴ መዝሙሮችና ኪርያላይሶን [ጌታ ሆይ፣ ማረን] የተባለው የምህላ ዝማሬ ከአረማውያን የመጡና ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ አድርጋ የተቀበለቻቸው ናቸው።”
“ሁሉን የሚችለው አምላክ ይሖዋ” ግን እንዲህ ዓይነቱን የጣዖት አምልኮ ከመቀደስ ይልቅ ክርስቲያኖችን “ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ . . . እርኩስንም አትንኩ” በማለት ይመክራል።—2 ቆሮንቶስ 6:14-18
-
-
ስመ ጥፉ በሆነችው አመንዝራ ላይ መፍረድራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
[በገጽ 237 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ቸርችል ‘ግልሙትናን’ አጋለጡ
ዊንስተን ቸርችል ዘ ጋዘሪንግ ስቶርም (በመሰብሰብ ላይ የሚገኘው ማዕበል) (1948) በተባለው መጽሐፋቸው ሂትለር “በኦስትሪያ ፖለቲካ ውስጥ የአመራር ቦታ የነበራቸውን ሰዎች ለመበከል ወይም ወደራሱ ለመሳብ” ሲል ፎን ፓፔንን በቪየና የጀርመን ሚኒስቴር አድርጎ እንደሾመው ጽፈዋል። በቪየና የዩናይትድ ስቴትስ ሚኒስቴር የነበረ ሰው ስለ ፎን ፓፔን ሲናገር “ፓፔን ድፍረትና አስመሳይነት በተሞላ ሁኔታ . . . ጥሩ ካቶሊክ በመሆን ያተረፈውን መልካም ስም እንደ ካርዲናል ኢኒትዘር ባሉት ኦስትሪያውያን ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እጠቀምበታለሁ ብሎ ነግሮኛል” ብለው ቸርችል ገልጸዋል።
ኦስትሪያ እጅዋን ከሰጠችና የሂትለር ሠራዊት ሰተት ብሎ ወደ ቪየና ከገባ በኋላ የካቶሊክ ካርዲናል ኢኒትዘር የኦስትሪያ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ የስዋስቲካ ባንዲራ እንዲያውለበልቡ፣ ደውላቸውን እንዲደውሉና የአዶልፍ ሂትለርን የልደት በዓል ለማክበር ጸሎት እንዲያደርጉለት አዘዙ።
[በገጽ 238 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
ቀጥሎ የቀረበው ጽሑፍ ከላይ ባለው ርዕስ ሥር በታህሣሥ 7, 1941 የኒው ዮርክ ታይምስ የመጀመሪያ እትም ላይ ወጥቶ ነበር:-
ለራይኩ የተደረገ ‘የጦርነት ቡራኬ’
“በፉልዳ የካቶሊክ አቡኖች በረከትና ድል እንዲገኝ ለመኑ . . .
የጀርመን ካቶሊክ አቡኖች በፉልዳ ባደረጉት ስብሰባ በሁሉም መለኮታዊ ቅዳሴዎች መጀመሪያና መጨረሻ ላይ የሚነበብ ልዩ ‘የጦርነት ቡራኬ’ እንዳወጡ አስታወቁ።
ቡራኬው አምላክ የጀርመንን የጦር ሠራዊት በመባረክ ድል እንዲሰጣቸውና የሁሉንም ወታደሮች ሕይወትና ጤንነት እንዲጠብቅ የተደረገ ልመና ነው። በተጨማሪም የካቶሊክ ቀሳውስት ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ በልዩ የሰንበት ስብከት ላይ ‘በምድር፣ በባሕርና በአየር’ ያሉ የጀርመን ወታደሮችን እንዲያስቡ አቡኖች አዘዋል።”
-