የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማስታወቂያዎች
    የመንግሥት አገልግሎት—2006 | ነሐሴ
    • ደብዳቤ (S-202) እንዳለው አረጋግጡ። ከሌለው ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ትችላላችሁ።

      ◼ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2007 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2007 እና የ2007 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ ይኖርባቸዋል።

      ◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- ቻይንኛ:- ክሪኤሽን፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ T-20 (ማጽናኛ)፣ አዲስ ዓለም ትርጉም (bi-12)፤ እንግሊዝኛ:- የ2005 የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ጥራዝ፣ አዲስ ዓለም ትርጉም በኤም ፒ3፤ ፈረንሳይኛ:- የ2006 የዓመት መጽሐፍ፤ ትግርኛ:- ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው (የጥምቀት ጥያቄዎችን የያዘ ቡክሌት)።

      ◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ የሙታን መናፍስት፤ እንግሊዝኛ:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ክሪኤተር፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ራእይ፣ ኮንኮርዳንስ፣ የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫ 30-85፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፣ የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፣ ጋይዳንስ ኦፍ ጎድ፣ የይሖዋ ምሥክሮችና ትምህርት፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ ኤ ሳትስፋይንግ ላይፍ፣ ሮድ ቱ ላይፍ፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም፣ የመዝሙር መጽሐፍ (ትንሹ)፤ ፈረንሳይኛ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ አዲስ ዓለም ትርጉም (bi-12)፤ ስዋሂሊ:- T-27 (መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል!)፤ ትግርኛ:- የዳንኤል ትንቢት፣ ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ hw (ሃው ቱ ስታርት ኤንድ ኮንቲኒው ባይብል ዲስከሽንስ)፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ sb-29 (የመዝሙር መጽሐፍ)።

  • በዘመቻ የሚሰራጭ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም
    የመንግሥት አገልግሎት—2006 | ነሐሴ
    • በዘመቻ የሚሰራጭ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም

      1 ሁሉም ሰው ለማለት ይቻላል የወፎችን ዝማሬ መስማትና ጀንበር ስትጠልቅ ማየት ያስደስተዋል። ይሁንና ብዙዎች እነዚህን ነገሮች የፈጠረው በሰማይ የሚኖር አፍቃሪ አባት መሆኑን አያምኑም። በመሆኑም የንቁ! መጽሔትን ልዩ እትም በማሰራጨት ይሖዋ ፈጣሪ ስለመሆኑ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችል ግሩም አጋጣሚ ተከፍቶልናል። (ኢሳ. 40:28፤ 43:10) የመስከረም ንቁ! መጽሔት ሙሉ በሙሉ “በእርግጥ ፈጣሪ አለ?” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው።

      2 በክልላችን ውስጥ:- የምትችሉ ከሆነ፣ በሁሉም ቅዳሜዎች ከጉባኤያችሁ ጋር ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት ለመካፈል ዝግጅት አድርጉ። እርግጥ ነው፣ በሌሎች ቀናትም ቢሆን ይህን ልዩ እትም ማበርከት ትችላላችሁ። ይህ መጽሔት በተለይ የአስተማሪዎችንና ከትምህርት ጋር ተያያዥነት ያለው ሙያ ያላቸውን ሰዎች ትኩረት መሳቡ አይቀርም። ስለሆነም በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ እነዚህን የመሰሉ ሰዎችን ለማነጋገር ልዩ ዝግጅት ልታደርጉ ትችላላችሁ።

      3 አንድ ሰው ፍላጎት እንዳለው ካሳየ በሌላ ጊዜ መልስ የምትሰጡበት ጥያቄ ማንሳት ትችላላችሁ። ለምሳሌ ያህል፣ ‘አፍቃሪ የሆነ ፈጣሪ ይህ ሁሉ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?’ ለማለት ትችሉ ይሆናል። ከዚያም በድጋሚ ስትሄዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 1 ወይም ምዕራፍ 11 ላይ ያለውን ሐሳብ ማስተዋወቅ ይቻላል። ወይም ደግሞ ፈጣሪ ለምድር ካለው ዓላማ ጋር የተያያዘ ጥያቄ በመጠየቅ ተመልሳችሁ ስትሄዱ በምዕራፍ 3 ላይ ለመወያየት ትመርጡ ይሆናል።

      4 በትምህርት ቤት:- ተማሪዎች ከሆናችሁ ይህን የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም ለአስተማሪዎቻችሁ ወይም አብረዋችሁ ለሚማሩ ልጆች ለምን በስጦታ መልክ አትሰጧቸውም? መጽሔቱን ዴስካችሁ ላይ ማስቀመጥ ብቻ እምነታችንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች እንዲነሱ መንገድ ሊከፍት ይችላል። በክፍላችሁ ውስጥ እምነታችሁን ለሌሎች ማስረዳት የምትችሉባቸው አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ እንዲሁም ሪፖርት አዘጋጅታችሁ እንድታቀርቡ ስትጠየቁ በዚህ መጽሔት ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ። በዚህ ረገድ መጽሔቱ “የወጣቶች ጥያቄ” በሚለው አምድ ሥር እናንተን ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ “በፍጥረት እንደማምን በደንብ ማስረዳት የምችለው እንዴት ነው?” የሚል ርዕስ ይዞ ይወጣል።

      5 ይሖዋ ሁሉን በመፍጠሩ ክብርና ውዳሴ ይገባዋል። (ራእይ 4:11) የመስከረም ወር የንቁ! መጽሔትን ልዩ እትም በቅንዓት በማሰራጨት ፈጣሪያችንን ማክበርና ሌሎች ይህን እንዲያደርጉ መርዳት እንችላለን።

  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎት—2006 | ነሐሴ
    • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?

      መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1

      “በችግር በተሞላው በዚህ ዓለም ውስጥ ብዙ ሰዎች ‘ሕይወት ይህን ያህል በመከራ የተሞላው ለምንድን ነው? አምላክ በእርግጥ ካለ፣ መከራን ለማስወገድ አንድ እርምጃ የማይወስደው ለምንድን ነው?’ በማለት ይጠይቃሉ። እርስዎስ እንዲህ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ይዟል።” ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ።

      ንቁ! ሐምሌ 2006

      “በዛሬው ጊዜ ውጥረት ውስጥ የገቡ ትዳሮች ቁጥር እየጨመረ ነው። ባለትዳሮች በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈውን ይህን ምክር ቢከተሉ ጥቅም የሚያገኙ ይመስልዎታል? [ኤፌሶን 4:32ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ ንቁ! መጽሔት ደስታ የሰፈነበት ትዳር ለመመሥረት የሚረዱንን ዘመን የማይሽራቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ያብራራል።”

      መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15

      “ለሰው ልጆች ችግሮች መፍትሔ የሚያስገኝ መንግሥት የምናይበት ጊዜ ይመጣል ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በማቴዎስ 6:9, 10 ላይ ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ዓይነት መንግሥት እንዲመጣላቸው ጸሎት እንዲያቀርቡ አስተምሯቸዋል። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ መጽሔት የአምላክ መንግሥት ከሰብዓዊ መንግሥታት በምን እንደሚበልጥና ለሰው ልጆች ምን በረከቶችን እንደሚያመጣላቸው ያብራራል።”

      ንቁ! ሐምሌ 2006

      ወጣት በምታገኙበት ጊዜ እንዲህ ማለት ትችላላችሁ:- “በአንተ ዕድሜ ያሉ ብዙ ወጣቶች ስለ ትዳር ያስባሉ። ይህን ጉዳይ በተመለከተ አስተማማኝ መረጃ ማግኘት የምትችለው ከየት ይመስልሃል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ጋብቻን ያቋቋመው ማን እንደሆነ እስቲ ተመልከት። [ማቴዎስ 19:6ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ደስተኛ ትዳር ለመመሥረት የሚረዱ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ያብራራል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ