የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማስታወቂያዎች
    የመንግሥት አገልግሎት—2000 | ነሐሴ
    • ማስታወቂያዎች

      ◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?​—⁠እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ እና የሙታን መናፍስት​—⁠ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ የምታደርጉላቸውን ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ኮንትራት ማስገባት ይቻላል። ከወሩ መገባደጃ ጀምሮ “አዲሱ ሺህ ዓመት​—⁠የወደፊቱ ጊዜ ምን ተስፋ ይዞልሃል?” የሚል ርዕስ ያለውን የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ማሰራጨት እንጀምራለን። ኀዳር፦ የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ስርጭት ይቀጥላል። ጉባኤዎች በክልላቸው ውስጥ ለሚገኘው ለእያንዳንዱ የቤት ባለቤት የመንግሥት ዜና ቁጥር 36ን አበርክተው ከጨረሱ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይቻላል።

      ◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን መጽሔት ገጽ 8 ላይ በመጽሐፍ ጥናት የምናጠናው የዳንኤል መጽሐፍ ፕሮግራም ወጥቷል። ለቀጣዮቹ ጊዜያት ሁሉ መጠቀም ትችሉ ዘንድ ፕሮግራሙን ፎቶ ኮፒ አድርጋችሁ በመጽሐፋችሁ ውስጥ መያዝ ትችላላችሁ።

      ◼ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሌላ ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ የሒሳብ ምርመራው ለጉባኤው በማስታወቂያ መነገር አለበት።

      ◼ ጉባኤዎች በመስከረም ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2001 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። የቀን መቁጠሪያው በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በሩሲያና በስፓኒሽ ቋንቋዎች ይገኛል።

      ◼ በ2001 የአገልግሎት ዓመት የምትጠቀሙባቸው በቂ መጠን ያላቸው ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ በመላክ ላይ ናቸው። እባካችሁ እነዚህን ቅጾች በአግባቡ ተጠቀሙባቸው። ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ መዋል ይኖርባቸዋል።

      ◼ በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን እስከ ነሐሴ 31, 2000 ባለው ጊዜ ውስጥ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቁጥር በጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚካሄደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18-AM) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቡድኑ ከታቀፈው ከእያንዳንዱ ጉባኤ የመጽሔት አገልጋይ ማግኘት ይቻላል። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18-AM) ይደርሱታል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ ከመስከረም 6 በፊት ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። የአስተባባሪ ጉባኤው ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። የአስተባባሪ ጉባኤው ጸሐፊና ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ።

      ◼ በቅርቡ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው አዳዲስ ጽሑፎች:- አረብኛ፦ የዳንኤል ትንቢት፤ እንግሊዝኛ፦ የ1999 ማውጫ፣ ፈረንሳይኛ፦ የ1999 የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞች።

      ◼ እንደገና ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው:- እንግሊዝኛ፦ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ፣ ፍጥረት (ትንሹ)፣ ዲቫይን ጋይዳንስ፣ አዲሲቱ ዓለም ትርጉም:- ዲሉክስ (Dbi12) እና ባለማጣቀሻው መጽሐፍ ቅዱስ (Rbi8)። የቴፕ ክሮች:- ታላቁ ሰው፣ ዓይናችሁ ቀና ይሁን፣ ማቴዎስ፣ የመንግሥቱ ጣዕመ ዜማዎች 1-4፣ የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር፣ የመንግሥቱ ጣዕመ ዜማዎች ቁጥር 2 በሲዲ።

  • የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች
    የመንግሥት አገልግሎት—2000 | ነሐሴ
    • የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች

      ◼ ጥምቀት፦ የጥምቀት እጩዎች ቅዳሜ ጠዋት ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት በተመደበላቸው ቦታ መቀመጥ ይኖርባቸዋል። እያንዳንዱ ተጠማቂ ልከኛ ልብስና ፎጣ ይዞ መምጣት አለበት። ባለፉት ጊዜያት አንዳንዶች የለበሷቸው ልብሶች ተገቢ ያልሆኑና የተመልካቾችን ሐሳብ ወደ ሌላ የሚያዞሩ እንደሆኑ ተስተውሏል። የፖሊስተር ልብሶችን አለመጠቀሙ ይመረጣል። በተጨማሪም የጥምቀት እጩው ሊለብሰው የሚያስበው ልብስ ውኃ ሲነካው ሰውነትን የሚያሳይ ወይም ሰውነት ላይ የሚለጠፍ መሆን አለመሆኑን አስቀድሞ ማየት ጥሩ ይሆናል። ሽማግሌዎች አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎች ከእጩ ተጠማቂዎች ጋር በሚከልሱበት ጊዜ እያንዳንዱ ተጠማቂ እነዚህን ነጥቦች የተገነዘበ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። አንድ ሰው ራሱን መወሰኑን የሚያሳይበት የጥምቀት እርምጃ በግለሰቡና በይሖዋ መካከል ብቻ ያለ የግል ጉዳይ ነው። ስለሆነም ለፎቶግራፍ ለመመቻቸት ሲባል መዘግየት አይገባም።

      ◼ ደረት ላይ የሚለጠፉ ካርዶች፦ እባካችሁ ስብሰባው በሚካሄድበት ከተማ በምትቆዩበት ጊዜ ሁሉ እንዲሁም ወደ እዚያ ስትሄዱና ስትመለሱ ለ2000 የአውራጃ ስብሰባ የተዘጋጀውን ካርድ ደረታችሁ ላይ ለጥፉ። እንዲህ ማድረጋችን ብዙውን ጊዜ ጥሩ ምሥክርነት ለመስጠት ያስችለናል። ደረት ላይ የሚለጠፉት ካርዶችና መያዣቸው በስብሰባው ላይ ስለማይገኙ በጉባኤያችሁ በኩል ማግኘት ይኖርባችኋል። ደረት ላይ የሚለጠፉትን ካርዶች ለእናንተና ለቤተሰቦቻችሁ ለመጠየቅ ስብሰባው የሚጀመርበት ቀን እስኪደርስ ድረስ አትጠብቁ። የወቅቱን በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ መያዛችሁን አትርሱ።

      ◼ መስተንግዶ፦ የጉባኤ ጸሐፊዎች የማረፊያ ቦታ የሚፈልጉ ወንድሞችን ስም፣ ዕድሜና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች የያዙ ቅጾች ለአውራጃ ስብሰባው የመስተንግዶ ክፍል ወዲያውኑ መላካቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። በዚህ ዝግጅት አማካኝነት ያገኛችሁትን የማረፊያ ቦታ ለመተው ካሰባችሁ ወዲያውኑ ለአውራጃ ስብሰባው የመስተንግዶ ክፍል ማሳወቅ አለባችሁ። እንዲህ ማድረጋችሁ የመስተንግዶ ክፍሉ ማረፊያውን ለሌሎች ወንድሞች ለመመደብ ያስችለዋል።

      ◼ የፈቃደኝነት አገልግሎት፦ በስብሰባው ወቅት ከሚኖሩት የሥራ ክፍሎች በአንዱ ውስጥ ለማገልገል ጊዜ ልትመድቡ ትችላላችሁን? ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ቢሆንም እንኳ ወንድሞቻችሁን ማገልገላችሁ ትልቅ እገዛ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ እርካታ ያስገኝላችኋል። በዚህ ረገድ እርዳታ ማበርከት የምትችሉ ከሆነ በስብሰባው ቦታ ለሚገኘው ለፈቃደኛ አገልግሎት ማስተባበሪያ ክፍል አስታውቁ። ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ከወላጆቻቸው ወይም ኃላፊነት ሊወስድ ከሚችል ሌላ ትልቅ ሰው ጋር በመሆን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ።

      ◼ የማስጠንቀቂያ ምክር፦ የመኪናዎቻችሁ በሮች ሁልጊዜ መቆለፋቸውንና መኪናውን ሰብሮ ለመዝረፍ የሚጋብዝ ከውጭ ሊታይ የሚችል ነገር ትታችሁ አለመሄዳችሁን አረጋግጡ። ሌቦችና ኪስ አውላቂዎች በብዛት በተሰባሰቡ ሰዎች ላይ ዓይናቸውን ይጥላሉ። ውድ ዋጋ ያላቸውን ማናቸውንም ነገሮች መቀመጫችሁ ላይ ትታችሁ መሄዱ ጥበብ አይሆንም። ዙሪያችሁ ያለው ሁሉ ክርስቲያን ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አትችሉም። ሌሎች ለምን እንዲፈተኑ እናደርጋለን? ከውጭ የገቡ ሰዎች ልጆችን አባብለው ለመውሰድ ሙከራ እንዳደረጉ የሚገልጹ ሪፖርቶች ደርሰውናል። ልጆቻችሁን በማንኛውም ጊዜ ከዓይናችሁ አታርቋቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ